Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የተመደቡለትን ተማሪዎችን እየተቀበለ | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም የተመደቡለትን ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው፡፡
------------------
በትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤታቸው ከ50% በታች የሆነባቸው እና የአቅም ማሻሻያ ትምህርት መውሰድ የሚችሉ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች በመግባት ላይ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን 1900 (አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ) በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ከሚገቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተጠቃሚ ተማሪዎች መካከል ከ5መቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
የተማሪዎች ቅበላ መርሐ ግብር ም በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል፡፡
መጋቢት 4/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ