Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ቅዱሳን ክፍል 6 እንግዲ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፡ይህ አዲስ ተደርጎ የተፈ | ሰማያዊ ስጦታ ቤተክርስቲያን 🌍

ሰላም ቅዱሳን ክፍል 6
እንግዲ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፡ይህ አዲስ ተደርጎ የተፈጠረው ሰው የመንፈስ ፍሬ ደግሞ አልፎም በስጋ ህይወት ላይ የሚገለጥ ህይወት አለው ብለናል።
መነሻ ጥቅስ ፥- ገላ 5፥22
ገላትያ 5 (Galatians)
22፤ የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።

አዲሱ ሰው እና የመንፈስ ፍሬ
6.በጎነት
Greek translation.... Agathosyne
English Translation...Goodness
አማርኛ ፍቺ.....በጎነት

በገላትያ ምዕራፍ 5
ከተገለጹት የመንፈስ ፍሬዎች መካከል አንዱ "በጎነት" ነው፡፡ በጎነት ለሰዎች ያለን መልካም አመለካከትና የምናደርገው ማንኛውም መልካም ሥራ ሁሉ ነው፡፡

በጎነት ማንኛውንም መልካምና ጥሩ፣ የበጀ የተወደደ፣ ሥራን ያካትታል:: አምላካችን እግዚአብሔር በባሕርዩና በሥራው በፈጠረው ፍጥረት መደነቁ ሁሉ የበጎነቱ አይነተኛ ምልክት ነው፡፡ ሁሉንም በየወገኑ በመፈጠሩ ማለቴ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በፍጥረቱ በጎነት ይታወቃል እንዳሉ አበው እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን በጎነት ሲባል ንጽጽራዊ በጎነት ማለት ነው፡፡ ፍፁም በጎነት የእግዚአብሔር ባሕርይ ብቻ ነው፡፡
“የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ” ማቴ. 5፡48 ተብሎ በጌታ ቃል ከተገለጸው ፍጹምነት ጋር ተመሳሳይ ነው ይህም ንጽጽራዊ ፍጹምነት ነው፡፡

  ሁለት ዓይነት በጎነት አለ ይኸውም

1.አሉታዊና
2.አወንታዊ

አሉታዊ በጎነት ማለት ክፋትና ኃጢአትን ማስወገድ ነው፡፡ ይህም በ10ቱ ትዕዛዛት ውስጥ የምንማራቸው ናቸው፡፡

“የአግዚአብሔር የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ…”ዘዳ.5፡11በሚለው ውስጥ በእምነት የምንተገብራቸው ናቸው፡፡

አወንታዊ ስንል ደግሞ በጎነትን በብሉይ ኪዳን ውስጥ ስንመለከት “አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍፁም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ኃይልህ ውደድ" ዘዳ.6፡5 በሚለው ውስጥ የተካተቱት ናቸው፡፡
አዲስ ኪዳንም ውስጥ ክርስቶስ ስለ ብፁዓን በተናገራቸው ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ ተጠቅሰዋል፡፡
"በመንፈስ ድሆች የሆኑ…የዋሆች….ልበ ንጹሖች…የሚያስታርቁ…ብፁዓን ናቸው ወዘተ…"ማቴ.5፡3፡፡ አሁን በጻፍኩላችሁ በበጎነት የመንፈስ ፍሬ ላይም በግልጽ የምንማረው ነው፡፡

ከማንኛውም ኃጢአትና ክፉ ሥራ ሁሉ ለመራቅ፣ እና በመልካም ምግባር ታንጾ ለመጓዝ ሁለቱንም መንገዶች መከተል አለብን በሕግና በፍቅር /በውዴታ/የምንፈጽማቸው የበጎነት ሥራ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ሙሉ የሆነ በጎነትን ገንዘቡ ካደረገ ከማንኛውም ክፉ ነገር ነፃ ይሆናል፡፡

ይህን በእውነተኛ መጽሐፍ ቅዱስ መረጃ ለማስረዳት የሞከርኩትን ከዚህ የሚከተለውን በጥሞና አንብባችሁ ተረዱልኝ፡፡ ይስሐቅና እስማኤል፣ ቃየልና አቤል በአንድነት መኖር እንዳልቻሉ ሁሉ መንፈስና ሥጋ /አሮጌ ተፈጥሮ/ እርስ በርሳቸው በተቃውሞና በጦርነት ላይ ናቸው፡፡

መንፈስ ቅዱስ አካላችንን የሚቆጣጠረው ከሆነ በመንፈስ እንመላለሳለን ሥጋ አካላችንን የሚቆጣጠረው ከሆነ በሥጋ ምኞትና ፍላጎት እንመላለሳለን፡፡ በመንፈስና በሥጋ መካከል ያለው ተቃውሞ ምክንያት መንፈስና ሥጋ የተለያዩ ፍላጎቶች ያላቸው መሆናቸው ነው፡፡

ለምሳሌ፡-
በግ ቆሻሻ ነገሮችን የማይወድ ንፁሕ እንስሳ ስለሆነ ነው፡፡
አሳማ ግን ከታጠበች በኋላ ወደ ጭቃ የምትመለስ ንጽሕናን የማትወድ ናት::

2ጴጥ 2፡19በኖኀ ዘመን የሆነው ቁራ ሥጋ በል እንደመሆኑ በቂ ምግብ በማግኘቱ በዚያው ቀረ፡፡
"መልካሟ ርግብ ግን የምሥራች ይዛ ተመልሳ መጣች ሁለተኛ ሲለቃት ወዲያው ቀረች የምታርፍበት ምድር ተስተካክሎ ነበርና"
ዘፍ.8፡6-12

ሮሜ7፡15 ፤ ዕብ10፡14 ፤ 2ቆሮ3 ፤ 1መዝ40፡8 ፤ 1ጢሞ1፡9 ፤ 2ጢሞ3፡2 ፤
ኤር. 17፡9 አንብቡ፡፡

ቅዱስ ዳዊት “ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም”መዝ.15፡2 ባለው መሠረት የክርስቲያኖች በጎነታቸው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ምክንያቱም ቃሉ እንደሚለን “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደአሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን” ሮሜ.8፡28
ከእግዚአብሔር የሆነው ነገር ሁሉ በጎ ነገር ነው፡፡
ይህንን የእግዚአብሔርን በጎነት ለሰው ልጆች በሙሉ ማስተማር መንገር አለብን 1ጴጥ.2፡9
ክርስቲያኖችም መልካም ሥራን መፈለግም ሆነ ማድረግ የምንችለው በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ነው፡፡
“የአግዚአብሔር በጎ ፈቃድም በስብከት ሞኝነት የሚያምኑ እንዲድኑ ነው" ፊልጵ2፡13
ቅዱስ ጴጥሮስ “በጎ ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው ብሏል" 1ጰጥ3፡13

በክርስትና ኃጢአት የሚባለው ክፉ ሥራ ብቻ ሳይሆን በጎ አለማድረግም ነው፡፡ “እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው”ያዕ4፡17:: ሐዋርያው ያዕቆብ በተጨማሪ እንዲህ ሲል ይመክረናል “የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ አትሳቱ በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡ በጎ መሆን በራሱ ስጦታ መሆኑን አስረድቷል”

በጎ ሥራ የሌለው እምነት የሞተ ነው

“ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ወንድም ወይም እህት ራቁታቸውን ቢሆኑ የዕለት ምግብንም ቢያጡ ከእናተ አንዱም በደኅና ሂዱ እሳት ሙቁ ጥገቡም ቢላቸው ለሰውነት ግን የሚያስፈልጉትን ባትሰጡአቸው ምን ይጠቅማቸዋል? እንደዚህም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞት ነው” ያዕ. 2፡14

በጎነት ከቅናት የራቀ ነው

"ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው?በመልካም አነዋወሩ ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ፡፡ ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም ነገር ግን የምድር ነው፣ የሥጋም ነው፣ የአጋንንትም ነው ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ሰፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ አሉና፡፡
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት በኃላም ታራቂ ገር እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት፡፡ የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል" ያዕ3፡13 ሲል ያስተማረው የበለጠ ልብ የሚነካ ምስጢር ነው፡፡

ስለዚህ አዲሱ ሰው ይህ ህይወት ስላለው ፡ወደዚህ መንግስት
" ኑ " እንላለን ።

እንግዲ አምላኬ እንደባለጠግነቱ መጠን የሚያስፈልጋችሁን ይሙላባችሁ እንዲባል የልቦልናችሁ አይኖች በርተው የመጥራቱ ተስፋ ምን እንሆን ማወቅ ይሁንላችሁ።
===============================
ለዚሁ ነው እኛም ጌታን ሰምተን የቻናላችን ስም Goodness of christ Gospel Minstry ያልንበት ክርስቶስ ኢየሱስ በዘመነ ምድሩ ጲጥሮስ ና በለኝ ካለ በኋላ በባህሩ ላይ ትንሽ ከተራመደ በኋላ መሃል ላይ ሊሰጥም ሲል እንጁን ይዞ (አዳነው) ይላል።

ይህ ነው ትክክለኛ መልካምነት ከኢየሱስ ያገኘነው።በዘላለም ጥፋት ውስጥ እንዳንገባ፡ራሱን ሰጥቶ ወደዘላለም ሃሳቡ በበጎነቱ የሳበን።ኢየሱስ ክርስቶስ ለአለም ሁሉ በጎነቱን ገልጿል