Get Mystery Box with random crypto!

ቀመሩል አምቢያ ያለሙ ጠሃይ ከዱንያ ህይወት ጋር ጀሰዱ ቢለይ   ሃዘን አድርቶበት ከታችም ከላይ | ሑስኒ-ሱልጣን = Husni sultan 🇪🇹

ቀመሩል አምቢያ ያለሙ ጠሃይ
ከዱንያ ህይወት ጋር ጀሰዱ ቢለይ
  ሃዘን አድርቶበት ከታችም ከላይ
ዟሂር አለቀሱ መሬትም ሰማይ
።።።።።።

ቀን ተስለመለመ ሃዋኡም ንፋሱ
ከዋክብቶች በቀን ሰማይ ላይ ፈሰሱ
የተደፋው ሃዘን ሁሉን ስለናጠ
  የወትሮ ሃለቱን የለም ያልለወጠ
።።።።።

  የሙስጦፋን መሞት በግር ተከትላ
መዲና ጨለመች ያ ብርሃኗም ላላ
   እንዴትስ ላትታይ ጉዱን አልችል ብላ
ባንቱ አይደል መድመቋ ሙነወራ ተብላ
።።።።።

ድንገት ያላሰቡት ጉድ ተደፍቶባቸው
ሶሃቦች በጅጉ ተለየ ሃላቸው
ሃዘንተኞች ሆኑ ደስታ ማያውቃቸው
በሽተኞች ሆኑም ሃኪም የሌላቸው
።።።።።
 
እኩሉ ያለቅሳል እስከ ጭላጭ እምባው
ከፊሉ ዋለለ ጠፍቶት መውጫ መግቢያው
ኸበሩ ሲደርሰው አቅሉን ሳተ ስንቱ
  ሌላው ተከንችሮ ቀረ እንደ ሃውልቱ
።።።።።

ዓሊይ ተባባሱ ኡስማንም ጠናቸው
  ጅስምን መቆጣጠር አልሆን እስኪላቸው 
  አዎን ያንን መሳይ መርዶስ ከመስማቱ
ልጅ ወላጅ ንብረትን ይቀላል ማጣቱ
።።።።።።።

ባለ ሃይባው ጀግና ዑመሩል ፋሩቁ
   እሱስ ይታገሳል ተብለው ሲጠበቁ
የተከሰተውን ማመን ስላልቻሉ
አልሞቱም ነብዬ ሞተ አትበሉኝ አሉ
።።።።።

ከዚህ ብሰው አልፈው ግለው ተወዝውዘው
  በቁጣ እንዲህ አሉ ሰይፋቸውን መዘው
    አልሞቱም ሃቢቢ ይነቃሉ ደርሰው
ሰይፌ ያርፍበታል ሞቱ የሚለኝ ሰው
።።።።
 
የሙላው መደሺያ የሙላው ክብረቱ
  ህመም ጠንቶባቸው ሰኞ ለት ቢሞቱ
ሰበብ ናቸውና ለመላው ፍጥረቱ
   የተቻለው ታጣ ሙስጦፋን ማጣቱ
።።።።።።