Get Mystery Box with random crypto!

ለ 'STEM' ፕሮግራም ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ | Injibara University

ለ "STEM" ፕሮግራም ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ "STEM" ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሶስቱም የእንጅባራ ከተማ አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተመረጡ ተማሪዎች መደበኛ የሳይንስ ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት የህይወት ክህሎት ሥልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የሥልጠናውን ላይ የዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ ሽፈራው ፕሮግራሙ ተማሪዎች በመደበኛው የትምህርት ጊዜያቸው በክፍል ውስጥ በቲዎሪ ደረጃ የሚማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር ቀይረው ለማየት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር መልካም አባተ ፕሮግራሙ የትምህርት ጥራትን ከማሻሻል አንጻር ከታች ክፍል መጀመሩ ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ከሶስቱም ትምህርት ቤቶች የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በመምረጥ በተለይ በሳይንስ ትምህርቶች ዙሪያ ያላቸውን የእውቀት ክፍተት ለመሙላት ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲው ሙህራን የተግባር-ተኮር ትምህርት የሚሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል። ይህ ፕሮግራም እንደ ዩኒቨርሲቲ በ2014 ዓም በክረምት መርሃ ግብር (Summer outreach) የተጀመረ መሆኑን ጠቅሰው እና በበጋው ደግሞ ቅዳሜ እና እሁድን በመጠቀም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንደሚሰጥ ገልጸዋል።


https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0BGXg5xPxN4xVqsVtc4CS56qYGmpGYHMmsQQsfQ9tF54eMe6rRL7ScfSPfUtQYtcxl/?app=fbl

"Every Child is a Scientist"
የካቲት 2/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ