Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የእምየ #ኢትዮጵያ ልጆች እንዴት ቆያችሁ ዛሬ በጸሎት አማካኝነት ስለም | መርጌታ አለምአየሁ

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ የእምየ #ኢትዮጵያ ልጆች እንዴት ቆያችሁ

ዛሬ በጸሎት አማካኝነት ስለምንጠቀምበት #መፍትሔ ሀብት እናያለን

#መፍትሔ_ሀብት_ምንድን_ነዉ ?

#መፍትሔ ሀብት ማለት በእለት ተእለት እንቅስቃሴአችን ስኬት እንዲኖረን የሚያደርግ የቀደምት ሊቃውንት የአባቶቻችን ጥበብ ነው።

የሰው ልጅ በእለት ተለት በሚያደርገው የእቅድ ማሳካትና ኑሮን የማሸነፍ ዘዴ እንቅስቃሴው ላይ የተለያዩ እክሎች ሲያጋጥሙት ይስተዋላል።
ለምሳሌ ፦
#አገኝብሎ ማጣት
#ብድር ጠይቆ አለማግኘት
#እሸጥብሎ አለመሸጥ
#እገዛብሎ አለመግዛት
#አበድሮ አለመመለስ (መከልከል)
#ይዞ በረከት ማጣት
#ለፍቶ ድካመ ከንቱ መሆን
#ሰርቶ እንዳልሰራ መሆን
#አስቦ መቅረት
#ጀምሮ አለመቋጨት
#ሥራ ጀምሮ ከስሮ መውጣት
#ከጓደኛ ጋር እኩል ተሰልፎ ወደ ኋላ መቅረት......ወዘተ
እንዚህ ሁሉ የሰው ልጅ የኑሮ ፈተናዎች ናቸው።

ታዲያ ይህን ችግር ለመቋቋምና ለማስወገድ እንዲሁም በእንቅስቃሴአችን ሁሉ ስኬት ለማምጣት ቀደምት ጠቢባን አባቶቻችን ብራና ፍቀው ቀለም በጥብጠው ብዕር ቀርፀው የተለያዩ ጥበቦችን በብራና መጻሕፍቶቻቸው ጽፈው ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ አስቀምጠውልን አልፈዋል።
ታዲያ እኛም ወግና ባህላችን ጠብቀን የአባቶቻችን ጥበብ በመጠቀም ችግሮቻችን ማስወገድና ስኬት ማግኘት እንችላለን።

#መፍትሔ ሀብት
፩, በጸሎት አማካኝነት ከእለት እለት በመጸለይ
፪, በእፅዋት አማካኝነት በመጠመቅ ፣በመብላት ፣በመታጠን ፣ሰርቶ ከቤት በማስቀመጥ ፣ከቤት በመቅበር እና በኪስ በመያዝ ይከናወናል
ከእነዚህም ውስጥ ዛሬ በጸሎት አማካኝነት የሚያገለግል #መፍትሔ ሀብት እነሆ
፩. ይህን ጸሎት ጥዋት ጥዋት ከምኝታዎት ሲነሱ ፯_( 7 ) ጊዜ እየጸለዩ ጸሎቱን ሲጨርሱ የእራሰዎትን ምራቅ ከእጀዎት ላይ እትፍትፍ ብሎ ግንባርን እየተቀቡ መውጣት
፪. በቅባ ቅዱስ ላይ ሰባት ጊዜ ጸልዮ ግንባርን እየተቀቡ መውጣት ነው ።
#ገብረ ሐና ከሚለው ላይ የራስን ስም ማስገባት
ይህ ጸሎት የተፈተነ የአባቶች ጥበብ ነው አክብረው በፈሪሐ እግዚአብሔር ይያዙት

#ጥበብ ትሔይስ እምኩሉ መዛግብት እንዳለው ሊቁ
የቅድመ አያቶቻችን ጥበብ ከወደቀበት እንፈልገው እናንሳው።