Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡ ////////////////// የጽዳት ዘመ | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡
//////////////////
የጽዳት ዘመቻውን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና የተማሪ ህብረት ተወካዮች አስጀምረውታል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች ጉዳይ ም/ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን(ዶ/ር) በማስጀመሪያው እንደተናገሩት ተማሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት የጽዳት ዘመቻ በማካሄዳቸው መልካም ነገር መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲተውን ጽዱ እና ለመማር ማስተማር ምቹ እንዲሆን የተማሪዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ወሀቤ አያይዘውም ግቢው አረንጓዴነቱን ጠብቆ እንዲቆይ ከጽዳት ባለፈ ተማሪዎች አረንጓዴ ቦታዎችን ባለመረገጥ እና በመንከባከብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በላይ ዘለቀ(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው “አረንጓዴው ግቢ” የሚል መጠሪያውን ይዞ እንዲቀጠል የተማሪዎች ተሳትፎም አስፈላጊ በመሆኑ ተማሪዎች ያደረጉት ነገር መልካም መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ከተማሪዎች ጋር በርካታ ስራዎችን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ዮሐንስ ጓዴ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ለማጽዳት ያሰብነው ከማጽዳት በተጨማሪ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በጋራ ለመስራት በማሰብ ነው ብሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በላይ ውብ እና ማራኪ እንዲሆን በቀጣይም በተከታታይነት የጽዳት ዘመቻ እንደሚያከናውኑ ተማሪ ዮሐንስ ተናግሯል፡፡
ጥር 6/2015 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ