Get Mystery Box with random crypto!

ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪

የቴሌግራም ቻናል አርማ httpyechalal — ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪
የቴሌግራም ቻናል አርማ httpyechalal — ይቻላል የፊልም እና የቴአትር ቡድን💪
የሰርጥ አድራሻ: @httpyechalal
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው
የራሣችንን ኢትዮዽያዊ ቀለም ይዘን፡፡
ባህልና ማንነታችንን በሃገር ተረካቢ
እፃናት እና ወጣቶች ላይ ለማስቀረት
ብሎም በጥበብ የተናፀነ ጥበበኛ ሠው
ለመፍጠር ፤ የአባቶቻችን እውቀትን
ጀግንነትንና ሃገር ወዳድነትን እያስተማርን
ጀግኖች አባቶች አሣምረው ያስቀመጡልንን
ሃገር ከዘረኝነትና ከፖለቲካ በፅዳ መንፈስ
እንዴት ማቆየት እንዳለብን እያስተማርን እንጓዛለን።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 21:34:56
ትጋት.....!!!

ሰውነት ባዳ ነው ቀን ጠብቆ ይከዳል:: ሠውነትክን ማጠንከሪያ አዕምሮ ነውና ትጋትን አስተምረው! ሁሉም ነገር ጥረት እና ትጋት ሳይኖረው እጅ በእጅ የተደላደለ ነገር አይኖረውም! ነገ ታላቅ ለመሆን ዛሬን ሳትሰለች መፍጋት አለብክ!!! ነገን ለማረፍ ዛሬ መስራት የግድ ነው!!! ነገን የተስተካከለ ለማድረግ ዛሬ መጣር አለብክ!!! ትጋት ፅናት እና ትግዕስት የበሳል ሰው አካሄድ ነው:: ልብክንም አዕምሮክንም ለለውጥ አዘጋጅተክ የደከመውን ሰውነት ብርታትን ስጠው!!! ደከመኝ ሰለቸኝ አትበል!!! ምክንያቱም የተፈጠርከውም ጥረክ ግረክ ልትበላ ነው!!! እናት አባትክ ያስቀመጡልክ የእኔ ነው አትበል!!! ያንተ የሆነው አንተ ፈግተክ ያኖርከው ብቻ ነው!!! የኔ ነው የምትለው ታሪክ እንዲኖርክ ከፈለክ ከተኛክበት ተነስተክ ሩጥ.... ሩጥ....ጀግን.....በርታ የምትፈልገውን እስክታገኝ ፈግተክ ስራ በብልጭልጭ እና በስሜትክ እንዳትረታ!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
161 viewsሚኪያስ አሳምነው (ኑንዬ), 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:30:59
የራስ ሚዛን!!!

ሁሉም የራሱ የሆነ ሚዛን አለው፡፡ ሚዛን በመዛኙ እና በሚመዝነው መሃል ያለ ቁስ ነው፡፡ ሁሉም እንደሚዛኑ ሳይሆን እንደመዛኙ ይወሰናል፡፡ ማንነትክንም የሚዛኑ ባለቤት መዛኙ ይለካዋል፡፡ ሚዛኑን ወደሚፈልገው ይመዝነውና ራሱ ዋጋ ያወጣልክና የሌለክን ስም እና ማንነት ይሰጥካል!!! ከዛም አልፎ ለብዙ መዛኞች አንተን አራክሶ ይነግርብካል አንተም ራስክን የበታች አድርገክ እንድታየው ይገፋፋካል!!! ምን መሠለክ ወዳጄ አንተ ነክ ላንተ ሚዛን ማዘጋጀት ያለብክ ሰው በሚተምንልክ ሳይሆን ራስክን በመዘንከው ልክ ለራስክ ዋጋ ስጠው ምክንያቱም አንተ ላንተ ውድ ነክ!!! አንተ ላንተ ታላቅ ነክ!!! አንተ ላንተ ሃያል ነክ!!! ለዚህ ደግሞ ወሳኙ ነገር ለራስክ ያዘጋጀከው ሚዛን ነው፡፡ ሚዛንክን ወደጥንካሬ እና ወደ ብርቱነትክ እንዲያመዝን ካደረከው መመረቅክም መረገምክም ላንተ አያስገርምክም!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
219 viewsሚኪያስ አሳምነው (ኑንዬ), 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:33:57
ሁሉም በልቡ ሊረሳው የማይችለው ትዝታ አለበት፡፡ ሁሉም ልቡ ላይ ሊፋቅ የማይችል የትናንት ቁርሾ በልቡ ይዞል!!! ትዝታ የትናንት ጥሩ መስታወት ነው:: ባለፈ ትናንት ፈገግታ ሃዘን ቁጭት ህመም አልፎ ይሆናል፡፡
አልፏል የሚለው ቃል ብቻ ብርታት ነው አልፏል!!! አልፏል!!! አልፏል!!! ሁሉም አልፏል!!! ማለፋ አንድም ለትዝታ አንድም ለተስፋ ዳርጎናል ትናንት አይረሳም በትናንት መንገድም የነበረ ከልብ አይጠፋም ከልብም አይወጣም ምክንያቱም መልካም ትዝታ ለመልካም ዛሬ!!! መጥፎ ትዝታ ደግሞ ለመልካም ዛሬ ትምህርት ሆኖ ስላለፈ ዛሬ ላይ ግን ትናንትም ይናፍቃል!!! ነገም ይናፍቃል!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
255 viewsሚኪያስ አሳምነው (ኑንዬ), 18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:38:14
ሁሉም ከልኩ አያልፍም!!!

ከባድ መስለው የሚታዩ ነገሮች በሙሉ!!! ሰው ሲያደርገው ወይም ሲሰራው ተመልክተን ወይኔ እኔስ እንደሱ መቼ ነው የማደርገው!! መቼ ነው እሱ የደረሠበት የምደርሰው!!! መቼ ነው አድጌ እሱ የሚሰራውን የምሰራው!!! ብለን አስበን ይሆናል!!!
ግና ነገሮችን አንዴ እስክንጋፈጣቸው ነው እንጂ ሁሉም ከልኩ አያልፍም!!! የእድሜ ወይም ደግሞ የመቅደም መቀደም ጉዳይ ሳይሆን የልብ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ የጠነከረ ልብ ካለክ መቼም በእኔ አቅም አይሆንም ብለክ ያሰብከውን ነገር ዛሬ ታደርገዋለክ፡፡ ተራራ መስሎ የሚታይክ ነገር የጀግና ሰው ልብ ባለቤት ከሆንክ ከተራራው በላይ የገዘፍክ ትሆናለክ፡፡ ብቻ ግን ለልብክ እንደሚሆን እንደምታደርገው እና እንደምትችል ደጋግመክ ንገረው፡፡ ልብክ የእውነት መንገድ ተጓዥ ከሆነ የማትችለው አለመቻልክን ብቻ ይሆናል!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
253 viewsሚኪያስ አሳምነው (ኑንዬ), 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 22:45:05
እራስህን አሸንፈህ ትግልህን ጀምር!!

ምን ጊዜም ከደስታም ሆነ ከሀዘን ጀርባ የማይፋቀው ማንነትህ የራስህ ስብዕና በውስጥህ አለ። ያንን ስብዕና ያንን በማህበረሰብ በአጉል አመለካከት የተጠመደውን ማንነትህን ታገለው! አሸንፈው!
እራስህን እመነው ማድረግ ፈልገህ ማድረግ የማችለው አለመቻልህን ብቻ ነው።
ያንተ ድክመት አንተ ነህ ያንተ አዋቂም አንተ ነህ። ለንፋስ ቦታ አትስጥ። ከቆምክበት አንዳችም ነገር እንዳያዛንፍህ ጠንክር።
እራስህንም አሸንፈህ ትግልህን ጀምር ካንተ በላይ የጠነከረ የለምና ::

ይህ የኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው!!!
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
262 viewsሚኪያስ አሳምነው (ኑንዬ), 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:55:58
ትወድቃለክ አትወድቅም እሱ ጥያቄ አይደለም!!! ሁሉም ይወድቃሉ ጥያቄው ግን ትነሳለክ ወይንስ እዛው ትቀራለክ ነው!!!! ጀግና ጀግንነቱ የሚታየው በፈተና እና በመሠናክል መሃል አልፎ ያለመው ላይ መድረስ ሲችል ነው!!! አንዳንዴ መውደቃችን ለመልካም ነው ብለን አስበን! ነገ መልካም እንደሚሆን ለልባችን ደጋግመን በመንገር ሃይላችንን ጨምረን ከወደቅንበት እንነሳ! ዛሬ ለነገ መሠረት ናት!!! ሰው ካስቀየምን በይቅርታ እናልፈዋለን! ሰው ከደከመ አይዞክ ብለን ለማበርታት እንሞክራለን! ታዲዬ ለእኛስ ያለ እኛ ማን አለን!!! ከሰውነታችን በላይ አህምሯችን እንዳይደክም ብርታትን እንስጠው! ከደከመ ከወደቀ ደግሞ ልባም እንደሆነ እና ማንም ከሚለው በላይ ጀግና እንደሆነ ለራሳችን ደጋግመን በመንገር ብርታትን እንስጠው!!! ምክንያቱም ላንተ ካንተ የቀረበ ማንም የለህምና!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
512 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 20:25:21
ክረምት እና በጋ

ከክረምቱ ከውርጩ ከጨለማው ጥልሸት ካጠቆረው ደመና የተሻገረ!!! እና ጨለማውንና ውርጩን ፈርቶ ተደብቆ ያለፈ ሠው መሃል ሠፊ ልዩነት አለ!!!
ያ ጨለማውን በተስፋ አብሮን የተጋፈጠ በከፋን ሰዓት ከጎናችን ሆኖ አይዟችው ያለን!! ሁሉም በራቀን ሰዓት አብሮን አዘናችንን የተካፈለ ዋጋው ከቃል በላይ ነው:: ሁሌም እንደምንለው ነው ሁሉም ያልፋል ሃዘንም በደስታ ይቀየራል ያጣ ያገኛል:: ክረምት በበጋ እንደሚቀየር ሁሉ ሃዘንም በደስታ እንደሚቀየር አስበን የጨለመን ተስፋ ከልባችን አርቀን!!! ነገን በብሩ ተስፋ አሻግረን እየተመለከትን አብረን እንደጀመርን አብረን እንጨርስ!!! ምክንያቱም ጀግና ማለት አብሮክ የጀመረ ሳይሆን አብሮን መጨረስ የቻለ ነውና!!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
354 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 21:10:18
አሸናፊዎች ራሳቸውን ማሸነፍ የቻሉ ናቸው!!!
ወዳጄ ያለተፎካካሪ መጓዝ እና በተፎካካሪ መሃል ሆነክ መጓዝ ሰፊ ልዩነት አለው፡፡ ያለተፎካካሪ መጓዝ ማለት ራስን ከሌላ ሰው ጋር አወዳድሮ ለማሸነፍ መጣር ሲሆን! በተፎካካሪ መጓዝ ማለት ደግሞ ራስን ከራስ ለማወዳደር መሞከር ነው፡፡ ፋክክርክ ከራስክ ጋር ይሁን !!!
ከራስ ጋር መሽቀዳደም ደግሞ የጀግና ሰው አካሄድ ነው ምክንያቱም የአሸናፊዎች አሸናፊ የመጨረሻው ዙሩ ራስን ከራስ ማወዳደር ነው፡፡ ፍርሃትን ከድፍረት ውድቀትን ከመነሳት ጨለማን ከብርሃን አለመቻል ከመቻል አወዳድሮ ድል ያደረገ መቼም መውደቅም ሆነ መሸነፍ አይችልም!!! ስለዚህ ወዳጄ ሃይልክን ጨምረክ ራስክን ከራስክ አወዳድረክ ከትናንት ዝቅታክ እና ከነገ ከፍታክ ዛሬ ተወዳደር ከዛ ትናንትን አሸንፈክ ታሪክ ስራ የምታሸንፈው ደግሞ መወዳደር ስላለብክ ብቻ ሳይሆን ተወዳድረክ ማሸነፍም ስለምትችል ነው!!
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
341 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 20:38:07
አጋጣሚዎች በሙሉ መልካም ክስተቶች ናቸው የምናመሠግንበት እንጂ የምንማረርበት አጋጣሚ የለንም በሕይወታችን ውስጥ ብዙ መልካም እና ደጋግ ሰዎችን አስተናግደናል ይቻላል የሰው ሃብታም ነው ብዙ አብረውን በመልካም ያሳለፉ መልካም የጥበብ ሰዎች ነበሩን አሁንም በችግራችንም በደስታችንም ፈጥነው የሚደርሱ ደጋግ ሰዎች ካገኘነው ነገር ውስጥ ትልቁ ሽልማታችን እነሱ ናቸው፡፡ በአብሮነታችን የምንደምቅበት ብዙ ሠው!!! ማንነታችን እንደስማችንና እንደስራችን መሆኑን በልበሙሉነት የሚያወሩበት መልካም ሰው የሰበሰበ ቤት ባለቤቶች ነን:: ይቻላል ሰው ናፋቂ ቤት ነው !! የዚህ ሁሉ ምክንያቱ ደግሞ ይቻላል የሠውመሆን ተምሳሌት ስብስቦች መሆናችን ብቻ ነው!!!

ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
335 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:15:36
ሁላችንም ያለነው በቃል ነው!!! ለብዙ ሠው ብርሃን!!! ለብዙ ሠው ድልድይ!!! ለብዙ ሠው መሠላል!!! ለብዙ ሠው ሻማ!!! ለብዙ ሠው ተስፋ!!! ለብዙ ሠው ወንድም!!! ለብዙ ሠው ህልም!!! እንድንሆን ያደረገን ቃላችንን በተግባር ማሳየታችን ነው፡፡ እውነት ነው ይቻላል አይደለም በሚያውቁን በቅርባችን ላሉ ሠዎች ይቅርና ለሩቅ ላሉትም ደስታ ነው የሁላችንም መንገድ የተለያየ ሊሆን ይችላል መድረሻችን ግን አንድ ነው፡፡ እኛ ይቻላሎች ከልባችን እንዋደዳለን እንተሳሰባለን እንከባበራለን ለዚህ ደግሞ ማሳያው የተሳካውና ያማረው ስራችን ምስክር ይሆነናል በተስፋ የተሞላ ቤት ነው የምንገናኝበት ቀን ይናፍቀናል የመጣነው መንገድ አስተሳስሮናል ይቻላል ከቃል በላይ ነው የምንለው በምክንያት ነው::
ይህ የእኛ የሁላችን የይቻላል ቤት ነው።
@httpyechalal
@httpyechalal
@httpyechalal
361 viewsMicki asaminew (ኑንዬ), 18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ