Get Mystery Box with random crypto!

ለልዩ ፍላጎት መምህራን የብሬል ኮንትራክሽን ስልጠና ተሰጠ *********** በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ | Injibara University

ለልዩ ፍላጎት መምህራን የብሬል ኮንትራክሽን ስልጠና ተሰጠ
***********
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪነት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር አምስት ወረዳዎች ለሚገኙ የልዩ ፍላጎት መምህራን የብሬል አህጽሮተ ጽሑፍ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት እና ሥነ ባህርይ ኮሌጅ መምህራን አማካኝነት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ የልዩ ፍላጎትን የሙያ ብቃት ማሳደግ፣ የተማሪዎችን ትክክለኛ የብሬል ጽሑፍ ስርዓት እንዲያውቁ ማስቻል እና የመማር ማስተማሩን ሂደት የተሳለጠ ማድረግ እንዲሁም በልዩ ፍላጎት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ የሚያስገነዝብ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ቃላትን በፊደል ማሳጠር፣ ሀረግ እና አረፍተነገርን በቃላት ማሳጠር፣ የተለያዩ ስርዓተ-ነጥቦችን ትክከለኛ አጠቃቅም እና መሰረታዊ የሂሳብ ስሌቶች የሚሉ አርዕስቶች በስልጠናው ተዳሰዋል፡፡

ስልጠናው ከእንጅባራ ከተማ አስተዳድር፣ ባንጃ፣ ጓጉሳ፣ አንከሻ እና አየሁ ወረዳዎች የተውጣጡ 30 (ሰላሳ) የልዩ ፍላጎት መምህራን የተሳተፉበት ሲሆን መ/ር ሀብታሙ ዓለምነህ፣ መ/ር ሀብታሙ ገኔ፣ መ/ር ካሳሁን አንተነህ እና መ/ርት ጥሩዬ አብዲ በተለያየ ጊዜ ለአራ ቀናት ያክል ስልጠናውን ሰጥተዋል፡፡
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ