Get Mystery Box with random crypto!

#አስገራሚ #አረንጓዴ #ሻይ #የጤና #ጥቅሞች #በጥቂቱ አረንጓዴ ሻይ አረንጓዴ ሻይ ለመድሀኒትነት | Information Science and Technology

#አስገራሚ #አረንጓዴ #ሻይ #የጤና #ጥቅሞች #በጥቂቱ
አረንጓዴ ሻይ
አረንጓዴ ሻይ ለመድሀኒትነት ለሺህ አመታት ሲጠቀሙበት ኑረዋል፣ መነሻው ከቻይና ቢሆንም በመላው ኤዥያ በስፋት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
ይህ መጠጥ በርካታ ጥቅሞች ሲኖሩት ከነዚህ ጥቅሞቹ መካከል የደም ግፊትን ከመቀነስ እስከ ካንሰርን መከላከል ናቸው።
የአረንጓዴ ሻይ ከጥቁር ሻይ አንጻር ይበልጥ የጤና ጥቅሞች ያሉት በምርት ሂደቱ ምክንያት ነው።
የጥቁር ሻይ አመራረት በማብላላት መልኩ ሲሆን የአረንጓዴ ሻይ አመራረት ደግሞ የማብላላት ሂደትን በማስወገድ ነው።
በዚህም ምክንያት፣ አረንጓዴ ሻይ ከፍተኛ የሆነ የአንቲ ኦክሲዳንት እና ፖሊ-ፌኖልስ መጠን አሉት እነዚህም ነገሮች አረንጓዴ ሻይ ብዙ ጥቅሞች እንዲኖሩት ምክንያት ናቸው።
ከዚህ በታች ጥቂት የሆኑት አስገራሚ ጥቅሞቹ ተዘርዝረዋል፡፡
አንዳንድ ጥቅም ተብለው የተዘረዘሩት አከራካሪ ቢሆኑም በአመዛኙ ብዙ ጥናቶች የሚደግፏት እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡
1.ክብደት ለመቀነስ
አረንጓዴ ሻይ የሰዉነት ክብደትን እና የተከማቸ ስብን የማስወገድ አቅም አለው።
አረንጓዴ ሻይ ሜታቦሊዝምን ይጨምራል።
በአረንጓዴ ሻይ የሚገኘው ፖሊፌኖል የስብ ኦክሲዴሽንን የሚያጧጡፍ ስራ የሚሰራና ሰውነታችን ምግብን ወደ ካሎሪ የመቀየሩን ተግባር የሚያለሳልስ ነው።
2.ለስኳር
ምግብ ከተመገብን በኋላ በደማችን ውስጥ የሚጨምረውን የስኳር መጠን፣ አረንጓዴ ሻይ ፍጥነቱ እንዲገታ ለማድረግ ይረዳል።
ይህም የከፍተኛ ኢንሱሊን ጡዘትንና የስብ ክምችት ማስከተሉን የሚከላከል ነው።
ስለዚህ ቢያንስ የስኳር መጠንን ባለበት ለመቆጣጠር ይረዳል።
3.ለልብ በሽታ
ሳይንቲስቶች እንደሚያስቡት፣ አረንጓዴ ሻይ በደም ቧንቧ የላይኛው ገጻቸው ላይ ስራውን የሚሰራና፣ የደም ቧንቧዎች ፋታ እንዲያገኙና ለደም ግፊት ለውጦች የተሻለ መቋቋም እንዲኖራቸው ይረዳል።
እንዲሁም ደግሞ የደም መርጋትን ይከላከላል፣ የደም መርጋት የልብ ችግር ግንባር ቀደም ምክንያት ነው።
4.የጉሮሮ ካንሰር
በጉሮሮ ካንሰር የመያዝ አደጋን የሚቀንስ ነው፣ ግን በስፋት እንደሚታወቀው የካንሰር ሴሎችን መግደል የሚችል እና በዙሪያው በሚገኙት ጤነኛ የሆኑ ቲሹወች ላይ ጉዳት የማያደርስ ነው።
5.ኮሌስትሮል
አረንጓዴ ሻይ በደም ውስጥ ያለን መጥፎ ኮሌስትሮል የሚቀንስና የጥሩውን ኮሌስትሮል ከመጥፎው ኮሌስትሮል የተሻለ የሚያመዛዝን ነው።
6.አልዝሃሚር እና ፓርኪንሰን
በአልዝሃሚር እና በፓርኪንሰን የሚመጡትን ችግሮች የሚያዘገይ እንደሆነ ይነገራል።
በአይጥ ላይ የተሞከረ ጥናት እንደሚያሳየው አረንጓዴ ሻይ የአዕምሮ ሴሎችን ከመሞት የሚያድንና የተጎዱ የአዕምሮ ሴሎችን የሚጠግን ነው።
7.የጥርስ መበስበስ
ጥናቶች እንደሚያመልክቱት በሻይ የሚገኘው “ካቴቺን” የተባለው አንቲኦክሲደንት ኬሚካል የጉሮሮ መመርቀዝ፣ የጥርስ መበስበስ እና ሌሎች የጥርስ ችግሮችን የሚያስከትሉትን ባክቴሪያና ቫይረሶች የሚያወድም ነው።
8.የደም ግፊት
አረንጓዴ ሻይን አዘውትሮ መጠቀም የደም ግፊት አደጋን እንደሚቀንስ ይታመናል።
9.ድብርት
ቲያኒን በሻይ ቅጠሎች በተፈጥሮ የሚገኝ አሚኖ አሲድ ነውደ
ይህ ንጥረ ነገር የሚያዝናና እንዲሁም የሚያረጋጋ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን ለሻይ ጠጪወችም ላቅ ያለ ጥቅም ይሰጣል።
10.ፀረ-ቫይረስ እና ፀረ-ባክቴሪያል
የካቴቺን ሻይ ጠንካራ ፀረባክቴሪያል እና ፀረቫይረስ ባህርይ ያለው ሲሆን ከኢንፍሉየንዛ እስከ ካንሰር ያሉ በሽታወችን በማከም ውጤታማ ናቸው።
በአንዳንድ ጥናቶችም አረንጓዴ ሻይ የአብዛኞቹን የበሽታወች ስርጭት መግታት እንደሚችል ያመላክታል።
11.ለቆዳ ውበት
አረንጓዴ ሻይ የቆዳ መጨማደድንና የማርጀት ምልክትን ለመቀነስ የሚረዳ ነው፣ ለዚህ ምክንያትም ያላቸው ፀረ ኦክሲደንት እና ፀረመመረዝ ተግባር ነው።
በእንስሳ ሆነ በሰው ላይ የተደረጉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት አረንጓዴ ሻይ በጸሀይ የሚመጣ ጉዳትን የሚቀንስ ነው።
ምን ያህል?
እነዚህ ከብዙ ጥቅሞቹ ጥቂቶች ሲሆኑ እውነታው ግን በቀን ውስጥ አንድ ስኒ ሻይ የጠቀስናቸውን ጥቅሞች ያስገኛል ማለት አይደለም።
ምን ያህል ስኒ በሚለው ላይ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም፤ አንዳንዶች እስከ ሁለት ስኒ ይላሉ ሌሎች ደግሞ አምስት ሲኒ ይላሉ እንዲሁም ደግሞ ብዙወች በቀን ውስጥ እስከ አስር ስኒ መጠጣት ይቻላል ይላሉ።
ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ካፊን እንደሚገኝ ነው፡፡
ስለዚህም ለካፊን ስሜታችሁ ስስ ከሆነ አንድ ስኒ በቂያችሁ ነው።
አረንጓዴ ሻይ ታኒስ (የብረትን እና የፎሊክ አሲድን ውህደት የሚቀንስ) ይገኝበታል፣ ስለዚህም ነፍሰጡር ከሆንሽ ወይም ደግሞ ለማርገዝ እቅዱ ካለሽ አረንጓዴ ሻይ ለአንቺ አይሆንም።
አረንጓዴ ሻይን እንደ ዝንጅብልና ሌሎች ጤናማ ንጥረ ነገሮች ላይ ማዋሀድ ይቻላል ።

ለተሻለ ዕውቀት፣ችግር ፈቺ፣ ወጪ ቆጣቢ እና የተለያዩ መረጃዎችን ከዚህ በፊት ዩትብ ላይ ከለቀቅናቸው ቪድዪዎች ብዙ ነገር ማግኘት ትችላላችሁ።
በተጨማሪም ዩቲዩብ ቻናላችንን በመቀላቀል በምስል እና በቭድዮ የተዘጋጁ ከስራ እና ከቴክኖሎጂ ጋር ይተዋወቁ Subscribe በማድርግ ሌሎች መረጃዎች ይሸምቱ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

https://www.youtube.com/channel/UCpKx7Pd_viT9nnmheRu6o8Q
▬▬ Share ▬▬
ለተጨማሪ እውቀት እና ጠቃሚ የቴክኖሎጂ መረጃ ለማግኘት በዚ የቴሌግራም ቻናላችንን ከታች ባለዉን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይችላሉ።
here it is
https://t.me/Information_Science_Technology