Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ። የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ | Injibara University

የ2015 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር የትንሳኤ በዓልን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል ፡፡
በበዓሉ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በላይ ዘለቀ (ዶ/ር) እና ሌሎችም የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ አመራሮች ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተማሪዎችም በዓሉን በመመገቢያ አዳራሽ ውስጥ በልዩ ሁኔታ በተዘጋጀው የሻይ ቡና እና የምሳ ግብዣ በጋራ ማክበራቸው የተለዬ የአንድነት ድባብ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

በዓሉ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በፀጥታና ደህንነት ሥራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ የፌደራል ፖሊስ አባላትም በልዩ ሁኔታ በተዘጋጀላቸው የምሳ ግብዣ በጋራ ሆነው በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

ሚያዚያ 8/2015፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ