Get Mystery Box with random crypto!

‘‘የትምህርት ዘርፍ ተግዳሮቶች እና መውጫ መንገዶች'‘ በሚል መሪ ሀሳብ የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደ | Injibara University

‘‘የትምህርት ዘርፍ ተግዳሮቶች እና መውጫ መንገዶች'‘ በሚል መሪ ሀሳብ የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የውይይት መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ ያስጀመሩት የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንግዳ ዳኛው ደግሞ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ የመድረኩ ዓላማ በትምህርት ስርዓታችን የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች እና መውጫ መንገዶችን ለማመመላክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በባህርዳር ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር አቢይ ይግዛው ቁልፍ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዓለምን ለመለወጥ ብቸኛው መንገድ ዕውቀት መሆኑን ጠቅሰው ሀገርን በሁሉም ዘርፍ ለማሳደግ የትምህርት ስርዓታችንን ማሻሻል ይገባል ብለዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥሉት አምስት እና አስር ዓመታት ስትራቴጅክ ዕቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው ከለያቸው የትኩረት መስኮች መካከል አንዱ የትምህርት ጥራት፣ ፍትሃዊነት እና አግባብነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የትምህርትና እና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ የቀጣይ ስምንት ዓመት የምርምር እና የማህበረሰብ አግልግሎት እቅድ በኮሌጁ ዲን በዶ/ር ዓለም አምሳሉ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል እቅዱም በትምህርት ዘርፍ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት በቁርጠኝነት መዘጋጅቱን በግልጽ አሳይቷል።
በውይይት መድረኩ የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እና የትምህርት እና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ መምህራን፣ የብሄረሰብ አስተዳደሩ የወረዳ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት እና ስነ-ህሪ ኮሌጅ ዲኖች ተገኝተዋል።
ህዳር 6/2015 ዓ.ም