Get Mystery Box with random crypto!

ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለመምህራን ሲሰጥ የነበረው Digital Literacy ስልጠና ተጠናቀቀ። | Injibara University

ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለመምህራን ሲሰጥ የነበረው Digital Literacy ስልጠና ተጠናቀቀ።

የምህንድስና እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ከአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ለሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች እና ለዲኖች እንዲሁም ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎች ከመጋቢት 27/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 05/2015 ዓ.ም ሲሰጥ የነበረው የDigital Literacy ስልጠና ተጠናቋል፡፡

የስልጠናዉ ዓላማ ተመራቂ ተማሪዎች በበይነ መረብ (online) አማካኝነት የሚሰጠውን የመዉጫ ፈተና ሳይቸገሩ እንዲፈተኑ ቀድመው ልምምድ እንዲያደርጉ እና ግንዛቤያቸውን ለማሳደግ የሚረዳ መሆኑ ተገልጿል። መምህራንም ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ብቁ እንዲሆኑ አቅጣጫ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል በስልጠናው ተሳታፊ ሆነዋል።
በስልጠናው ለተመራቂ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም እና፣ ስለ ኦንላይን ፈተና ጠቅላላ ገለጻ በመስጠት በመምህራን የተዘጋጁ "ሞዴል" ጥያቄዎች ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ E-learning ሲስተም መጫን፤ የኦንላይን ፈተና ስርዓትን ማለማመድ እንደሚቻል ተዳሷል።
የምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን ደመቀ አለነ፣ የአይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዳውድ ኡመር እና የሲስተም አድሚኒስትሬተር ባለሙያ አዱኛ ተሰማ አማካኝነት ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በ 2015 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪ ያላቸዉ ኮሌጅ ዲኖችና ምክትል ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ሚያዚያ 5/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ