Get Mystery Box with random crypto!

በዶክተር/ዘማሪ ለዓለም ጥላሁን ተጻፈ! 'በጉባኤ አምልኮ ሰዓት' 1,ትኩረት ወደራስህ አትሳብ! የ | Vocal Clinic🎷🎺🎸🎹🎻📡🔭

በዶክተር/ዘማሪ ለዓለም ጥላሁን ተጻፈ!

"በጉባኤ አምልኮ ሰዓት"
1,ትኩረት ወደራስህ አትሳብ! የትኩረት ሁሉ ማዕከል ተመላኪው እግዚአብሔር ነውና!!

2,ልብህን ለማፍሰስ እንጂ ስለውጫዊው እንቅስቃሴ እምብዛም አትጨነቅ። የተሰበረ ልብና የተዋረደ መንፈስ መለኮትን የሚስብ ብርቱ ማግኔት ነውና!!

3,በመንፈስ ለመነዳት ራስህን ስጥ። በመንፈስ እየነጎድክ ስሜትህን ንዳው እንጂ ስሜትህ እንዲነዳህ አትፍቀድለት።

4,ነጻነትህ እስከመፋነን እንዳያደርስህ ተጠንቀቅ!! በመንፈስ ጀምረህ በስጋህ እንዳትጨርስ ለስጋህ አርነት አትስጥ!!

5,በአዘቦቱ ቀን ያልሆንከውን አዲስ ማንነት ድንገት በጉባኤ ሰዓት ይዘህ ብቅ አትበል!! be real, be genuine... በአንተ ማንነት ራሱን መግለጥ ጌታ ይቻለዋልና።

6,የቀጠሮ አምላኪ አትሁን!....በጉባኤው አምልኮ ያገኘኸውን የባርኮት አቅም በቤትህም ሆነ በዕለታዊ ስምሪትህ ለማስቀጠል ራስህን አስለምድ።

ጌታ ሆይ ትውልዴንና እኔን ትረዳናለህ።
ዶ/ር ለዓለም ጥላሁን