Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ. ሚስት .. አንድ. ሸይኽ እንዲህ አሉ [ ብናውቅ ኖሮ በእናታችን ሆድ ውስጥ ሆነን መልካ | 📚منهج السلف طريقن الى الله 📚

ምርጥ. ሚስት ..

አንድ. ሸይኽ እንዲህ አሉ
[ ብናውቅ ኖሮ በእናታችን ሆድ ውስጥ ሆነን መልካም ሚስት ስጠን ብለን እንለምን ነበር ብለዋል። ]

ተወልደን አድገን አልፎም ያገባው ስለመልካም ሚስት ዱአ  ሊዘናጋ አይገባም።
ምድር ካስተናገደቻቸው ምርጥ ሚስቶች መሐከል፦


ዛሬ ባለትዳሮች መሐከል ይህ ድርጊት ታደርጋለች ተብሎ ባይታሰብም የነብዩ ባለቤት አይሻ
( አሏህ ስራዋን ይውደድላትና)
እንዲህ ነበረች ፦
[ የመልክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ልብስ እርጥብ
መንይ በነካው ጊዜ አጥብላቸው ነበር መንዩ ደርቆ ከሆነ

እፈቀፍቅላቸውና ይሰግዱበት ነበር ] ብላለች።
~ አይሻ ሳትጠየፍ ሳታፍር ሰርታ ያለፈችው ዛሬ በኢልም ማዕዶች ላይ ስለዚህ ርዕስ ሲወራ
ወንዶችም

መሽሞንሞናቸው ሴቶች አይን አውጣ እባለለሁ ይሁን ብቻ አላውቅም ከሀቅ ያፍራሉ ።


~ አይሻ እድሜዋ ከ ነብዩ ሲጋቡ ዛሬ በሰፈራችን የሚጫወቱ ህጻን አይነት እድሜ ላይ ነበረች
~ አይሻ ውዱ ነቢይ ወደ አኼራ ሲሄዱ እድሜዋ 18 ዛሬ ለትዳር ለማጨት ስትጠይቅ እድሜዋ አልደረሰም ብለው
እንደሚሸኙ አይነት ነው


~ አይሻ ከ 9 እስከ 18 አመት ባለው እድሜዋ የመልክተኛው የጀርባ አጥንት ሆና አለፈች ዛሬ አላህ ያዘነላቸው ሲቀር በሆነ ባልሆነው የምትነዘንዝ በዝተዋል


~ አይሻ በዛች እድሜዋ የሰራቻቸው መልካም ስራዎች የተጎነጨችው ኢልም ዛሬ የእኛ እህቶች መሬት ወርደው

እንደ ሚዳቆ በገመድ ዝላይ እና ሰለጠኑ ከተባለ በቀለም አሸብርቆ በታኮ ጫማ ልታይ ባይነት ያሳስባቸዋል

~ አይሻ ከመልክተኛው ጋ ከአንድ ወር በላይ ቤታቸው እሳት ሳያቀጣጥሉ እንዲሁም የሚበላ አጥተው አሳልፈዋል የእኛ እህቶች ዱንያ ዘውታሪ መስሎዋቸው ይሁን ብቻ አላውቅም እቃ ቤት ውስጥ  አስቤዛ ካልተከማቸ ይሉሃል

~ አይሻ ከነቢያችን ጋር ስታሳልፍ ተደራራቢ ብፌ፣ አረቢያ መጅሊስ፣ ዘመናዊ ማንኪያ፣ ጭልፋ ፣አልጋ እንዲ አይነት፣ፍራሽ ካልገዛህ አላለችም ዱንያ አላፊ መሆንዋን ተረድታ የነበረው የዘምባባ ኬሻዋን አበጃጅታ ይተኙበት ነበረ

~ አይሻ እንደ ዛሬ ቀለም ሰራተኛ መስለው ወጥተው ከሚታዩ ሴቶች በተቃራኒ ከደሳሳ ጎጆዋቸው መውጣት

አታስበውም ነበር የዛሬዎቹማ ኒቃብም ለብሰው ኒቃባቸው ከፍተው ሲመገቡ ካፌ ላይ ይታያሉ ___ከአይሻ ያለው
እርቀት !!

~ አይሻ የእኛ እናት የረሱል ሚስት.    የትዳር ምርጥ ተምሳሌት
[ የነብዩ ሙሐመድ አለይሶላቱ ወደሰላም ምርጥ ሚስታቸው ነበረች  ]
ልጠቅልለውና


ጥሩ ሚስት እያልክ ስትቦርቅ የመልክተኛው ባህሪ ሙሉ
ስብዕና ለሚስታቸው ምን አይነት እንደነበሩ ማወቅ
መልካም ሴት ከመፈልግ ይቀድማል ብዬ አምናለሁ።


https://t.me/umufwzan
https://t.me/umufwzan