Get Mystery Box with random crypto!

2. መገለጥ (revelation) መገለጥ መናፍስትን በመለየት የፀጋ ስጦታ ውስጥ ትልቁን ስፍራ የ | ካቦድ ☁️

2. መገለጥ (revelation)

መገለጥ መናፍስትን በመለየት የፀጋ ስጦታ ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚወስድ ነው

ይህ በህልም ፣ በሌሊት ራዕይና በቀጥታ ራዕይ ምስል ከሳች ሆኖ የሚመጣ የመገለጥ አይነት ሲሆን የመንፈሱን አይነትና ባህሪ በግልጽ መረዳት የሚያስችለን ፀጋ ነው

ርኩሳን መናፍስት ራሳቸውን በተለያየ አይነት ማንነት የሚገልጡ ሲሆን እነዚህን ማንነታቸውን ሊወክሉላቸው በሚችሉ ምልክቶች ራሳቸውን መስለው የሚኖሩ ናቸው

እነዚህ በብዛት ከሚገለጡባቸው ማንነቶች መካከል በጥቂቱ:- እባብ፣ዘንዶ፣ የሌሊት ወፍ፣ አሞራ፣ውሻ የተለያዩ አውሬዎች እንደ ጅብ፣ ተኩላ፣አምበሳ...ወዘተ ሲሆኑ በሞቱ ሰዎች በመመሰል፣ ጭለማንና ጭጋግን በመልበስ የሚደረጉ መገለጦችንም የሚጨምር ነው

ርኩሳን መናፍስትን መለየት በራዕዮች ወይንም በህልም እንደነዚህ ያሉ የክፉው መገለጦችን ከመንፈስ ቅዱስ በመረዳት የሚደረግ ነው

በመገለጥ መናፍስትን ማወቅ የመለየት ፀጋ በሌላቸው ሰዎችም ሊታይ የሚችል ነው ። ይህ አይነት መገለጥ ታዲያ ከእግዚአብሔር ዘንድ አሊያም ደግሞ ከራሱ ከክፉ ሆኖ ሊመጣ ይችላል

በመጽሐፍ ቅዱሳችን መዝሙረኛው ዳዊት ከእግዚአብሔር ስለሚሰጥ መገለጥ “የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።” በማለት ይናገራል ። መዝ 13፥4

በሌላ ስፍራም “ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።” ብሎ እግዚአብሔር ለሚፈሩት አስቀድሞ ስለሚሰጠው መገለጥ ይናገራል። መዝ 60፥4

ከክፉው የሆነው መገለጥ በአብዛኛውን ጊዜ ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ የሚመመጣ ሲሆን በተጨማሪም በሌሊት ራዕይና በህልም ሰዎችን ለማርከስ ይጠቀምበታል

@intoglory