Get Mystery Box with random crypto!

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ   የታሪኩ ርዕስ #የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት       #ክፍል | ISLAMIC SCHOOL

አሳዛኝ እዉነተኛ ታሪክ
 
የታሪኩ ርዕስ
#የሆድ_ዉስጥ_ፉም_እሳት
      #ክፍል ☞ አስራ ሰባት

ፀሀፊ ☞ #አሚር_ሰይድ





ነዋል ከምሬ ነዉ አንቺን ማዉራት ከጀምርኩ ቡሀላ ወላሂ በልቤ ገብተሻል እወድሻለሁ አለኝ.....

 
እኔም የሰማሁትን ማመን አቃተኝ ... ተክዞ የተኛዉ ጆሮየ ቀጥ አለ....በጣም ደስ አለኝ የምሆነዉን አሳጣኝ...አቁነጠነጠኝ...መቼም በስልኩ ድምፅ ነዉ እንጂ የዛን ጊዜ ሚፍታህ ቢያየኝ ተገርሞም ስቆም አያበቃም ነበር ...ይሄን ደስታየን በግድ መዋጥ አለብኝ ሴት ነኝ እና ደስታየን መቆጣጠር አለብኝ
.....አረ ሚፍታህ አቀልድ አልኩት
...........ወላሂ ከምሬ ነዉ ነዋል ደግሞ ጊዜ መስጠት አልፈልግም ቶሎ ሀላሌ እንድትሆኝ ነዉ የምፈልገዉ፡፡ Coc ከተፈተንሽ ቡሀላ ቤተሰቦቼን ነግሬ ሽማግሌ እልካለሁ አለኝ፡፡
...........እኔም እሺ ልሰብበት ጊዜ ስጠኝ አልኩት..ብዙ ሴቶች እየወደድን ቶሎ እሺ ማለት ሴትን ልጅ ያስንቃል ብለን እናስባለን እየወደድኩም ቢሆን መግደርደር የሴትነት ወጉ ስለሆነ እኔም ልቤ እየፈለገ አፌ ልሰብበት የሚለዉን አስቀደምኩኝ ፡፡

ከ ከ3ቀን ቡሀላ ሚፍታህ ደዉሎልኝ የጠየኩሽን ጥያቄ ምን ወሰንሽ ??? ብሎ ጠየቀኝ
......እኔም እሺ ተስማማቻለሁ አልኩት
ሚፍታህ በጣምምም ተደሰተ በስልክ ደስታዉን ሊቆጣጠረዉ አልቻለም....የእኔም ደስታ ከሱ ቢበልጥ እንጂ አያንስም ...ይገርመኛል የኔዉ ሞኙ ልቤ ከካሊድና ከየሱፍ አስበልጦ ለሚፍታህ ትኩረት ሰጥቷል፡፡

ሚፍታህ ረመዷን ሲያበቃ ኢንሻ አላህ ለኢድ ጅማ መጥቼ በአካል እንገናኛለን አለኝ፡፡
.....እኔም ለሚፍታህ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልሴ እሺ ብቻ ሁናል፡፡ ረመዷን ደረሰ ሚፍታህ ጋር ሁሌ ማታ ማታ እናወራለን ፡፡ ከማዉራታችን ብዛት አንዳንዴ ተራዊህ የማልሄድባቸዉ ቀናቶች ነበሩ...

ረመዷን አልቆ ኢድ ላይ ደርሰናል....ሚፍታህም ኢድን ቤተሰብ ጋር ለማክበር ከአዲስ አበባ ጅማ ተከስቷል.... ጅማ የኢድ ሶላት የምንሰግደዉ ጅማ ስታዲየም ነዉ.... ሰግደን ስንወጣ በስልክ ተደዋዉለን ለመጀመሪያ ጊዜ ሚፍታህ ጋር ተገናኘን . . እኔ እና ሚፍታህ ስንገናኝ ሁለት እህቶቹ ጋር አብሮ ነበር....አንዷ እህቱ የወንድሜ ሚስት ነዋል እንዴት ነሽ ብላ ሳመችኝ
.....እኔም ሚፍታህን እያየሁ በእህቱ ሁኔታ ተግባብተን ሳቅን
....ከመስገጃ ቦታዉ እየተመለስን ስለ አንዳንድ ነገሮች እያወራን ነዉ....ሚፍታህም እንዲህ አለኝ ፡- ነዋል ሁሉንም ቤተሰቦቼን እናቴም አባቴም እህቶቼም አንቺን እንደማገባ እቤት አሳዉቂያለሁ አለኝ ...
....ግን እናቴ አንቺን እንዳገባ አልተስማማችም አለኝ
.......እንዴት ላትስማማ ቻለች ??አልኩት
...........ነዋል እኮ ከ10ኛ ክፍል ቡሀላ አድጋ ነዉ እንጂ ገና ልጅ ናት ...አለችኝ አለኝ
...... እና ምን አልካት ??? አልኩት
............ነዋል ነዉ ማግባት የምፈልገዉ አሁን ትልቅ ሰዉ ሁናለች ቁመት ብጨምርም አብራ አስተሳሰብ ጨምራለች የትናንቷ ልጅ አይደለችም ብየ አሳኳት አለኝ
.......እናቴም፡- እሺ አንተ የወደድከዉን እኔም እወዳለሁ ብላ በኔ ሀሳብ ተስማማች አለኝ
እንደዚህ እየተጨዋወትን በደስታ ሁለታችንም በወሬ ፍንክንክ ብለን እኔን እቤቴ ሸኝቶኝ እሱም ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
 
በዚሁ በኢድ ቀን የሚፍታህ እናት እና አባት የኔን ቤተሰቦች ሊዘይሩ እኛ ቤት መጡ፡፡
ከበፊትም ጀምሮ የእኔ ቤተሰቦች እና የሚፍታህ ቤተሰቦች በጣም ይግባባሉ፡፡ በተለይ ደግሞ የኔ አባት እና ኡስታዝ(የሚፍታህ አባት)በጣም ይቀራረቡ  ይዋደዳሉ፡፡ አባቴ የሆነ ሀሳብ ሲይዘዉ..ግራ የሚያጋባ ጉዳዮች ሲገጥሙት የሚፍታህን አባት ብዙ ጊዜ ሲያማክር አስታዉሳለሁ፡፡

ሚፍታህ ቀን በቀን በደወለ ቁጥር ይቼ ቃላት ምላሱ ላይ አብራ የተሰፋች ነዉ የሚመስለዉ ... #እወድሻለሁ_አፈቅርሻለሁ ሳይለኝ ዉሎ አድሮ አያቅም ...እኔም ይሄን ቃል ስሰማ ደስታኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል... አሁን ዘመን ላይ ፍቅርን በአፋችን ስንገለፀዉ ለምላስ የብናኝ ያህል ክብደት አይኖረዉም ..እዉነተኛ ፍቅር ግን ማን ነዉ መግለፅ የሚችለዉ?? ስለፍቅር ምን በአንተ አስተሳሰብ ግለፅ ብላችሁ መቶ ሰዉ ብትጠይቅ የመቶዉም ሰዉ ስለፍቅር ያለዉ አመለካከት የተለያየ ነዉ ...ግን ለምን ይሆን በብዙ ሰዉ ልብ ያለን ፍቅር ቃላት ለመግለፅ የማይችለዉና ..ቃላቱ ሶስት ቃላት ናቸዉ #ፍቅር ግን ስለፍቅር ምን ትላለህ ሲባል ፍቅርን በቃላት መግለፅ አልችልም ሲሉ ይደመጣሉ..አንዳንድ ሙሁር ተብየዎች..ገጣሚዎች..ዘፋኞች ..ፍቅርን በማይታይ ህልም ሲስሉት እናስተዉላለን..ግማሹ የሰዉነቷን ክፍል ቆራርጠዉ አይኗ ከዋክብት..ጥርሷ ነጭ በረዶ ..ሷቋ የፀሀይ ጮራ ቁመቷን ተራራ..አፍንጫዋን ጥሩ መአዛ ብቻ የሚቀበል መጥፎ ሽታን የሚያስወግድ ..ችቧ አይሞላም ወገቧ ማር እሸት ነዉ ቀለቧ እየተባለ ..ወዘተ ብለዉ ሲጠቆሱት እያየን ነዉ...ግን ይሄ አገላለፅ ፍቅርን ይገልፀዋል ወይ??

★★★አንዳንድ ሠዉ ስለ ሌላ ሰዉ በዚህ ፍቅር ተብየዉ እየተጨነቀ ያስብና እየተቆጨ ይኖራል..በእርግጥም ሌላ ሠዉ መልካምን ለማድርግና ችግሩን ለማቅለል መጨነቅ ማሰብና መቆጨት መልካም ነዉ.
.
.
ማፍቅር መልካም ነገር ነዉ* አላህ በሰዎች መካከል የሚስቀምጠዉ ደስታን፣እርካታን የሚያጣጥሙት የሂወት ቅመም ነዉ ይህ ፍቅር ግን ያለቦታዉ ገብቶ የማይዋልበት ቦታ ሲገባ ስቃይና መከራ ይሆናል.
..
ከመፍትሄ ይልቅ ችግር ከእረፍት፣ ይልቅ ስቃይ ፣ከደስታ ይልቅ ሀዘንን ያበዛል .በተለይ በልጅነት ሂወት ላይ ሲከሰት መካራዉ ይደራረባል ሂወት አጭር ናት ከትደሰትክባት በሚል የተሳሳተ ተስፋ አጭሯን ሂወት ለስቃይና ለመከራ የሚያደርግ ስስት ዉስጥ ይገባል .
"
"
በጓደኛም ይሁን በአይን ስህተት* በጅንጀናም ይሁን በዉሸት ፍቅር የያዛቸዉ ይህንን ፍቅር የሚሉትን ስሜት ለማስታገስና ለማከም የማይገባዉ ጉድጓድ ዉስጥ ይገባሉ .ለመዉጣት ደግሞ መዉጫ ቀዳዳ ይጠፋል ..

:
ለማናዉቃቸዉና ለማንተማመንባቸዉ ጊዜ አዊይ ስሜቶች የማናዉቀዉን የማንተማመንበት ጣፋጭ ሂወት እናበላሻለን ከሸይጧን ግፊት ለሚደረግበት ስህተት ፍቅር በሚል ሽንገላ ከአላህ ሽልማት የሚጠበቀዉን እድል እናፈርሳለን...ግን ለዚህ ሁሉ መፍትሄዉ ፍቅርን በሰዎች ሁሉ ለሰጠዉ ፈጣሪ አመስግኖ መጀመሪያ ፍቅርን ለሰጠን ፈጣሪ ፍቅሩን ለፈጣሪ ከሰጠነዉ ሁላችንም አሸናፊዎች ነን፡፡ ፍቅርን ሳናባክን መጀመሪያ የሰጠንን ፈጣሪ አንርሳ ለምን የሰጠንን ነገር ሁሉም የሚቀመጠዉ በሂደት ነዉ...
መጀመሪያ ማስቀመጥ ያለብን ለፈጣሪ መሆን ሲገባዉ ነገር ግን ይሄን የመጀመሪያ እድል ለፍጡር ከተደረገ የፈጠረህን ፈጣሪ ሀቅ አጉድልሀል ..ባለቤቱ አምጥቶ አደራ ብሎ አስቀምጦ የሄደዉን ለሌላ ለማያገባዉ ከሰጠን ጥፋቱ አደራዉን የካደዉ ነዉ ...አደራችንን የሰጠንን ፈጣሪ እያስታወስን እናስቀምጥ፡፡ የዛን ጊዜ እኛ በፈጣሪ እገዛ አሸናፊዎች ነን፡፡

      ከኢድ ቀን ቢያነስ ከ15 ቀናት ቡሀላ የሚፍታህ አባት እንደ ሽምግልና ባይሆንም የአባቴን ሀሳቡን መረዳት ያክል እሳቸዉ እና የሚፍታህ አጎት ሁነዉ አባቴ እቤት ባለበት ሰአት መጡ....

ለአባቴ -------እኔና ሚፍታህ በአንድ ጎጆ ለመኖር መጨረሳችንን ሁሉንም ነግረዉት ግን የአንተ ፍቃደኝነት ያስፈልጋል .... ሚፍታህ ልጅህን ነዋልን ማግባት ይፈልጋል ፍቃደኛ ነህ ወይ ??? ብለዉ ጠየቁት