🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

ጥንቃቄና ጸሎት! እናት ልጇን ሁል ጊዜ እንዲህ ስትል ትመክረው ነበር፡- “ጀርም፣ ባክቴሪያና ቫ | ሁለንተናዊ ስኬት

ጥንቃቄና ጸሎት!


እናት ልጇን ሁል ጊዜ እንዲህ ስትል ትመክረው ነበር፡- “ጀርም፣ ባክቴሪያና ቫይረስ እንዳያገኝህ እጅህን ቶሎ ቶሎ ታጠብ፤ ከሰዎች ጋር ስትነጋገር ደግሞ በጣም አትቅረብ፣ ሰዎች ሲስሉ ወይም ሲያስነጥሱ በቶሎ ዘወር በል፣ ክፉ እንዳያገኝህ ደግሞ ሁል ጊዜ ወደፈጣሪህ ጩህ፡፡”


ልጁ ግን፣ “ጀርም፣ ባክቴሪያና ቫይረስ ስለሚባሉት ፈጽሞ በአይኔ አይቼያቸው ስለማላውቃቸው ነገሮች መስማት ሰለቸኝ፡፡

ፈጣሪ የምትይውንም ነገር ቢሆን እስካሁን በአይኔ አይቼው አላውቅምና አትነዝንዢኝ” እያለ አይሰማትም ነበር፡፡

አንድ ቀን በጀርም ይሁን በባክቴሪያ፣ ወይም በቫይረስ በማይታወቅ ሁኔታ ታመመና ስለጠናበት ሃኪም ጋር ሄዶም ሊድን አልቻለም፡፡


በመጨረሻ ተስፋ ሲቆርጥ እናቱን ጠራና፣ “ከዚህ በአይን ከማይታይ ጀርም፣ ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ እንዲያድነኝ በአይን የማይታየውን ፈጣሪን ለምኚልኝ” አላት ይባላል፡፡


ሁለት ምክሮች


1. በግድ የለሽነትና በምርጫችን ራሳችንን አጋልጠን በሰጠንበት ሁኔታ ምክንያት ለሚደርስብን ነገር ፈጣሪን ማማረር እናቁምና ተገቢውን ጥንቃቄ እንድርግ፡፡

2. ምንም ብንጠነቀቅ ከቁጥጥራችን ውጪ ስለሆኑ ነገሮች ከመጨነቅ ይልቅ ለፈጣሪ እንስጠውና ልባችንን እናሳርፍ


መልካም ቀን!


#DR EYOB MAMO

@hulentenawisket