🏡 The complete catalog of thousands of rent-to-own properties in USA Get Mystery Box with random crypto!

ሁለንተናዊ ስኬት

የቴሌግራም ቻናል አርማ hulentenawisket — ሁለንተናዊ ስኬት
የቴሌግራም ቻናል አርማ hulentenawisket — ሁለንተናዊ ስኬት
የሰርጥ አድራሻ: @hulentenawisket
ምድቦች: መጠነሰፊ የቤት ግንባታ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.98K
የሰርጥ መግለጫ

🇪🇹አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
🌐 በቻናላችን
➢ ስለ ስኬት ምንጮች እና መንገዶች
➢ አስተማሪ ታሪኮች እና ወጎች
➢ ወቅታዊ ጉዳዮች
➢ የታዋቂ ሰዎች አባባል
➢ አነቃቂ መልዕክቶች
➢ የተለያዩ ገፆችና መጣጥፎች
➢ አጓጊ ሽልማት ያላቸው ውድድሮች
ይቀላቀሉን
https://t.me/joinchat/AAAAAEvpYIGhf7233N6veA
ለማንኛውም አስተያየት @ethiomerja_bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-02 13:25:18
እንኳን ለ127ኛው ለታሪካዊ ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ነፃነት በር ለሆነው የጥቁር ህዝቦች ኩራት የአድዋ ድል በአል በሰላም አደረሰን

@hulentenawisket
89 viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 19:52:19 የምታቀው የውሃ ኩሬ ራቅ ብለህ ስትመለስ ደፍርሶ ቢጠብቅህ...ንጹህ ውሃን ለመጠጣት ያለህ አማራጭ ድፍርሱ እስከሚጠራ መጠበቅ ብቻ ይሆናል ። "አፈር የተቀላቀለበትን ውሃ እንዲጠራ ከፈለግክ፤ተወው አታማስለው" ይላል ፈላስፋው አለን ዋትስ። በመተው፤በመረጋጋት፤ በዝምታ፤ ለፍተን ያጣናቸውን ውድ የህይወት ስጦታዎች እናገኛለን።

ልክ እንደዚህ ሁሉ በህይወታችን የሚገጥሙንን ችግርና እንቅፋቶችን አንዳንዴ የምናጠራቸው መሃል ላይ እጃችንን ስለከተትን ብቻ ላይሆን ይችላል ። አንዳንዴ ዝምታችን እና ትእግስታችንም ብዙ ነገሮች በራሳቸው ጊዜና ሁኔታ እንዲስተካከሉልን እድል ይሰጡልናል ። እኛ ችግራችንን ለመፍታት የምናደርገው ጥረት ይበልጥ ችግር ውስጥ እንዳይዘፍቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል ። አለዝያ የችግሩ አሳዳጊ እና አባባሽ እንጂ የችግሩ ፈቺ አንሆንም ።

ለተረጋጋ አይምሮ አለም ትገበራለች ብሏል ጥንታዊው ፈላስፋ። ምንም እንኳን ብዙ ነገሮች በጥረትና በሩጫ የሚገኙ ቢሆንም፤ አንዳንድ ወሳኝ ነገሮች ግን በእርጋትና በመተው እንዲሁም በዝምታ የሚገኙ ናቸው።

             ውብ  ምሽት

#EthioHumanity
60 views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 08:49:05
እውነትን ፣ቅንነትን ፣ ገንዘብ ከማድረግ በላይ ኮተትን ብቻ  ገንዘብ አድርጎ ህይወቱን በክህደት፣ በውሸት ፣በጥቅመኝነት ፣በአስመሳይነት በብልጣብልጥነት እየኖረ ኑሮ የበራለት የሚመስለው ሰውነት እንዴት ያልታደለ ነው።

የህሊና ፣ የቤተሰብ ሰላምና ደስታ በብልጣብልጥነት አይመጣም። ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣የቆምን መስሎን የዘነጋን…. ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው፣ ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ሁሉ ራስህንም ያጠፍል፤ ሀሳብህን አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

መጥፎ ነገራችንን ሁሉ በመልካም ይቀየርልን

                               ሄለን ካሳ

            ውብ  ቀዳሚት

#EthioHumanity
18 views05:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 06:24:58 ጥንቃቄና ጸሎት!


እናት ልጇን ሁል ጊዜ እንዲህ ስትል ትመክረው ነበር፡- “ጀርም፣ ባክቴሪያና ቫይረስ እንዳያገኝህ እጅህን ቶሎ ቶሎ ታጠብ፤ ከሰዎች ጋር ስትነጋገር ደግሞ በጣም አትቅረብ፣ ሰዎች ሲስሉ ወይም ሲያስነጥሱ በቶሎ ዘወር በል፣ ክፉ እንዳያገኝህ ደግሞ ሁል ጊዜ ወደፈጣሪህ ጩህ፡፡”


ልጁ ግን፣ “ጀርም፣ ባክቴሪያና ቫይረስ ስለሚባሉት ፈጽሞ በአይኔ አይቼያቸው ስለማላውቃቸው ነገሮች መስማት ሰለቸኝ፡፡

ፈጣሪ የምትይውንም ነገር ቢሆን እስካሁን በአይኔ አይቼው አላውቅምና አትነዝንዢኝ” እያለ አይሰማትም ነበር፡፡

አንድ ቀን በጀርም ይሁን በባክቴሪያ፣ ወይም በቫይረስ በማይታወቅ ሁኔታ ታመመና ስለጠናበት ሃኪም ጋር ሄዶም ሊድን አልቻለም፡፡


በመጨረሻ ተስፋ ሲቆርጥ እናቱን ጠራና፣ “ከዚህ በአይን ከማይታይ ጀርም፣ ባክቴሪያ ወይም ቫይረስ እንዲያድነኝ በአይን የማይታየውን ፈጣሪን ለምኚልኝ” አላት ይባላል፡፡


ሁለት ምክሮች


1. በግድ የለሽነትና በምርጫችን ራሳችንን አጋልጠን በሰጠንበት ሁኔታ ምክንያት ለሚደርስብን ነገር ፈጣሪን ማማረር እናቁምና ተገቢውን ጥንቃቄ እንድርግ፡፡

2. ምንም ብንጠነቀቅ ከቁጥጥራችን ውጪ ስለሆኑ ነገሮች ከመጨነቅ ይልቅ ለፈጣሪ እንስጠውና ልባችንን እናሳርፍ


መልካም ቀን!


#DR EYOB MAMO

@hulentenawisket
252 views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 10:26:59 መዝራትና ማጨድ

“እያንዳንዱ ቀንህን መመዘን ያለብህ በሰበሰብከው ፍሬ ሳይሆን በዘራኸውና በተከልከው ዘር ነው” - Robert Louis Stevenson

ሁሉም ነገር የሚፈጠረው ሁለት ጊዜ ነው፣ በመጀመሪያ በሃሳብ መልክ፣ ከዚያም በገሃዱ ዓለም፡፡ ዛሬ በሃሳብ፣ በንግግርም ሆነ በተግባር የሚዘራው ዘር የነገውን እውነታ እንደሚፈጥርበት የማያስተውል ግለሰብም ሆነ ሕብረተሰብ ጥበብ እንደጎደለው ማሰብ አያስቸግርም፡፡ ይህንን የመዝራትና የማጨድ ሕግ ያልተገነዘበና ስርአት የሌለው ሕብረተሰብ በውጤቱ ለአመለካከቱና ለራሱ የሚገባውንና የሚመጥነውን አለም ይፈጥራል፡፡

የምትኖርበት ሕብረተሰብ ያለበትን የወቅቱን ሁኔታ ተመልከት፡፡ ይህ ሕብረተሰብህ ያንን ሁኔታ ማንም አልፈጠረበትም፤ ቢፈጥርበትም ያንን ተቀብሎ የመኖርን ደካማነት ማንም አላስታቀፈውም፡፡ ይህ ሕብረተሰብ ትናንት የዘራውን ዘር ፍሬ ዛሬ እየበላ ነው፡፡ ይህ እውነታ ደግሞ በዙሪያችንም ሆነ በግል ሕይወታችን የምናያቸውን መልካምም ሆነ ክፉ ሁኔታዎች የሚወክል የማይለወጥ እውነታ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ ማሕበረሰብ የምንኖርበትን ዓለም የምንፈጥረው እኛው ራሳችን ነን፡፡    

አንድ ሕብረተሰብ ከጥበብ ጎዳና ሲርቅ፣ ትናንት ያቆሸሸው አካባቢ ዛሬ በስብሶ ነገ በሽታን እንደሚሰጠው ማሰብ ያቅተዋል፡፡ ይህ አይነቱ ህብረተሰብ ባለበት ሲርመሰመስና የራሱን ቁስል በራሱ ምርጫና ውሳኔ ሲፈጥር አመታትን ያሳልፋል፡፡ ዛሬ በራስ ወዳድነት፣ በእኔ እበልጣለሁ ስሜትና በስግብግብነት የጎዳው የሕብረተሰብ ክፍል ነገ መልሶ ያንኑ ዛሬ እርሱ የዘራውን ዘር ፍሬ ጨምቆ መራራ ጽዋ እንደሚያስጎነጨው አያስተውለውም፡፡ በከፍታ ዘመኑ ለሰዎች ግድ-የለሽነት የዘራ ጥበብ-የለሽ ሰው፣ የእርሱ ዘመን አልፎ የሌላው ዘመን ሲመጣ ከእርሱ የባሱ ግድ-የለሾች እንዲፈጠሩ የሚያደርገው እርሱው ራሱ መሆኑን መዘንጋት የለበትም፡፡

የዛሬ ጉልበተኛ፣ ነገ ከእርሱ በኋላ የሚነሳው የዘመኑ ጉልበተኛ እንዲረግጠው የሚያደርግን ዓለም የሚፈጥረው ራሱው ነው፡፡ ይህንን ሕብረተሰቡ ከዘመን ወደ ዘመን ሲርመሰመስ የሚኖርበትን ኡደት ግን ለመስበር አቅም ያለው ሰው የጥበብን መንገድ ለማስተዋል ራሱን የሰጠ ሰው ብቻ ነው፡፡  

በጤንነት ዘመንህ ጊዜ ያልዘራኸውን በሕመም ጊዜ አታገኘውም፣ ያልተዘራው አይበቅልምና! በወጣትነት ጊዜ ያልዘራኸውን በሽምግልናህ ዘመን አታገኘውም፣ በሽምግልና ዘመን የሚበላው በወጣትነት ዘመን የተዘራው ዘር ነውና፡፡፡ በብዙ ወዳጅ በተከበብክና በተወዳጅነትህ ጊዜ ያልዘራኸውን በብቸኝነት ጊዜ አታገኘውም፡፡ በአመራር ከፍታ ዘመንህ ያልዘራኸውን የአመራር ዘመንህ ሲያልፍ (ማለፉ አይቀርምና) አታገኘውም፡፡  ከዚህ ውጪ ስሌት የለም፡፡ 

በሚገባ ስናስበው ምርጫችን እጅግ ውስን ነው፡፡ አንዱ ምርጫችን ጤና-ቢሱን ዘር ዘርተን ጤና-ቢሱን ፍሬ ሲበሉ መኖር፡፡ ሌላኛው ምርጫችን፣ የነገን በማሰብ ዛሬ መልካም ዘርን በመዝራት የነገውን ፍሬያችንን በቁጥጥር ስር ማዋል ነው፡፡ ከእነዚህ ከላይ ከተጠቀሱት ምርጫዎች ለየት ያለውን ምርጫ የሚከተሉ ብዙ ሰዎች፣ በጠማማ መንገድ ረጅም ርቀት ከተጓዙና በመጨረሻ ሁሉን ነገር ካጡ በኋላ ትክክለኛውን ነገር ፍለጋ ወደኋላ ይመለሳሉ፡፡ በንግግራቸውና በተግባራቸው የማይሆንን ዘር ሲዘሩ ከርመው አረምን ሲለቅሙ የመኖር ሞኝነት፡፡

መፍትሄው አጭርና ግልጽ ነው፡፡ የምትበላውን ፍሬ ካልወደድከው፣ የዘራኸውን ዘር አስተውልና ቀይረው፡፡ ዘርህ ሲቀየር ፍሬውም ከዚያው ጋር ይለወጣል፡፡ ዛሬ  በምትወስነው ውሳኔህ፣ በምትመርጠው ምርጫህና በምትዘራው ዘርህ የነገህን በትክክል መተንበይ ትችላለህ፡፡

              ውብ ቀን

@hulentenawisket

#EthioHumanity
43 views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:51:58 Live stream finished (11 minutes)
19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:40:20 Live stream started
19:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:38:28 Live stream finished (28 seconds)
19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:38:00 Live stream started
19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:28:15 https://www.youtube.com/@Letarik_4758
222 views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ