2022-07-25 07:28:36
ክፍል አንድአል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን
የተሰኘው ጠማማ አንጃ!!!
▬▭▬▭▬▭▬▭▭▬
ከአንጊሊዛዊው ሸይኸ
አቡ ኸዲጃህ ዐብዱል ዋሒድ
(ሀፊዘሁሏህ)ጽሁፍ
አል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን በሐሰን አል-በና በ1928 CE ተመሠረተ። አላማውም ስልጣን ለመቆናጠጥ እና አመራር ለማግኘት ነበር። አዳዲስ የፈበረኳቸው ቃዒዳዎችን (መርሆዎችን) ይጠቀማሉ። አካሄዳቸው ከመንሐጀ ሰለፍ የሚጣረስ ነው። የግድያ፣ የአመፅ፣ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ፣ ሽብርተኝነት፣ ማህበራዊ አለመረጋጋት እና ዲሞክራሲን ይጠቀማሉ። ይህ ሁሉ ልፋት የፖለቲካዊ አላማ ነው።
ታላቁ ሊቅ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁሏህ) ይህ ቡድን ከጀማአት አት-ተብሊግ ጎን ለጎን ከ72ቱ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።
ሱሩሪዮች
የሙሐመድ ሱሩር ዘይን አል-ዓቢዲን የፖለቲካ አስተምህሮ ተከታዮች ናቸው። ጽንፈኛ በሆነው አመለካከቱ የተነሳ ከሳዑዲ አረቢያ የተባረረው የአል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን የቀድሞ የሶሪያ አባል ወደ ኩዌት ከዚያም በርሚንግሃም (England) ዩኬ ሄዶ ዳር አል-አርቀምን መሰረተ፣ በመቀጠል ለንደን አል-ሙንታዳ አል-ኢስላሚ የሚባለውን ተቋም አቋቋመ። በዓለም ዙሪያ ከአቡ ሙስዓብ ዘራቃዊ፣ ከአቡ ሙሐመድ አል-መቅዲሲ እስከ ሰፈር አል-ሃዋሊ እና ሰልማን አል-አውዳህ ድረስ በከዋሪጅ ጽንፈኞች የተወደዱ ነበሩ።
የተከበሩ ታላላቅ መሸይኾችና ዐለማዎችን እና የሳውዲ ባለስልጣናትን በተክፊርነት እስከ መፈረጅ የደረሠ ሰው ነው። በተጨማሪም፣ ዑለማዎችን የምዕራባውያን አሻንጉሊት ብሎ ተችቷል።
ቁጥቢዮች
ቁጥቢዮች ደግሞ የአል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን አስተምሮት የተፈለፈሉ ናቸው። መሪያቸው ደግሞ ሰይድ ቁጥብ ይባላል። #የናስርን መንግስት ለመጣል ባደረገው ሙከራ በመጨረሻ በ1966 የተገደለው ግብፃዊው የፖለቲካ አክቲቪስት ነው። እሱ ምናልባት በዓለም ላይ ካሉት “ ጽንፍ የረገጡ ” ቡድኖች ሁሉ በጣም ተደማጭነት ያለውና አፈቀላጤ፤ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ነበር።
የእሱ መጽሐፎች በገፍ የሚቆጠሩ ቋንቋዎች ታትመዋል። በሰፊውም ተሰራጭተዋል።
ሰይድ ቁጥብ ኡማውን “ጃሂሊያህ” (ቅድመ-እስልምና ድንቁርና) ውስጥ እንዳለች አድርጎ ይቆጥር ነበር።
ጀማሉዲን አል-አፍጋኒ
(እ.ኤ.አ. በ1897 የሞተ)፦ አመጣጡ በምስጢር የተሸፈነ ነው ነገር ግን ከሺዓ ቤተሰብ የመጣ ነው፣ እና ይህ ኢራንን ደጋግሞ መጎብኘቱን እና በመረጃ የተደገፈ ነው። የሺዓን አምልኮ ስፍራዎችን በመጎብኘት እና በኢራን ያደረገው የፖለቲካ ማሻሻያ ጥረት ማሳያ ነው።
በጉርምስና ዕድሜው ለሙስሊሞች የፖለቲካ ስልጣንን ለማግኘት የእስልምና ልዩነቶች ወደ አንድ ጎን እንዲቆሙ የሚጠይቅ የፖለቲካ አራማጅ ነበር። እስላማዊ እምነትን ከዘመናዊው የምዕራባውያን እና የአውሮፓ እሴቶች እንደ ብሔርተኝነት፣ ዴሞክራሲ፣ መገለጥ እና ምክንያታዊነት ጋር ለማስታረቅ የሚሞክር የእስልምናን አስተሳሰብ “ዘመናዊነት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
በመሠረቱ ከሌሎች ሃይማኖቶች፣ ርዕዮተ ዓለሞች እና አስተሳሰቦች መበደር ጥቅሙን ያዩ ምክንያታዊ አዋቂ ነበሩ። ለፖለቲካ ዕርገት መንገድ። “ሰለፊያህ” የሚለው ቃል ብዙውን ጊዜ የጀማል አድ-ዲን አል-አፍጋኒን እና የተማሪውን መሐመድ አብዱህ ርዕዮተ ዓለምን ለማመልከት በስህተት ይገለገላል፣ እውነቱ ግን ሁለቱም የዘመናዊ አስተሳሰብ አራማጆች ከሰለፊዝም ይልቅ ከሙዕታዚላ አስተምህሮ ጋር ተመሳሳይ መሆናቸው ነው። ሰለፊዝም በሃይማኖት ውስጥ ፈጠራን አይቀበልም እና ከነብዩ እና ሰሃቦች አካሄድ ማፈንገጥን አይቀበልም በሁሉም የህይወት ዘርፍ የፖለቲካውን መድረክ ጨምሮ። አል-አፍጋኒ እና ተከታዮቹ ከኢስላም ውጭ የሆኑ ባዕድ አስተሳሰቦችን ይቀበላሉ።
አል-አፍጋኒ፣ ሙሐመድ አብዱ እና ራሺድ ሪዳ፣ የኢጅቲሃድ በሮች እንዲከፈቱ ጥሪ ቃቀረቡት ዋነኞቹ ናቸው።
ይቀጥላል...
ሸይኽ አቡ ኸዲጃህ (ሀፊዘሁሏህ)
ሼር ጆይን
@IBNUMOHAMMEDABUASIYA
@IBNUMOHAMMEDABUASIYA
@IBNUMOHAMMEDABUASIYA
70 views04:28