Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር በለጠ ሞላ ከሊቀመንበርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ! የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስ | Arat Kilo Media - አራት ኪሎ ሚዲያ

ዶ/ር በለጠ ሞላ ከሊቀመንበርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ!

የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ነው። አብን ካለበት ተቋማዊ ችግር ተላቆ ተጠባቂ ሚናውን እንዲወጣ ዶ/ር በለጠ ሞላ ጌታሁን መፍትሄ ያሉትን ማዕከላዊ ኮሚቴው ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚከተሉትን ነጥቦች አቅርበዋል።

፩. ዶ/ር በለጠ ሞላ ከሊቀ-መንበርነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርበዋል

፪. የአብን ነባሩ ሥራ - አስፈፃሚ የድርጅቱ የችግር ማዕከል በመሆኑ መልቀቂያ እንዲያስገባና በአዲስ አመራር እንዲተካ

፫. ድርጅቱን በጊዜያዊነት የሚመራ ሊቀ-መንበር እንዲሰየም ፣የጉባኤ አመቻች እንዲመረጥና በአንድ ወር ውስጥ ጉባኤ ተጠርቶ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ሥራ አስፈፃሚ እንዲዋቀር ጥያቄ አቅርበዋል።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ምን ይወስን ይሆን?
Mulugeta Anberbir