Get Mystery Box with random crypto!

የአምልኮ መሪዎች ።።።።።።።።።።።።።የአምልኮ መሪዎች ።።።።።።።።።።።።። ➊ አምልኮ መሪዎች | Vocal Clinic🎷🎺🎸🎹🎻📡🔭

የአምልኮ መሪዎች
።።።።።።።።።።።።።የአምልኮ መሪዎች
።።።።።።።።።።።።።
➊ አምልኮ መሪዎች በትህትና የሚመሩ ናቸው። በመድረክ የቆሙት የህዝቡን አድናቆት እና ጭብጨባ ለመሰብሰብ አይደለም። ይልቁን ከህዝቡ ጋር ተገናኝተው በሙዚቃቸዉ ከጌታ ጋር መገናኘት እና ማገናኘት ዋና ትኩረታቸው ነው።
➋ አምልኮ መሪዎች ሙዚቃን ያጠናሉ ያቀናጃሉ ይፀልያሉ መዝሙሮችን በጥንቃቄ ይመርጣሉ ፣ለህዝቡ በሚመች ሁኔታ ያቀናጃሉ ፣መዝሙሮችን በቃል እስከሚይዙ ድረስ ያጠናሉ።
➌ አምልኮ መሪዎች መዋቅር እና መልክ አላቸው። አጀማመር ፣አካሄድ እና አጨራረስ በሚገባ አስበው ሰርተው ያዘጋጃሉ።ተመሳሳይነትና አሰልቺነት የሌለው ጣፋጭ የአምልኮ ጊዜ ወይም የመፍጠር አቅም አላቸው። ሁሉ ሰው በተሰጠው ፀጋ ያገልግል የሚል መደምደሚያ ሰጥቼ ልለፍ ሁሉም ለአካሉ መታነፅ ጠቃሚ ነውና።
ሮማን ታምሬ