Get Mystery Box with random crypto!

ሲንቄ ባንክ ሲንቄ ባንክ በአዲስ መለያ (Brand) የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ሲንቄ ባንክ

ሲንቄ ባንክ በአዲስ መለያ (Brand) የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።

ሲንቄ ባንክ ከማይክሮ ፋይናንስ ወደ ባንክ በማደግ ከዚህ ቀደም ይሰጠው የነበረውን የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎትም በማካተት የተሟላ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱንም ገልጸዋል።

ሲንቄ ባንክ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩ 405 ቅርንጫፎቹ መካከል 250ዎቹ የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን ፈቃድ ከብሔራዊ ባንክ አግኝቷል።

ሲንቄ ባንክ 15 ቢሊየን ብር የተመዘገበና 7 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል በመያዝ የአገሪቱን የባንክ ኢንዱስትሪ የተቀላቀለ ባንክ ነው።