Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ሰኔ ፳፩ #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው #ሰኔ_20_እና_ | ወልድ ዋሕድ

​​​​ሰኔ ፳፩ #የእመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው

#ሰኔ_20_እና_21

#ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ #ሕንጸተ_ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ #ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ነው፤
ቦታው #ፊልጰስዩስ ነው፤ #ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ #በእመቤታችን ስም ነው።

#ጴጥሮስ፤ #ዮሐንስ #በርናባስና ሌሎችም #ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ #በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ #መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል #እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን #እመቤታችንን እና #ቅዱሳን_መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ #ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ #ሐዋርያት #ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው #ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

#የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ #እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

.......የተወደደችው ጊዜ አሁን ፤ የመዳን ቀን አሁን ነው።
1ኛ ቆሮ 6÷2

ወ ስ ብ ሐ ት ለ እ ግ ዚ አ ብ ሔ ር
ወ ወ ላ ዲ ቱ ድ ን ግ ል
ወ ለ መ ስ ቀ ሉ ክቡር