Get Mystery Box with random crypto!

HÜDÃ~ìslmìç~çhåññēl

የቴሌግራም ቻናል አርማ huda_islamic_channel — HÜDÃ~ìslmìç~çhåññēl H
የቴሌግራም ቻናል አርማ huda_islamic_channel — HÜDÃ~ìslmìç~çhåññēl
የሰርጥ አድራሻ: @huda_islamic_channel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.08K
የሰርጥ መግለጫ

* Islamic post

Join as @Huda_islamic_channel
Leave ከማለታቹ በፊት ያልተመቻቹ ነገር ካለ @Hudiii_bot ያድርሱን

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:43:04 አሰላሙ አለይኩም ውዶቼ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ልብ ወለዶችን በኛ ምርጫ ስናቀርብላችሁ ቆይተናል አሁን ግን እናንተን ለማስመረጥ ወደድን በቀጣይ ምን ይቅረብ

1 ህሊና
2 የመራም ማስታወሻ
3 ሀፍሳ
4 ተመኒ
333 views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 20:35:04 ያው ነው ማጣት የሌለብኝን ሁሉ አጥቻለሁ ፣ እንዳላጣ ያልኩትን ሁሉ ተነፍጌያለሁ ፣ ለማጣት የምሳሳላቸውን ሁሉ ማጣት ከጀመርኩ የሆኑ ብዙ ዙ ጊዜያት ነገር...እንጃ ወይ የሆኑ አመታት.. ማጣት ለኔ አዲስ አይደለምና አልፈራም። አጣዋለሁ ብዬ የምፈራለት ምንም የለማ! በቃ ምንም.. የማጣት አይነትን ሁሉን አውቃለሁ። ይመስለኛል..ወይ ምን አልባት የምሸሸው እጦት..የምሰጋለት ወይ የማጣው ምንም ያለ አይመስለኝም።
ስልህ ማጣትን ስትለምድ መያዝም አዲስ ስለማይሆንብህና ስለማይበርቅብህ ነገርም ነው። ያው 10 ሰአት ላይ ልታጣውም አይደል 9 ሰአት የያዝከው? ታዲያ ማን ያዝ አለህ? ወይንስ በመያዝህ ውስጥ የመልቀቅ ፍራቻ ነበር?

/አብድልቃድር ኑር/

ከስሜት ጋር
328 views17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:38:13
ሲሰላመት ምንነቃው እኛስ ??

ኢብኑ ጁበይር

ከስር ያለውን የቴሌግራም ሊንክ
JOIN በማድረግ የጀመዐው አባል ይሁኑ
https://t.me/ibnujubair00
527 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:26:05
ለፈገግታ

ኢብኑ ጁበይር

ከስር ያለውን የቴሌግራም ሊንክ
JOIN በማድረግ የጀመዐው አባል ይሁኑ
https://t.me/ibnujubair00
618 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:13:10 ገጣሚኢልሀም
ከናዝሬት

ሰቢትኒ

ወንጀለኛ ነኝ አው ወንጀለኛ
በወንጀሌ ውስጥ በዛው የቀረሁኝ
መውጣትን ፈልጌ ወንጀል ውስጥ ያለሁኝ
ወንጀለኛ ነኝ ብዙ ያጠፋሁ
በሀራም ስራ ውስጥ ገብቼ የቀረሁ
አውቄ እንዳላወቀ በዛው የቀረሁ
ወንጀሌ ብዙ ነውእንዲህ ማይነገር
ምን ብዬ አወራለው ኢሄን መጥፎ ነገር
ኢላሂ እርዳኝ አውጣኝ ከሀራሙ
በሀላል አርገኝ ጠብቀኝ ከመጥፎ

@huda_islamic_channel
639 views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:09:14
.
"እንባዎችም ጸሎቶች ናቸው...እኛ...መናገር በማንችልበት ጊዜ ወደ #አላህ ይጓዛሉ"
.
.
610 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 07:12:44
አላህ ይጠብቀን

ኢብኑ ጁበይር

ከስር ያለውን የቴሌግራም ሊንክ
JOIN በማድረግ የጀመዐው አባል ይሁኑ
https://t.me/ibnujubair00
631 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:08:56 አሰላሙ አለይኩም ውዶች ፍቅር የመሰለ ታሪኩ እውነተኛ ታሪክ ነው ስሞቻቸው ግን ተቀይሯል እናም ከዚህ ታሪክ የተማራቹትን @focus012345 or comment ስር አስቀምጡልኝ እናም ብዙዎች የመመሪያ ሰበብ ይሆናቸው ዘንድ shear አድርጉ ይሄን ታሪክ ላነበቧቹ ሁሉ ጀዛኩሙላህ
667 viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:54:27 ሚመስለኝ ይሆናል። ሰው አፈቀርኩ ሲል በጣም ያበሽቀኛል። ይህንንም የተረዳሁት በቅርቡ ነው! ከዚሁ የቅዠት አለም ስወጣ፤ እርግጠኛ የሆንኩበት ክስተት ሲፈጠር! ምግብ አልበላ አለኝ፣ ካልሴ ሰፋኝ.... ምናምን እያለ ሲዘባርቅ ደግሞ ደሜን ያፈላዋል። ቆይ ትላንት ለማያውቁት ሰው እንዲህ መሆን ምን የሚሉት ነው? "ውዴ፣ ፍቅሬ፣ ማሬ፣ ካላንቺ መኖር አልችልም...." ሙስሊም ከሆኑ ደግሞ "ሁቢ፣ ሀቢቢ፣ ሀቢብቲ፣ ያ ሩሂ" ምናምን ሲባባሉ የዕውነት በጣም ነው የምስቀው። ከእብድ ይቆጥሩኛል ግን ፍቅርን አለማመኔ ልፍቀው የማልችለው እውነታ ነው። ለዛም ነው ከሰው ጋ መቀላቀልና መስማማት የማልችል መስሎ የሚሰማኝ። "ለሁሉም ነገር መሰረቱ ፍቅር ነው!" የሚል መፈክር የያዘ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋ "ፍቅር ውሸት ነው!" የምትል ሴት እንዴት ነው ልትስማማ የምትችለው? ከኹሉዴ ጋ ግን መስማማት ችለናል። አንድ አይነት መፈክር መያዛችን ይሆን? ብዙ ጊዜ ደግሞ ከፍቅር ግንኙነት በኋላ የሚጎዱት ሴቶች ናቸው የሚል እምነት ሲተላለፍ ይስተዋላል። በእርግጥ እንደ ኹሉዴ ሴቶች ቅስማቸው ተሰብሮ የሚቀሩ እንዳሉ ሁሉ እንደ ፉዲም አገኛታለሁ ብለው በፍቅር የሚሰቃዩ ወንዶች ስፍር ቁጥር የላቸውም። ለዚህ ሁላ መንስኤው ሀላልን ወደኋላ ማድረጋቸው ነው። ያ የሆነ ቀን.. የተሰበረ ወንድም ሆነ ሴት አይኖርም!

*
ጁምዓ በዛ መልኩ አለፈ። ሰኞ ላይ ክላስ ከጠዋት ብቻ ነበረን። ከሰዓት ደግሞ ፈተና ስለሚኖር ቤት ደርሳችሁ ተመለሱ ተብለን ነበር። የኔና የኹሉድ ሰፈር ከትምህርት ቤታችን በጣም ስለሚርቅ እዛው ለመዋል ቀናችንን ነድፈናል። ትምህርት እንደጨረስን ሰፊፊፊፊው ሜዳ ላይ ጠለስ ቦታ ፈልገን ተቀመጥን።
<እኔ ግን የሰባህ ነገር አስጨንቆኛል!> አለችኝ ኹሉድ መሬት መሬት እያየች።
<እንዴት?> አልኳት።
<ማለት በቃ... እዛም እንዲህ አይነት ስህተት እንዳትሰራ እየፈራሁ ነው። በዛ ላይ ከአሽረፍ ጋ አጠገብ ለአጠገብ ነው ቤታቸው። ገና አንድ ወር እንኳን ሳይሞላት ከፉዓድ ጋ እንደዚህ ከሄደች እዛ አስበሽዋል?> አለችኝ።
<ልክ ነሽ! የሆነ.. ትምህርት ሰጥተን የምናልፍበት መንገድ ቢኖር ግን ደስ ይለኛል!>
<አስቤው ነበር... ሰባህ ስትመጣ ይሻላል ብዬ እኮ ነው..>
<ኣ ኣ እንዳትሳሳች ኹሉድ። ከነገርሺኝ እንደተረዳሁት ከሆነ ሰባህ የምታመጣው ሀሳብ ደግመን ጓደኛቸው ሁነን እንጫወትባቸው ከሚለው እንኳ የተሻለ አይሆንም> አልኳት። <አዎ ልክ ነሽ.. እና....> ያኔ ነው የመፃፉን ሀሳብ ያመጣነው። ስለ ፅሁፉ በደምብ እያወራን እያለ ኹሉዴ ፈገግ አለችና <ስሚ ሪኑ ፋፊ እኮ በስንት ጊዜው ቴሌግራም ላይ አወራኝ!> አለችኝ።
<እና ምን ያርግ እንደዛ ስቀሽ ተቀብለሻቸው> አልኳት ላናዳት ብዬ።
<እንደውም ላሳይሽ...> አለችና ስልኳን ከፍታ ቴሌግራም ውስጥ ገባች። የፉዓድን የማህደር ምስል ከፍታ ፎቶውን ስታሳየኝ እንደ ድንገት ከአንዲት ልጅ ጋ የተነሳው ፎቶ ብቅ አለ። ቀና ብዬ ሳያት <ተረኛዋ!> አለችኝ።
<ክርስቲስ?> አልኳት ተገርሜ።
<ወላሁ አዕለም!> አለችኝና ቸኮሌት ልትገዛ ተነስታ ሄደች። ሜዳውን በአርምሞ ቃኘሁት። የኹሉዴ ታሪክ ሜዳው ላይ የተዘራ ይመስል ቁልጭ ብሎ ታየኝ። ብያችሁ ነበር እኮ! ፍቀር እንዲህ በስድስት ፊደላት ብቻ በአንደበት የሚገለፅ አይደለም። "ወድጃለሁ" ያለ ሁሉ አፈቀረ አይባልም። ኹሉዴም ሰባህም ሁለቱም ፉዓዶች አፈቀርን ብለው ነበር። ግን አላፈቀሩም! አሁን ገና ነው የፍቅር ትርጉም በደምብ የገባኝ። ልብ ቀድማ ፈጣሪዋን ካላፈቀረች ለሰው ከተራ ስሜት የዘለለ ውዴታ አይኖራትም። ያ ፍቅር ሳይሆን ፍቅር የመሰለ ..... የሆነ ነገር እንበለው ብቻ! ነፍስ ፈጣሪዋን ያፈቀረች ዕለት፤ ትዕዛዙን ታከብርና ወደ ሀላል ትሮጣለች። በሀላል ትተሳሰርና የትዳር አጋሯን ብቻ ታፈቅራለች! እኛ ግን ፍቅር እየልን ያለነው ይሄኛውን ነው! ይሄኛው ማለት? መልሱን ለናንተ ትቸዋለሁ! ኹሉዴ ከነፈገግታዋ በቸኮሌት ታጅባ መጣች። ስለ ፅሁፉ እያወራን እያለ በ12 ተፈታኞች ምክንያት ሁለት ሳምንት ትምህርት እንደተዘጋ ተበሰርን። የልብ የልባችንን አውርተን ከሁለት ሳምንት በኋላ እንደምንገናኝ ተስፋ ተሰጣጥተን ተለያየን። ወይ ሁለት ሳምንት! ይሄው የትምህርት ቤቱን ደጃፍ አልረገጥንም። ሰፈርም አንድ አንዴ እንገናኛለን። ብቸኛው ቤታችን ግን ቴሌግራም ብቻ ነው። አዎን! አሁን እናንተ ይህን ፅሁፍ እያነበባችሁበት ያለበት ቤት!
.
.
.
.ተፈፀመ!


@Huda_islamic_channel

for any comment
@focus012345
658 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:54:06 ፍቅር የመሰለ
ክፍል ሰባት (የመጨረሻው ክፍል)
(ሪና ሁዳ)


መንገድ ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው ዎክ እያረጉ ፋፊ <ኹሉዴ....> አላት።
<ወዬ ፋፊ>
<ኹሉዴ... አንድ የምነግርሽ ነገር አለኝ... ከዚህ በላይ እንድትጎጂብኝ አልፈልግም..> አላት። አሁን ግራ ተጋባች።
<እሺ ምንድን ነው?> አለችው።
<ያቺ....... እኔ የምወዳት.. እሱዋም የምትወደኝ፤ ግን መናገር የፈራችውን ሴት እውነታ.... ልነግርሽ እፈልጋለሁ!> አላት። ኦኬ ጊዜው ደረሰ ማለት ነው? አለች በሆዷ
<ማን ናት?> አለችው። ፋፊ ትንሽ ልቧን ካንጠለጠለው በኋላ <ክርስቲና... > አላት። ኹሉድ ደንግጣለች። ቃል ማውጣት ተስኗት ዝም ብላ የሚያወራውን ታዳምጠዋለች።
<ኹሉዴ... ክርስቲን እወዳታለሁ። ቤቷ ስሄድ ሁሌ ምልክት ትሰጠኛለች ግን ደፍራ መናገር አልቻለችም። ደግሞ በእኔና በአንቺ መካከል ያለውንም ሁሉንም ታሪክ ታውቃለች።.....>
<ለምን ለኔ መንገር አስፈለገ?> አለችው ቆጣ ብላ።
<ኹሉዴ እንደወደድሺኝ እንኳን እኔ ማንኛውም ሰው ከአይንሽ መረዳት ይችላል። አሁን መናደድሽም አንዱ ምልክት ነው። ግን እንድትጎጂ ስለማልፈልግ ብቻ እንደነገርኩሽ እወቂልኝ....> አላት። ምን ትበል? አንዲት ቃል ሳትተነፍስ ቤቷ ደረሰች። ቻው እንኳን አላለችውም ነበር። ቤቷ ከገባች በኋላ አልቅሳ ሲወጣላት ለሰባህ ነገረቻት። ሰባህ ከመናደዷ የተነሳ ደውላ ልትሰድበው ሁላ አቃጥቷት ነበር። ካልወደዳት ለምን እንድትወደው አደረገ? ጨዋታ ላይ ነበር እንዴ?

*
ጊዜው ነጎደ። ሰባህም ወደ ክፍለ ሀገር ተመለሰች ፉዓዶችም ወደ ጊቢ አቀኑ። ኹሉድ ግን የክርስቲና ጉዳይ እስካሁን ውስጧን ይሰረስራታል። ለምን እንደደበቀቻትም ብቻ ሳይሆን ይህን ያህል ጊዜ እያወቀች እንዴት እንደተወቻት ማወቅ ፈልጋለች። አንድ ቀን ሆነ ብላ በጠዋት ቤቷ ትሄዳለች። ሀሳቧ የነበረው ጠይቃት ለመመለስ ነበር። ቤት ከሄደች በኋላ ግን ፈራች። እንዴት ትንገራት? ስለ ፉዓድ አንድም ሳታወራ ምሳ ሰዓት ደረሰ። ምሳ ከበሉ በኋላ እነ ክርስቲ ሱቅ ገብተው ቁጭ እንዳሉ ደፍራ ለመናገር ወሰነች።
<ፉዓድ ምንሽ ነው?> አለቻት ቆፍጠን ብላ።
<ፉዓድ ማለት?>
<ፉዓድ የወንድምሽ ጓደኛ!>
<ወንድሜ ነዋ!> ለማስቀየስ ሞከረች።
<አትዋሽ!> በጣም እየተናደደች መጣች።
<ሁሉም ሰው ምንሽ ነው እያለ ይጠይቀኛል። እኔና እሱ ግን እንደ እህትና ወንድም....> አላስጨረሰቻትም።
<ክርስቲ ከዚህ በላይ ባትዋሺኝ ምን ይመስልሻል? ፋፊ ሁሉንም ነገር ነግሮኛል። ቴሌግራም ላይ ያወራናቸውን ሁላ እንደምታነቢ ጭምር..> አለቻት። ክርስቲና አለቀሰች። ምን አስለቀሳት?
<ኹሉዴ ማርያምን እኔ አልወደውም። መጀመሪያም በሱ ስልክ ፎቶ እንድንነሳ ያረኩት እኔ አንቺ ጋ እንዲሆን ስለምፈልግ ነው እንጂ እኔ አልፈልገውም... አሁንም ላስታርቃችሁ እችላለሁ!> አለቻት አሁንም እያለቀሰች። ኹሉድ ይበልጥ ተናደደች። እንዴት እንደዚህ ታስበኛለች? እኔ አሻንጉሊት ነኝ እንዴ ከፈለገችው ወንድ ጋ እንድሆን የምታደርገኝ?
<ክርስቲ! እንኳን እንደገና ልንመለስ ቀርቶ ከዚህ በፊት አብረን የነበርንባቸው ጊዜያቶች ሁላ ፀፅተውኛል። ቢችል አጠገቤ እንዳይደርስ! ምናልባትም ሙስሊም ብትሆኚ ያልኩሽ በደምብ የሚገባሽ ይመስለኛል!> ብላት ወደ ቤቷ ሄደች። ከዛች ቀን በኋላ የክርስቲና እና ኹሉድ ግንኙነት እየቀዘቀዘ መጣ። አስረኛ ክፍልን እንደምንም ከክርስቲ ጋ ከተማረች በኋላ አስራ አንደኛ ክፍልን ሌላ ትምህርት ቤት ተመዘገበች። እዛም ነው ከእኔ ጋ የተገናኘነው። ኹሉዴ ከምላችሁ በላይ ተግባቢ ናት። ምናልባትም ያለፈውን ታሪኳን ላለማስታወስ ስትልም ይሆናል በሳቋ ለመደበቅ የምትሞክረው። ከእኔ ግን መሸሸግ አልቻለችም ነበር። አሁንም ታሪኳን ስታገባድድልኝ ወደ ቤት እየተመለስን ባለበት ሰዓት ነበር። አላህዬ ሲለው ደግሞ ሁለቱም ፉዓዶች ከፊት ለፊታችን ወደ እኛ ሲመጡ ተመለከትናቸው። ኹሉድ ፈጠን አለችና <ሪናዬ በአላህ ዝም ብለሽ አውሪኝ ባላየ እንዳልፍ> አለችኝ። የኔ ነገር! ወሬው ከዬት ይምጣልኝ? ለወትሮውማ ከኹሉድ ጋ የምናወራው ብናጣ የምንተርበው አናጣም ነበር። የዛኔ ግን ጠፋብኝ። እኛም እየሄድን እነሱም እየመጡ አጠገባችን ሲደርሱ ኹሉድ ሳቋን ለቀቀችው። ተናደድኩ የምር! እነሱም ስትስቅ ገባቸው መሰል <አሰላሙ አለይኩም> ብለውን አለፉ። ኹሉድ <ወአለይኩም ሰላም> ካለች በኋላ በራሷ ተናዳ በእጇ የያዘችውን ባይንደር መደብደብ ጀመረች።
<አንቺ እኮ ችግር አለብሽ! ለምን ሳቅሽ?> አልኳት እየተናደድኩ።
<ባክሽ ልክ ፉዲን ሳየው መጀመሪያ ላይ ለሰባህ "እኔ እንደዚህ አይነት ነገር አይመቸኝም" ሊል የደወለው ስልክ ትዝ አለኝ። አላስቻለኝማ!> አለችኝ። አሁንም እየሳቀች። እኔም ፈገግ አልኩ።
<ግን ፉዲ አሁንም.....> አልኳት።
<አዎን! አሁንም.. ሰባህን ይጠብቃታል። አሁንም ይወዳታል!> አለችኝ። ገረመኝ! እንዲህ በቃላት የተጀመረ ፍቅር እዚህ ይደርሳል ብሎ የገመተ ማን ነበር?
ቆይ ግን ፍቅር ምንድን ነው? በስድስት ፊደላት ብቻ ልብን ሰርስሮ ገብቶ ህይወትን የሚያቃውስ መሳሪያ ልበለው? ወይስ ላይ ላዩን ብቻ የሚነገር፤ በፊልም እና ልብ ወለዶች ብቻ ደምቆ የሚታይ ወሸት የሆነ ዓለም ልበለው? ትርጉሙ እስካሁን ሊገባኝ አልቻለም! እንዲገባኝም አልፈቀድኩለትም! ጊዜ ማባከን ስለ
628 views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ