Get Mystery Box with random crypto!

'ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ' ~ የልጅ አእምሮ ነጭ ወረቀት ማለት ነው። እኛ ዋዛ የሚ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

"ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ"
~
የልጅ አእምሮ ነጭ ወረቀት ማለት ነው። እኛ ዋዛ የሚመስሉንን ብዙ ነገሮች እንደ ቁምነገር ይይዛል። በልጅነቱ የሰው ጅብ ወይም ጭራቅ የሚባል አለ ብለው ስለነገሩት ካደገ በኋላም እንዲህ የሚባል ነገር አለ ብሎ የሚያምን ብዙ ሰው አለ። በርግጥ ከእድገት ጋር የሚቀየሩ ነገሮች አሉ። ቢሆንም ኋላ ተቀየረም አልተቀየረም ለህፃናት ያልሆነ ነገር እየነገርን አእምሯቸው ውስጥ የተዛባ ነገር እንዳንተክል መጠንቀቅ ይገባል። ከዚህ ጋር የተያያዙ እንደየሃገሩ እንደየባህሉ ብዙ ልማዶች አሉ። ለምሳሌ፦
* ህፃናት ሲጫወቱ "ጨረቃ ዳቦ ጣይልኝ፣ ኮከቢት ተቀበይልኝ" እያሉ መዘመር። ይሄ ሺርክ ነው።
* ጥርሳቸውን ሲጥቅሉ "አይጢቷ! የኔን ወስደሽ ያንቺን ስጪኝ" ብሎ ጣራ ላይ መጣል። ይህም ሺርክ ነው።
* ጆሮ ደግፍ ሲያዛቸው የሰው ቤት በድንጋይ እንዲመቱ መላክ። በዚህም ውስጥ ትንሹ ሺርክ አለ።
* የቀብር አፈር ቤት ላይ መበተን። ልጆች ውጭ ላይ አጥፍተው ሲመጡ ቤተሰብ እንዳይቀጣቸው ሲፈሩ የቀብር አፈር ይዘው በመምጣት ቤት ላይ ይበትናሉ። በቃ ይህን ሲያደርጉ ቤተሰብ ስለዚያ ጉዳይ አይጠይቅም ብለው ያምናሉ። በዚህም ውስጥ ሺርክ አለ።
መስጠት የፈለግኩት ጥቆማ ነው። እነዚህና መሰል ባህሎች ዛሬ ከተማ ውስጥ በብዛት አይኖሩም። ግን አንዳንዴ የማንጠብቀው ነገር ይዘው እናገኛቸዋለን። ስለዚህ ልጆቻችንን በጨዋታም ይሁን በቁም ነገር፣ በእምነትም ይሁን በልማድ መልክ የተዛባ ነገር እንዳይዙ መጠንቀቅ መልካም ነው። አንዳንዱ በጨዋታ መልክ የሚቀርብ ቢሆንም በሺርክ መቀለድ በእሳት መጫወት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor