Get Mystery Box with random crypto!

አንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ (Agri service Ethiopia) ጋር በጋራ ለ | Injibara University

አንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከ አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ (Agri service Ethiopia) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
---------------
ዩኒቨርሲቲው ስምምነቱን የተፈራረመው አንከሻ ወረዳ ከሚገኘው እና ማህበረሰብ ልማት ላይ ከተመሰረተው “አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ” ከተሰኘ ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር ሲሆን በግብርና እና በተለያዩ የሙያ መስኮች ላይ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ተግባራትን ለማከናወን በሚያስችል አቅጣጫ ነው፡፡

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ጋርዳቸው ወርቁ ዶ/ር አግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ በዘረጋው ሥርዓት ዩኒቨርሲቲው ያለውን ኃይል በመጠቀም በምርምር ታግዞ በርካታ ችግር ፈቺ ተግባራትን በማከናወን በግብርና፣ በጤና እና በትምህርት እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

የአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ ከአንከሻ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን በወረዳው ውስጥ ካሉ ቀበሌዎች ስድስቱን በመምረጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉን የማህበረሰብ ክፍል ቅድሚያ ዕድሉን በመስጠት እና በመለየት የስንዴ፣ የጤፍ እና የበቆሎ ምርጥ ዘር በማቅረብ፣ ለእንስሳት እርባታ የሚሆኑ በጎችን እና ዶሮዎችን በመስጠት፣ የጓሮ አትክልት ዘሮችን በማቅረብ፣ ለአሲዳማ መሬት ማከሚያ የሚሆን ኖራ በነጻ በመስጠት ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የተለያዩ ልማታዊ እና ግብረገባዊ ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ግብረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid034nQeCkvv2zXv5YqYARXSsdBP7EYHWiR3Nx9E9oHHrTbHqeuihnDLRWfQq2zXKfzLl/?app=fbl
መጋቢት 5/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ