Get Mystery Box with random crypto!

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሳምንታዊ የቴሊቪዥን ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ | Injibara University

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሳምንታዊ የቴሊቪዥን ፕሮግራም ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ስለዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ መረጃ ገለጻ አድርገዋል። የዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ እንዲሁም የትኩረት መስክ አድርጎ በለያቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚያከናወናቸውን ተግባራት፣ ተሞክሮዎችን ለማስፋት ተጨማሪ ጉልበት የሚሆን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በየ15 ቀኑ የሚተላለፍ ፕሮግራም መጀመሩን አብስረዋል።
በመርሐ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው የህዝብ እና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መ/ርት ይርጋ ታደሰ የፕሮግራሙ አስፈላጊነት መሰረት ያደረገ ገለፃ አድርገዋል።
ከዚህ በፊት በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎች ተደራሽ ሲደረጉ መቆየታቸውን ጠቅሰው ከዩኒቨርሲው ማስፋፊያ ሥራዎች አንጻር በቴሌቪዥን አየር ሰዓት ተደራሽ ለማድረግ መሰራቱን ገልፀዋል።
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተወካይ እና የብራንዲንግና ሁነት ዝግጅት ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሰረት አስማረ በበኩላቸው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ስራዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተደራሽ ለማድረስ እንሰራለን ብለዋል።
ተሳታፊዎችም ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን ተግባራት ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ያለበትን ሂደት አድንቀው በፕሮግሙ መደሰታቸውንም ገልጸዋል።

በመርሐ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዊ ብሄ/አስ ከፍተኛ አመራሮች፣ የካውንስል አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የቴሌቪዥን ፕሮግራሙ በየ15 ቀኑ የሚተላለፍባቸው ቀናት፦
ቅዳሜ ምሽት፡ 1፡30-2፡00
ማክሰኞ ረፋድ፡ 5፡30-6፡00
ሐሙስ ቀን፡ 10-30-11-00 ናቸው

ህዳር 15/2015ዓ.ም