Get Mystery Box with random crypto!

#Telegram የማንፈልጋቸው የቴሌግራም ግሩፖች(Groups) ላይ ማንም ሰው አድ(Add) እንዳያ | ETHIO TECH™

#Telegram
የማንፈልጋቸው የቴሌግራም ግሩፖች(Groups) ላይ ማንም ሰው አድ(Add) እንዳያደርገን ማድረግ እንዴት ይቻላል?

#ቴሌግራም ላይ ብዙ ዓይነት ግሩፖች አሉ፡፡ እነዚህ ግሩፖች ሁሉንም ላንፈልጋቸው እንችላለን፡፡ አንዳንዴ ግን ፈለግንም አልፈለግንም ሳናውቀው የተለያዩ ግሩፖች ላይ አድ)Add) ተደርገን እናያለን፡፡ እንደውም የማንፈልጋቸው ግሩፖች ላይ አድ እየተደረግን የተማረርን ሰዎች እንኖራለን፡፡
ስለዚህ ማንም ሰው እየተነሳ የፈለገው ግሩፕ ላይ አድ እንዳያደርገን ለማድረግ እንችላለን፡፡በጣም ቀላል ነው፡፡ እነዚህን ስቴፖች መከተል ነው።

1. ቴሌግራም አፕሊኬሽን እንክፈት
2. ከላይ በግራ በኩል ያሉት ሶስተ ሰረዞች ክሊክ እናድርግ
3. ከሚመጡት አማራጮች Settings የሚለውን ክሊክ እናድርግ
4. ከዚያ Privacy and Security የሚለውን ክሊክ እናድርግ
5. ከዚያ ከሚመጡት አማራጮች Groups የሚለውን ክሊክ ማድረግ
6. Groups የሚለውን ክሊክ ስታደርጉ ሁለት ምርጫዎች ይመጣሉ Everybody እና My Contacts የሚሉ፡፡ እናንተ My Contacts የሚለውን ምረጡ፡፡
7. ከዚያ ከላይ ማረጋገጫ(√) ክሊክ ማድረግ፡፡
በቃ ከአሁን በሁዋላ ማንም ሰው የፈለገው ግሩፕ ውስጥ አድ(Add) አያደርጋችሁም ማለት ነው፡፡

Comment @On_living

#LIKE
#SHARE
#EYORIKATECH