Get Mystery Box with random crypto!

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋሸራ (ዳንግሌ) በግ ዝርያ ማሻሻል ላይ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ | Injibara University

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የዋሸራ (ዳንግሌ) በግ ዝርያ ማሻሻል ላይ አበረታች ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በዛሬው እለት የመስክ ጉብኝት እና በአመት ሁለቴ ከዝናብ መውጫና መግቢያ ጋር ተያይዞ የሚሰጠውን የውስጥ ጥገኛ በሽታን የማከም አገልግሎትም ተሰጥቷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዝርያው እየጠፋ የነበረውን የዋሸራ (ዳንግሌ) በግ ለመታደግ ICARDA ከሰተኘ ድርጅት ጋር በመሆን በፋግታ ለኮማ ወረዳ በዝምብሪ መስክ ዙሪያ ባሉ 4 መንደሮች 622 አባውራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማህበረሰብ ዓቀፍ ዝርያ ማሻሻል ፕሮጀክት ቀርጾ በመስራቱ አበረታች ለውጦች መታየታቸውን ተናግረዋል፡፡ በማህበር ለተደራጁ የአካባቢው ማህበረሰቦች 114 አውራ በጎች መሠራጨታቸውንም ተናግረዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር እና የእንስሳት ህክምና መምህር የሆኑት ዶ/ር መልካም ፕሮጀክቱ ሥራ ከጀመረበት ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ነጻ የበጎች የውስጥ ጥገኛ ህክምና እንደሚሰጥ ተናግረዋል። አርሶ አደሮቹ የእንስሳት መኖ እንዲያለሙ ሰርቶ ማሳያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ይህንን ፕሮጀክት በሌሎች ወረዳዎችም ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዋሸራ (ዳንግሌ) በግ የማህበረሰብ አቀፍ ዝርያ ማሻሻል ፕሮጀከት አስተባበሪ የሆኑት መምህር መልካም ጸጋ የዋሸራ በግ ዝርያ ከሌሎች የበግ ዝርያዎች የሚለዩት በሶስት ወር ለገበያ የሚደርሱ እና ከአንድ አስከ አራት በጎችን በአንዴ የሚወልዱ መሆናቸው ተናግረዋል፡፡
መርጌታ ስለሺ መንበሩ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በሚሰጠው ህክምና እና የአውራ በጎች ስርጭት ጥሩ ዝርያ ያላቸውንማርባት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው ዩኒቨርሲቲውን አመስግነዋል፡፡
ታህሳስ 2/2015 ዓ.ም