Get Mystery Box with random crypto!

ሳማንታ ፓወር በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያን፣ ኬንያን እና ሶማሊያን ይጎበኛሉ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

ሳማንታ ፓወር በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያን፣ ኬንያን እና ሶማሊያን ይጎበኛሉ

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማትና ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በተያዘው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ እንደሚያቀኑ ገልፀዋል፡፡
ኃላፊዋ በአገራቱ በሚኖራቸው ጉብኝት ድርቅን ተከትሎ እየተከሰተ ባለው ሰብአዊ ቀውስ ምክንያት የተጎዱ ዜጎችን እንደሚጎበኙ አስታወቀዋል፡፡
ሳማንታ ስለጉብኝታቸው የተናገሩት፣ USAID ለአፍሪካ ቀንድ አገራት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገደማ ድጋፍ መስጠቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
ድጋፉ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ሶማሊያ ለሚገኙ ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ የሚውል መሆኑን ገልጸዋል፡፡