Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም ሃክ ተደርጓል ? ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ ተደርገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚ | Abrilo info Tech

ኢትዮ ቴሌኮም ሃክ ተደርጓል ?

ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ ተደርገ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ትክክል እንዳልሆነ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ አሳወቁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ይህን ያሳወቁት ኢትዮጵያ ቼክ ለተሰኘው የመረጃ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።

ባለፉት ቀናት ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ እንደተደረገ የሚጠቁሙ የተለያዩ መልዕክቶች እና መረጀዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ነው፤ በርካቶች ደግሞ አንድ ኮድን በመጠቀም በነፃ የኢንተርኔት ፓኬጅ ማግኘት እንደቻሉ ሲፅፉ ነበር።

በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ፥ "ኢትዮ ቴሌኮም ሀክ አልተደረገም። ስራችን ሳይቋረጥ አዳዲስ አገልግሎቶች ላይ ማስተካከያ (configuration) እያረግን ነው። በዚህ ምክንያት ጥቂት ደንበኞቻችን አንዳንድ አገልግሎቶችን [በነፃ] ሊወስዱ/ሊያገኙ ችለዋል። ሁኔታውን እኛም አውቀነው እየሰራንበት ነው፣ በቁጥጥራችን ስር ነው" ብለዋል።

Source @tikvahethiopia