Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በጃዊ ወረዳ በዩኒቨርሲቲው እየለማ ያለውን የሽምብራ እና | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በጃዊ ወረዳ በዩኒቨርሲቲው እየለማ ያለውን የሽምብራ እና የስንዴ ልማት ጎበኙ።
////////////////

በጉብኝቱም በግብርና ልማት ስራው ባጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ የትብብር እና የልማት መስኮች ዙሪያ ከጃዊ ወረዳ እና ከጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ በጉብኝት ወቅት እንድተናገሩት የግብርና አመራረት ሂደትን ሳይንሳዊ ዘዴን በመከተል በአካባቢው ለተሰማሩ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ምሳሌ በመሆን እንዲሁም ዘመናዊ የእርሻ ቴክኖሎጂንና ግብዓትን በተሻለ መንገድ በመጠቀም ምርት እና ምርታማነትን በሚያሳደግ መልኩ ዩኒቨርሲቲው መስራት አለበት ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በዚህ ዓመት ያጋጠሙ ችግሮች በቀጣይም እንዳያጋጥሙ ሳይንሳዊ መፍትሄያቸውን ከወዲሁ መቀመር ያስፈልጋል ብለዋል።
በመጨረሻም በሁለቱም የግብርና ቦታዎች ተሰማርተው ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ለሚገኙ ሰራተኞች እና አስተባባሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጥር 27 2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ