Get Mystery Box with random crypto!

💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው ቅድሚያ ለተዉሂድ💎🎀

የቴሌግራም ቻናል አርማ https_asselefya1 — 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው ቅድሚያ ለተዉሂድ💎🎀
የቴሌግራም ቻናል አርማ https_asselefya1 — 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው ቅድሚያ ለተዉሂድ💎🎀
የሰርጥ አድራሻ: @https_asselefya1
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.89K
የሰርጥ መግለጫ

◁النساء السلفية اغلى من الذهب الأحمر
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

➧የሰለፊይ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው።
➷ውስጧ በዐቂዳ፣ በሱና የጠራ
በሀያእ በእውቀት፣ልቧ የጎመራ
በሠለፎች መንገድ፣ እምነቷን ተያዘች
አማኟ እህቴ እሷማ ውድ ነች!!
«المرأة الصالحة

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 08:15:42 ➧ሀቢብቲ ያንቺ  መከናነቢያና ኒቃብሽ ⁈

በእምነትሽ ላይ ያለሽን እውቀት
የሚገልፅ ነው።  አለማወቅን መላቀቅሽንና
ብልጠትሽን እጅግ ውብ ዘመናዊነትሽን ያሳያል።

እንደመሸፋፈኛሽ አንደበትሽም ንቁና የተረጋጋ አሰተዋይ ሀቀኛ ይሆን ለማወቅ በምታደርጊው ጥረት ድክመትሽን ጃሂልነት  ያደረጉ ለሚቆነጥጡሽ ሰዎች በመልካም ባህሪ አዋቂነትሽን አሳያቸው።

አላህ በሰጠሽ እውቀት ላይ አመስጊኝ  ጭማሪን ታገኚ ዘንድ በተሰጠሽ ላይ አለማመሰገን አንድ ክህደት ነውና !!

وإذ تأذن ربكم لئن شكرتم لأزيدنكم ولئن كفرتم إن عذابي لشديد
ማወቅ ባለብሽ ነገር ላይ ጥረትን አድርጊ በጥረትሽ ላይ አላህ እንዲ ከፍትልሽ ዱዓ አድርጊ፣አስባቡንም  አድርሺ፣ስራሽን ፍፁም ለጌታሽ አጥሪ አላህ ለሱ ብሎ የታገሉትን አይጥልምና !

وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا
وَإِنَّ اللهَ لَمَعَ المُحْسِنِينَ
እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡

https://t.me/https_Asselefya1
124 viewsedited  05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:09:52 ➧የዕለቱ መልዕክት➛ወንድ ሁን!

ሴት ልጅ ትለምነኝ ትለማመጠኝ አትበል
ትታገልልኝ ላድክማት  ልፈትናት ልንቀባረርባት አትበል!!

ወንድ ሁን አንዱ የውንድነት መገለጫህና ውበትህ የወንድነት መለያህ  ከላይ የተጠቀሰው በግልባጭ አንተጋ ሚገኙ ሲሆኑ ነው በቃ ወንድነሃ እነዚህ ያንተ ስራዎች ናቸው ወንድነት በፆታ ብቻ አይገለፅም በዋናነት ተግባሩ ነው ሚገልፀው!
!

ስለዚህ ቀድህ ተገኝ ለሴት ልጅ ተንበርከክጂ እንድትን በረከክልህ አትፍቀድ አሸንፍጂ አትሸነፍ  ቅደምጂ አትቀደም ኢማም ሁንላትጂ ኢማም  አትሁንልህ ፈጣን ቀልጣፋ ጂ ልፍስፍስ አትሁን ምራትጂ አትምራህ አስተዳድራትጂ አታስተዳድርህ አግባትጂ አታግባህ ለምናትጂ አትለምንህ  ምከራትጂ አትምከርህ አስተምራትጂ አታስተምርህ!!

ደግ ሁንላትጂ አትክፋባት ታዘዛትጂ አትገልምጣት እጄ አስገባኋትጂ እጄ አስገባሁት አትባል በቃ ወንድ ሁን ቀዳሚጅ ተቀዳሚ አትሁን ፈጣን እንጂ አዝግም አትሁን!

አስተዋይ እንጂ ዝፍቅ አትሁን ሚያስደስትንና ሚያስጠላን ራስህ ለይጂ ሰዎች እንዲለዩልህ አትፍቀድ ጧሊበተል ኢልምጂ ጃሂል አትሁን በቃ ቅደምምምምም  ይህ ነው በወንድ ላይ ሚያምረው ሚገልፀው ስለዚህ መገለጫዎችህን እወቅ ላንተ የሆኑትን ያልሆኑ ቦታ ላይ እንድታይ አትፍቀድ......!!

ኮፒ!

https://t.me/https_Asselefya1
366 viewsedited  05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 08:04:40ልጅ መውለድን አብዙ ሲሳያችሁ ይበዛል

ሙሀመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:-

➲"በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬን በማሳደር ልጆችን አታብዙ፤ ሲሳያችሁ ይጠባል ያለ ሰው በእርግጥም ግልጽ የሆነ ጥመትን ተጣሟል።

➲በአርሹ ጌታ እምላለሁ በዚህ ንግግራቸው ዋሽተዋል። ይልቁንም ልጅ ሲያበዙ አሏህ ሲሳያቸውን ያበዛላቸዋል።

➲ምክንያቱም በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ሪዝቋ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ወጪ ታደርግላቸው ዘንድ የልጆችህን ሲሳይ የሚከፍትልህ አሏህ ነው።


➲አብዛኛው ሰው ግን በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ያሳድራል፤ ፊት ለፊቱ ባለው በሚታየው ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ ይደገፋል፤ የወደፊቱንም አያይም፣ የጌታውንም ችሎታ አይመለከትም። ልጆች ቢበዙም ሲሳይን የሚለግሰው እሱ 7 ነው።ልጆችን አብዛ ሲሳይህ ይሰፋል።ትክክለኛው ይህ ነው ።"

ሸርህ ሪያዱሷሊሂን [1/91]


https://t.me/https_Asselefya1
167 views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 07:58:05 تلاوة جميلة لخواتيم سورة المؤمنون

للقارئ صالح الفالح

https://t.me/https_Asselefya1
132 viewsedited  04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:37:16 ሸር አድርጋችሁ አሰራጩት

#ዘመንመለወጫ!!?

ማነሽ እንቁጣጣሽ..!!?

http://t.me/nuredinal_arebi
452 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:37:16
#ዘመን_መለወጫ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዘመን መለወጫ የለንም ወዳጄ፡
ኮተት አልፈልግም ዘወር በል ከደጄ፡
ሙሉ ፅድት ያለ ሐቅ ነው መንሀጄ፡
ከሉቃስ ዩሀንስ ከማርቆስ ክርስቶስ፡
ከሰውች ወደሰው ከቄርቆስ ቆሮንጦስ፡
ኸረ ለቀቅ አርገኝ አያልቅም ያንተ ጦስ?
ወደ ሰው መጠጋት ሙስሊሞች አንወድም፡
ከአንድ አምላክ በስተቀር ለማንም አንሰግድም፡
ለማርቆስ ለሉቃስ አናጎበድድም፡
ምንክንያቱም ሙታን ምንም አይፈይድም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ስለዚህ ራቂኝ ማነሽ እንቁጣጣሽ፡
ወደኛ አትጠጊ ዞር በይ እስከ ሻንጣሽ፡
እኛ እናውቅሻለን ከየት እንደመጣሽ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በእስልምናችን የለም እንቁ ጣጣሽ፡
ዘመን መለወጫ የሽርክ ብጥስጣሽ፡
የድግምት የመተት ክፋት መተግበሪያ፡
የክፋት የሴራ ተንኮል መቀመሪያ፡
እውነታ የሌለሽ የኩፋር መመሪያ፡
እውነትን ሰርዘሽ ውሸት ማስተማሪያ፡
ሐቅን ባጢል ብለሽ ጥመት ማበጠሪያ፡
ውስጥሽ ውጭሽ ቦድ ግድግዳሽም ጣሪያ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኢብሊስ የገነባሽ የጭፍሮቹ መተት፡
አማኞች አያውቁም እንድህ አይነት ኮተት፡
ሐቁ መመሪያችን ካላፀደቀልን፡
ውዱ ነብያችን ካልመሰከረልን።
በነሉቃስ ቀመር ተጓዥ አይደለንም፡
ዘመን መለወጫ ፈፅሞ የለንም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአመፅ የበደል የወንጀሎች ቅርጫ፡
የሸይጣን የአጋንንት የጥመት መፈንጫ፡
የመጥፎነት ማዕረግ የሙሽሪኮች ዋንጫ፡
ሽርክን ክህደትን በጥብጦ መጠጫ፡
ሙስሊሞች የለንም ዘመን መለወጫ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ኑረዲን አል አረቢ 01/26/1443
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
518 views14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:00:35 ተከታታይ የኪታብ ደርስ


ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
➊➊

በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
440 viewsedited  12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:02:10 ➮አደራ ሸር በማድረግ አሰራጩት

በተለይ_በሀገራችን_ወሎ___!!

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
530 viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 10:56:07 የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች

ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-


➧ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

➧ ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

➧ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

➧ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።


3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-


አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)


የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
639 viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ