Get Mystery Box with random crypto!

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ . በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአነስተኛ ወጪ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ
.
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአነስተኛ ወጪ ተገንብተው የተጠናቀቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው ዕለት ተመርቀው ለተጠቃሚዎች ይተላለፋሉ።

ባለፉት 60/90 ቀናት በልዩ ድጋፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአነስተኛ ወጪ ተገንብተው የተጠናቀቁት እነዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው ዕለት ተመርቀው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ 70 ያህል አባወራዎች ይተላለፋሉ ተብሏል።

ግንባታቸው የተጠናቀቀው እነዚህ ባለ ሶስት ብሎክ ጂ+1 የጋራ መኖሪያ ቤት እያንዳንዳቸው ባለ አንድ መኝታ ክፍል ያሏቸው ሲሆን የህዝብ ቤተ መጽሃፍት፣ የጋራ የሆነ የምግብ ማብሰያ ቦታዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል።