Get Mystery Box with random crypto!

‍ ----------- ------------ ★ለፍቅር ፊዳ★ ----------- ----------- | ikhlas Tube

‍ ----------- ------------
★ለፍቅር ፊዳ★
----------- ------------

★ክፍል ሰላሳ አንድ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…"የኔ አይናፋር በይ አታስቁሚው ውጪ" አሏት የአባቷን ግንባር ስማ ቻው ብላው ወጣች መኪናውን ከፍቶ ሲያስገባት ንግስት የሆነች ያህል ተሰማት ጉዞ ወደ ቤቱ ጀመሩ ቤት ደርሰው ክላክስ እንዳሰማ በ40 ዎቹ እድሜ የሚገኝ ጎልማሳ በሩን ከፈተላቸው የግቢው ዘበኛ ነበር ልክ እንደገቡ ግቢያቸው በጣም ከሚባለው በላይ ቆንጆ ነበር በአረንጓዴ ነገር የተሞላ ከነገራት በላይ ውብ ሆኖ አገኘችው ከሱ መኪና ውጪ ሁለት ዘመናዊ መኪና ጊቢው ውስጥ ቆሟል የነሱ እንደሆነ እርግጥ ነው ከመኪናው እንደወረዱ ሀፍሲ ወደሱ ዙራ
"እንዴ ሰሚ ግቢያቹን እኮ እንደዚ አልነበረም ያልከኝ መናፈሻ አይደል እንዴ ሚመስለው"
"ከናንተ ባይበልጥም"
"ዝምበል ባክህ"
"በይ አሽቃባጬ እንግባ"ብሏት እሱ ከፊት እየመራ እሷ ከኀላ ሆና ወደ ሳሎኑ አቀኑ ልክ ሲገቡ ሱፍራ ላይ በሚያምር መልኩ ባይነት ባይነት ምግብ ቀርቦ የሰርግ መንዙማ ተከፍቶ የሰሚር እህትና ባሏ አንድ ላይ ቁጭብለው አንዲት ልጅ ደሞ ቤቱን በእጣን አፍናው ቡና እየቆላች ነበር የሰሚር እህት ልክ ስታያቸው ከተቀመጠችበት እየተነሳች
"አሰላሙ አለይኩም የኔ ቆንጆ"ብላ አቀፈቻት
"ወአለይኩም አሰላም"
"ወይኔ ሰሚሬ አላህ ሲወድህ እንደዚች ቆንጆ ልጅ ሰጠህ ታድለህ"
"አረ ዩሚ አታካብጂያ"
"ቲ ቦዘኔ የምን ማካበድ ነው የምሬን እኮ ነው"
"እሺ በቃ ትቀመጥበት ወረኛ የወሬ ሱስ አለብሻ"
ሁሉንም ሰላም ብላ ወደ ሱፍራው ቀረበች ምሳ ተመግበው ሀፍሲ ና ዩሚ አንድ ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ ዛሬ የተዋወቁ ሳይሆን ለአመት የተዋወቁ ነበር የሚመስሉት የዩሚ ባል ደሞ ሰሚርን ስለትዳር እያስረዳው ነው ሰሚር ገና ዩሚ ጋር ሲመጣ ለትዳር የፈለኳትን ልጅ ዛሬ አስተዋውቃቹሀለው ለምሳ ይዣት እመጣለው ስላላቸው ነበር እንዲ ቤቱን አስውበው የተቀበሏት ሀፍሲ ደሞ እንዲ እንዳላቸው ዩሚ ስትነግራት በድንጋጤ አፏ ተሳሰረ
"እንዴ ሀፍሲ ምን ሆነሻል ደነገጥሽ እኮ አቶጂውም ማለቴ ሀላልሽ እንዲሆን አትመኚውም"
"ኧረ እንደዛ አይደለም ደስ ብሎኝ ነው"
"ማለት?አልነገረሽም እንዴ "
"ኧረ ምንም ማቀው ነገር አልነበረም እኔ እኮ እንደ እህቱ ሚያየኝ መስሎኝ ነበር"
"እንዴ እና አንቺ እንደወንድምሽ ነው ምታይው"
"አይደለም" ብላ ፈገግ ብላ አንገቷን ደፋች
"እና ምንድነው ሀቢብቲ ንገሪኛ አደብቂኝ"
"እኔ እኮ ከመውደድም አልፌ ነው ማፈቅረው ማለት እኔ ለዚ ነገር ያስበኛል ብዬ አላሰብኩም"አይኖቿ እንባ አቀረሩ
"እንዴ እና የምን ማልቀስ ነው ውዴ ለዚ እኮ አይለቀስም"እንባዋን ጠርጋ ስታቅፋት ሰሚር አይቶ ከተቀመጠበት በፍራቻ ወደነሱ እየተጠጋ
"እንዴ ምን ብለሻት ነው ዩሚ"
"ኧረ ምንም አላልኳትም የደስታ ነው ምታለቅሰው"
"ሆ በይ ተነሺ እሺ እንሂድ ቤት እንዳታስገድዬኝ አሱር እየደረሰ ነው"
"እንዴ ቆይ እንጂ ትንሽ ትቆይ አንተ ምን ቤት ነህ ቦዘኔ"
"አይ ዩሚዬ ሌላ ምንሄድበት ቦታ ስላለ ባንቆይ ይሻላል"
"ከሆነ እሺ በቃ ሂዱ"ተሰናብተዋቸው ወደነ ማያ ቤት አቀኑ መኪና ውስጥ ስለ ህይወታቸው እያወሩ ማያ ቤት ደረሱ ወርደው በሩን ማንኳኳት ጀመሩ ማያ ውጪ ፀሀይ እየሞቀች ስለነበር ከፈተች ሀፍሲ አይታ ወደ ሰሚር ስታይ ያየችውን ማመን ከበዳት በእጇ አፏን ይዛ
"ሰ…ሰ…ሚ…ር"አለች…

★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents