Get Mystery Box with random crypto!

እስቲ ፈገግ በሉልኝ አንድ ሰው በሚስቱ ክፋት ተማረረና ለአንድ ሸህ ብሦቱን ተናገረ፡፡ እነ ሸህ | ikhlas Tube

እስቲ ፈገግ በሉልኝ

አንድ ሰው በሚስቱ ክፋት ተማረረና ለአንድ ሸህ ብሦቱን ተናገረ፡፡ እነ ሸህ “ምላሷን አልቻልኩም፣ አቆሰለችኝ፡፡” አላቸው፡፡
ሸሁም “እስቲ አትናገራት፤ መጥፎ ይሁን ጥሩ በምትሠራው ነገር ሁሉ  ዝም ብለህ አወድሳት፡፡” አሉት።
ሰውዬውም የሸሁን ምክር ተቀበለ፡፡ ወደ ተግባር ለመለወጥም ተዘጋጀ፡፡
አንድ ቀን ሚስቱ እራት አመጣችለት፡፡ አስቀምጣለትም ዘወር አለች፤ እንዳትርቅበት እየተጣደፈ ገና አንድ እንደጎረሰላት
“ዉይ ዉዴ የዛሬው ምግብሽ ሲጣፍጥ እኮ!” አላት፡፡
እሷም “አልቀረብህም፤ እንደው እኮ ትገርማለህ! ስንት ዓመት ሙሉ መርዝ የበላህ የኖርክ መሰለህ፤? እኔ የሠራሁትን ምግብ አንድም ቀን ሳታሞግስና ሳታደንቅ ዛሬ ጎረቤታችን ያመጣችዉን ምግብ የምታደንቀው?፡፡
ለካስ የቀረበለት ምግብ ከጎረቤት የመጣ በሀዲያ መልክ የመጣ መሆኑን አላወቀም ነበር ሚስኪን ባል ወይ ኪሳራ።
.
.    #Ⓔ︎Ⓛ︎Ⓤ︎ነኝ

ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ
  @ikhlasstudents
  @ikhlasstudents