Get Mystery Box with random crypto!

ከፍ በል በኢስላም! ~ አለባበሳችንን፣ አነጋገራችንን፣ የፀጉር ቁርጣችንን፣ የሜካፕ አጠቃቀም፣ የል | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ከፍ በል በኢስላም!
~
አለባበሳችንን፣ አነጋገራችንን፣ የፀጉር ቁርጣችንን፣ የሜካፕ አጠቃቀም፣ የልብስ ምርጫችንን፣ ... ለመወሰን በወቅታዊ ፋሽን መሸነፍ አይገባም። ሸሪዐው ሲያዝ አሻፈረኝ ብለን የዘመኑ ፋሽን ሲሆን የምንንበረከክ ልፍስፍሶች መሆን የለብንም። እኛ በኢስላማዊ እሴቶቻችን ፈፅሞ የማንሸማቀቅ ኩሩዎች እንጂ የተሸነፈ ስነ ልቦና የያዙ ደካሞች ልንሆን አይገባም። ደግሞም ለራሳችንም ዋጋ መስጠት መልካም ነው። አላህ በኢስላም ካከበረን በኋላ፣ 0ቅልን ያክል ኒዕማ ከሰጠን በኋላ ከሰውነት ወለል ወርደን የልብስ መስቀያ፣ የፋሽን ማሳያ አሻንጉሊት ልንሆን አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor