Get Mystery Box with random crypto!

‍ ----------- ----------- ★ ለፍቅር ፊዳ ★ ----------- ----------- | ikhlas Tube

‍ ----------- -----------
★ ለፍቅር ፊዳ ★
----------- -----------

★ክፍል ሰላሳ★

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…"እና የኛዋን ማያ ታቃት ነበራ ታዲያ"
"አው ትናንት እኮ ስልሽ ይሆናል ብለሽኝ ሄድሽ እኮ" ለካ ትናንት ሀሳቧ ስላልነበር ያለውን አላስተዋለችም አሁን ነው ትዝ ያላት
"አሀ ደስ ሲል እሺ ቀጥል"
"ከዛ እኔ እየወደድኳት ስሄድ እሷ እየናቀችኝ መጣች"
"ለምንድነው ምትንቅህ?"
" እኔ ከጓደኞቼ በተለየ ዝምተኛ ነበርኩ እሷ ደሞ የሆነ ጊዜ ላዋራት ስል ዝምተኛ ቀርፋፋ ወንድ አይመቸኝም ብላ ነበር ለዚ ለሷ ስል ግዴታ ተጫዋች ሳቂታ ሁሌ ደስተኛ ሴቶችን ማተራምስ ሰው መሆን አለብኝ ግን ኬት ይምጣ ራስን ለመቀየር መሞከር ራሱ አንድ የህይወት ፈተና ያክል ከባድ ነበር ግን እነደምንም ራሴን አደፋፍሬ ለመለወጥ ተነሳው ሁልጊዜ ጓደኞቼ በሚያወሩት ወሬ አጭር መልስ ነበር ምሰጣቸው አሁን ግን በሚያወሩት ነገር ረጅም አስተያየት ሰጣቸዋለው ከነሱ ገር መላፋት መጨቃጨቅ ለቀልድ መደባደብ አዲስ ባመጣሁት በሀሪ እነሱ ሁላ ተገርመዋል ብቻ እሷ ምትፈልገውን አይነት ወንድ ከመቶ በዘጠና አምስት ፐርሰት ተሳካልኝ እሷን እንደወደድኳት ጓደኞቼ እንኳን አያቁም ታዲያ አንድ ቀን ካሊድ ጠርጥሮኝ ወደሀታል ብሎ ጠየቀኝ እኔም እውነቱን ሁሉ ነገርኩት ከዛ እንዲህ አለኝ ይሀውልህ ሳሚ ለሴት ልጅ እራስህ ዝቅ ካረክ ትንቅሀለች ለሷ ብለህ እራስህን እነደቀየርክ አቃለው ግን ሁላችንም የኛ ጀማ ሁሉ በሴት ምክኒያት ነው ላይፉ የተቀየረው ድሮ ደስተኛ ከሆንክ ፍቅር እንድትቀየረ ሀዘንተኛ እንድትሆንም በቃ ላይፍህን ጠቅላላ በራስህ መንገድ እንዳትሄድ ታረግሀለች ሴት ስትባል አስመሳይ ፍጡር ናት ነው ምለው እኔ ወንድ እውነተኛ አፍቃሪ ነው ሴት ግን አስመሳይ አፍቃሪ ናት ብሎ መከረኝ ታቂያለሽ በዛ ሰአት የተሰማኝ ሴት ሁሉ አንድ ናት ሁላቸውም ለፍቅር ደደብ የሆኑ ጨካኝ ፍጡር ናቸው በቃ እውነትም አስመሳይ ፍጡር ብዬ ራሴን አሳምኜ ምክሩን አምኜ ተቀበልኩ ግን ምንም ቢሆን እሷን እንድጠላት መንገድ አልከፈተልኝም ታዲያ አንድ ቀን በመቀየሬ ከኔ ጋር እያወራች የባጥ የቆጡን እያወራች ትውላለች አንዳንድ ቀን ደሞ ከሌላ ወንድ ጋር ትውላለች ከሌላ ሰው ጋር ሳያት ከመከፋት አልፎ ወንድነቴን ሁላ አጣወለው አፍቃሪ ሆነሽ ስሜቱን ብትረጂው ደስ ይለኛል"
"አቃለው ይከብዳል አይዞህ"
"በምን አወቅሽ አፍቅሬ አላቅም አላልሽ"
"ባላፈቅር ሰውን አልረዳም አሁን ወሬህን ትተህ ቀጥል"
"ከዛ ቀን በቀን እየተደጋገመ ሲመጣ መቅናቱ እየሰለችኝ ተስፋ እየቆረጥኩ ለሴት ያለኝን ጥላቻ እየጨመረችብኝ መጣች እንዲም ሆና መቼም አልጠላትም አንድ ቀን ወደ ቤት እየሄድን ማያ ካሊድን ፍለጋ ስትመጣ እሷም አብራት መጣ ነበር እና ከኔ ጋር እያወራን በመሀል
"አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ"አልኳት
"ይቻላል ሰሚ"
"ፍቅር ፈቅደሽ ምታመጪው ነገር አይደለማ ከፈጣሪ የሚመጣ በራስሽ ማትወስኚው ማይጨበጥ ስሜት ነዋ እኔም ላንቺ ያ ስሜት ተፈጥሮብኛል አፍቅሬሻለው ትቀበይኛለሽ"
"ይቅራት ሰሚ ይሄ ነገርህ ገብቶኝ ነበር እኔ ግን ሌላ ምወደው ሰው አለኝ አንተን አልፈልግህም ካንተ በተሻለ ለኔ ሚሆነኝ እሱ ነው ገባህ አለቀ ደና ሁን ብላኝ ሄደች ሀፍሲ በምን ላስረዳሽ ቅስሜ ስብርብሩን ነው ያወጣችልኝ ኡፍ…

★ይቀጥላል★…

ከወደዱት ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!!

Join and share
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents