Get Mystery Box with random crypto!

ለመምህራን በእጣ የተላለፉ ቤቶችን የተመለከተ ማስታወቂያ ለመምህራን የተላለፉ 435 የጋራ መኖሪያ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ለመምህራን በእጣ የተላለፉ ቤቶችን የተመለከተ ማስታወቂያ

ለመምህራን የተላለፉ 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውል የመፈፀም ሂደት ነገ በ12/08/16 ዓ.ም  ይጀመራል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ6/07/2016 ዓ.ም በተለያየ ምክንያት ሳይተላለፋ የቀሩ 435 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ለመምህራን በእጣ መተላለፋቸው ይታወሳል።

በመሆኑም የቤት እድለኛ የሆናችሁ መምህራን ከሀሙስ ማለትም ከ12/08/16 ዓ.ም ጀምራችሁ  በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ውል መፈፀም የሚያስችል ሂደት እንድትጀምሩ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ይገልፃል።

ተዋዋዮችም በአለቱ  የታደሰ መታወቂያ ፣ በተጨማሪም መምህር/ት መሆናችሁን የሚያሳይ ማስረጃ የት/ቤት መታወቂያና  ከትምህርት ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ ይዛችሁ  መገኘት አለባችሁ በማለት ኮርፖሬሽኑ እያሳሰበ በዉክልና ለመስተናገድ የምትመጡ አካላት  በቂ ማስረጃ መያዛችሁን አትዘንጉ።

ማሳሰቢያ

- በ60 ቀናት ዉስጥ ቀርቦ ዉል ያልፈጸመ እድሉን እንደተወ ተቆጥሮ ተጠባባቂዎች በቅድመ ተከተል እንደሚስተናገዱ እናሳስባለን!

- ተዋዋዮች ለመዋዋል ስትመጡ ከታች የተቀመጠውን መስፈርት ታሳቢ እንድታደርጉ እናሳስባለን!

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን