Get Mystery Box with random crypto!

የአርባምንጭ ሙዝ፣ የአዊ ድንች እና የጨንቻ አፕል ምርቶች 'ብራንዲንግ' መርሐግብር ተካሄደ፡፡ -- | Injibara University

የአርባምንጭ ሙዝ፣ የአዊ ድንች እና የጨንቻ አፕል ምርቶች "ብራንዲንግ" መርሐግብር ተካሄደ፡፡
------------
ስትራቴጂክ ተብለው ከተለዩት የግብርና ምርቶች መካከል የአርባ ምንጭ ሙዝ፣ የጨንቻ አፕል እና የአዊ ድንች ምርቶችን ብራንድ ተደረጉ
በኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን አነሳሽነት በአይነታቸው የተለዩ በኀብረት ሥራ ማኅበራት አባላት የሚመረቱ “የአርባ ምንጭ ሙዝ”፣ “የአዊ ድንች” እና “የጨንቻ አፕል” ምርቶች አዳዲስ የብራንድ መለያ እና ስያሜ ተሰጣቸው።
በግብርና ሚኒስቴር የኢንቨስትመንትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶክተር) እንዳሉት፤ ይህ አይነቱ ተግባር የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ መሪነት ማረጋገጥ የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲው አንዱ ግብ ነው ብለዋል።
ከውጭ ሀገራት የሚገቡ የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካትና በሀገር ውስጥም ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ምርት ማምረት ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል።
ከዚህ በፊት የሀገር ውስጥ ምርቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን ጠብቀው ቢመረቱ እንኳን ብራንድ አለመዘጋጀቱ ፈትኗቸዋል ያሉት ዶክተር ሶፊያ፤ ይህን ችግር ለመቅረፍ መሰል የብራንዲንግ ሥራዎች አሥፈላጊ ናቸው ብለዋል።
የግብርና ምርቶች ብራንዲንግ የገበያ ችግሮችን ለመቅረፍና የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ለመስጠት ዕድል ይሰጣል ሲሉ ገልፀዋል።
በዓይነታቸው የተለዩ በኅብረት ሥራ ማህበራት አባላት የሚመረቱ የአርባምንጭ ሙዝ፣ የአዊ ድንች እና የጨንቻ አፕል ምርቶች በሀገር አቀፍ ገበያ በስፋት ተደራሽ የመሆን እምቅ አቅም አላቸው።
በአሁኑ ጊዜ በደካማ የገበያ ትሥሥር፤ በገበያ መሰረተ ልማት እጦት እና በእሴት ሰንሰለት ውስጥ ጥቂት ነጋዴዎችና ደላሎች እንዳሻቸው የዋጋ ተመን በማውጣት ገበያውን በሚቆጣጠሩበት የግብይት ሥርዓት በመገደባቸው አምራቹም ሆነ ሸማቹ ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቆይተዋል ተብሏል።

ብራንዲንግ በምርት ግብይት ማዕቀፍ ውስጥ ከመወዳደሪያ አቅም መለኪያዎች ውስጥ አንዱ እና አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ወደፊት በሌሎች ምርቶች ላይ አተኩሮ ይሠራል።

(ኢ.ፕ.ድ) ሰኔ 28/2014 ዓ.ም