Get Mystery Box with random crypto!

#የወሎ_ልጅ_አብሽር_!! --------------------------------- አንዳንዴ ተናገር ግ | 📚منهج السلف طريقن الى الله 📚

#የወሎ_ልጅ_አብሽር_!!
---------------------------------
አንዳንዴ ተናገር ግድ ፃፍ ይለኛል፡
ሙስሊሙ ሲነካ ሲጠቃ ያመኛል፡
ልቤ ከነርሱ ጋር ጭልጥ ይልብኛል፡
እምነቴ ሲደፈር ውስጤን ይነዝረኛል፡
ወተት ነህ እያሉ አልበውት ሲያበቁ፡
ዛሬም ያሴራሉ እየተደበቁ፡

በኛ ሸፍጥ ሰርተው ፊኛ ቢወጠርም፡
ወሎዬ በፍርሀት አይጠረጠርም፡
ጀግና ልጅ እያለው ክብሩ አይደፈርም፡
ዳግም ለህውሀት ወሎዬ አይገብርም፡
ነጋሪት ተመታ ማንም ተደለቀ፡
የወሎ ልጅ ቆርጧል አይሆንም አለቀ።

-------------------------------------------
ደሙ እየፈሰሰ ንብረቱን ተዘርፎ፡
በሙስሊምነቱ ሁሌም ተወርፎ፡
ማንም ሲዝትበት እሱን ብቻ አኩርፎ፡
በሁሉም አቅጣጫ ወሎ አሁን ተነስቷል፡
መሸሹ ቀረና ወደ ግንባር ዘምቷል፡
እምነቴን ለመድፈር ከቤቴ ከመጣህ፡
ታሪኩን ልትደግም ወገኔን ካቃጣህ፡
ምናለ ይህ ፀሀይ ለአንተ ሲል ባልመሸ፡
እንዳትጠራጠር እጥፍ ነው ምላሸ፡
ተቀባብሏል አብሽር ፅዱ ነው ክላሸ፡

--------------------------------------------
የወሎ ጀግና #ያ_ሽርጥ ለባሽ፡
ያዘጋጂሻል እንደሚገባሽ፡
ለግፍሽ ሁሉ ይሰጣል ምላሽ፡
ወሎን አትንካ እንዳትበላሽ፡

በፍቅር ባደጉት በሀላል ልጆቿ፡
ትኮራለች ወሎ ሁሌም በጀግኖቿ፡
#ደምሌን ተመልከት #የጊራናን ነብር፡
#ከከረሙ_ልጅ ጋር #ምሽጉን_ሲሰብር፡
የእስላም ልጅ ታማኝ ነው አይገዛም በብር፡
የትግራይ ሙስሊሞች እኛን አልተዋጉም፡
ፍፁም ሰላም ናቸው መጥፎ አላደረጉም

ለወሎ ልጅ ትግሬ መቼም አያሰጋም፡
ምን ሴራ ቢቆመር መንገዱ ቢዘጋም፡
መድፍ ስናይፐር መትረየስ ቢተኮስ፡
ህዝቡ እንዳይገናኝ እሾህ ቢቸረኮስ፡
ትግራይና ወሎ አይነጣጠልም፡
ፍቅር ዘምሮ እንጂ በቂም አይቀጥልም፡

--------------------------------------------
የትግራይ የወሎ መሪር ጠላታችን፡
ህውሀት ብቻ ነው ችግር የህዝባችን፡
ሀያ ሰባት አመት በመከራ አኑሮን፡
ካላጠፋሁ ብሎ አሁን ደግሞ ወሮን፡
መድፍ ከተኮሰ ብሎ ወሎን ላጥፋው፡
ወሎ ተነስና ከመጣበት ግፋው፡
ተነስ ተጠራራ ሀገርክን አስከብር፡
አግስተህ ውጣበት ዘለህ እንደ ነብር፡

------------------------------------------
ጀበርናውን ለብሶ ክላሹን ወልውሎ፡
ፈገግ ይላል ፊቱ ከጦር ግንባር ውሎ፡
ፍቅር ጀግንነት ጋር እንደዚህ ነው ወሎ፡

ደረቱን ለጥይት እየገለበጠ፡
ጠመንጃ ይነጥቃል እርሳስ እንደዋጠ፡
➻#አብሽር_ወሎ___!!
ይሄ ነው ታሪኩ አይንበረከክም፡
ደፍሮ ለወረረው ሽማግሌ አይልክም፡
ለሀበሻ ምድር ወሎ ደም ገብሯል፡
እየተጨቆነ ፍቅር አስተምሯል፡
ተፈናቅሎም ደግሞ በየቦታው ሰፍሯል፡
ወሎ ከባንዳወች አልተፈራረመም፡
ለዚህም ነው መሰል ጭቆናው አልቆመም፡
#አብሽር_ወሎ__!!

ማንንም አልነካን ከምኑም የለንም፡
መጥቶ ከወረረን አማራጭ የለንም፡
ከደቡብ ከሰሜን ከሁሉም አቅጣጫ፡
ከምዕራብ ከምስራቅ አይኖርም ማምለጫ፡
የአክሱም ሙስሊሞች ዱዐ አድርገውብህ፡
አሏህ ፀሎት ሰምቶ ወሎን አስነሳብህ፡
የትግራይ ሙስሊሞች አብሽሩ አይዟችሁ፡
#አሏህ#ክፉ አይሰራም በርቱ በዱአችሁ

➻#አብሽር_ወሎ___!!
የጦለሀ ጀዕፈር የአባ ጂፋር ወንድም፡
ወሎ በታሪኩ ባንዳ ልጅ አይወልድም፡
በእምነትና ባገር ፈፅሞ አይቀልድም፡
ፈሪና ሰላቱ በጭራሽ አይወድም፡
የአርሹ ባለቤት አሏህ ከፈቀደ፡
ጌታችን ከረዳን እሱ ከፈረደ፡
#ደብረ_ፂወንና_ጌታቸው_ረዳ፡
በወሎ ራያ ላይ ይሆናሉ ፊዳ፡
ትግራዋይ ወገኔ አይገርም ታፍኖ፡
ምኞቴ ነው እኔ ማየት ሰላም ሰፍኖ፡
➻አብሽር_ወሎ__!!

በአሏህ እገዛ በጀሊሉ ጉልበት፡
ሰላም ይሁን ሀገር ብዙ ግፍ አለበት፡
#ወሎ_በጀግኖቹ_ይከበራል_አብሽር
#ሀገሩ_ተደፍሮ_አይወጣም_ሽርሽር
#አንግቶ_ይዘምታል_ያባቱን_ሚኒሽር
በተግባር ተመልከት ያን ጀግና ሽርጣም፡
ምሽግ ሰባሪ ነው ሳያወልቅ ጥምጣም፡
ወሎ በፍቅር እንጂ በፀብ አያዋጣም፡

የአሏህ ስጦታ ነው ምድሩ ጀግና አያጣም፡
ወሎን አትሳደብ #ይተዋል ጫት መቃም፡
ጠላቱን ብቻ እንጂ በዘር አያጠቃም፡
ወሎ የሀገሩን ልጅ ሀሽሽ አያጠጣም፡
ስትነካኩት እንጂ ለማጥቃት አልመጣም

▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
#አብሽር_ወሎ__!!
የሚመረትበት ፍቅር ሻይ በዳቦ፡
ወደ ግንባር ሔዷል ዘምቷል ወረባቦ፡
ወሎ አሁን መሮታል ሰሜኑም ደቡቡ፡
መጥተዋል ሊገርፉህ ትጥቅ እንዳነገቡ፡
ሴራህን አክሽፈው ሰላም ለመገንባት፡

አቅፈው ሊዘይሩ የ#ትግራይን አባት፡
በጭካኔ ይዘህ አንተ ስታፍናት፡
ካንተ ሊለያዩ የ#ትግራይን እናት፡
የ#ወሎ_ኦሮሞ የጦር ጠበብቶቹ፡
ወደ ራያ ግንባር ዘምተዋል ጀግኖቹ

ከነፋሪስ ሀገር ከጅሌ ጥሙጋ፡
ዘምቷል የወሎ ልጅ ወሎን ሊያረጋጋ፡
ያንን የሀገር ጠላት ሊገርፈው በአለንጋ፡
ከባቲ ከሚሴ ከአርጡማ ፋርሲ፡
ተሟል የወሎ ልጅ #ጂርቱ እያለ #አከሲ፡
የወሎ መከራ ያንቀጠቀጣቸው፡
ቀጠን ቀጠን ያሉት ጀግንነት መጧቸው፡
የወሎ አናብስቶች መጡ ጠብቃቸው፡
ጀግና ናቸውና ፍፁም አይፎክሩም፡
ለፍቅር ነው እንጅ አያቀረቅሩም፡
ታሪኩ ይናገር ጠላት አያከብሩም፡
ምሽግህን ሰብረው ሳይገርፉህ አይቀሩም፡
➻#አብሽር_ወሎ__!!
ወሎን አያውቀውም ቀረርቶ ፉከራ፡
#ቢበዛም_ጠላቱ_ቄስና_ደብተራ፡
ሁሉን አስተናግዷል ፈቅዶ በየተራ፡
ሀገሩን በመሸጥ ወሎዬ አይታማም፡
ልቡ ተራራ ነው ማንንም አይሰማም፡
የጦር ሜዳው ንጉስ በልበት ሽርሽር፡
አሏህ ይከተልህ የወሎ ልጅ አብሽር

▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
        #በኑረዲን_አል_አረቢ
▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi