Get Mystery Box with random crypto!

#ሰላም #ጤና #ፍቅር #ኢትዮጵያ ሰላም ፍቅር ጤና ለሁላችሁም ቤተሰብ እና ለሰው ልጅ በሙሉ እየተመ | መርጌታ አለምአየሁ

#ሰላም
#ጤና
#ፍቅር
#ኢትዮጵያ
ሰላም ፍቅር ጤና ለሁላችሁም ቤተሰብ እና ለሰው ልጅ በሙሉ እየተመኘሁ ዛሬም እንደተለመደው በጥያቄያችሁ መሰረት ስለ #ቡግር ማጥፍያ እንሆ!

#ኢትዮጵያ ታበፅሕ እደዊሃ ለእግዚአብሔ!

ብጉር እንዴት ይከሰታል?

የተለያየ የብጉር አይነቶች አሉ በጣም የተለመደው ግን በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚከሰተው ነው። ለአቅመ አዳም እና ሄዋን ስንደርስ የሆርሞናችን መጠን ይጨምራል በተለይ ቴስቴስትሮን። ይህ የሆርሞን ለውጥ የቆዳችን ዕጢ ብዙ ዘይት(ሴበም) እንዲያመርት ያደርገዋል። በቆዳችን ቀዳዳ የሚወጣው ዘይት ዋናው ጥቅሙ ቆዳችን ጤናማ ወዝ እንዲኖረው ማድረግ ነው። ብጉር የሚጀምረው ዘይት ከሞቱ የቆዳ ሴሎች ጋር ይቀላቀልና የቆዳችንን ቀዳዳ ይዘጉታል በዚህ ውህደት ውስጥ ባክቴሪያ ያገባና ያድጋል። ይህ ውህድ ከጐን ወዳለው የቆዳ ስጋ በማፈትለክ እብጠት፣ መቅላት እና መግል ይፈጥራል።

#የሚከተሉት ብጉርን የሚያባብሱ ሁኔታዎች ናቸው፦

※ ቆዳን የሚፈገፍጉ/የሚፈትጉ ነገሮች ለምሳሌ፦ ቀበቶ፣ ታይት፣ ሄልመንት፣ እጅ ላይ የሚታሰሩ ነገሮችና የመሳሰሉትን መጠቀም።

※ የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የምያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ

※ ፊትዎን ዘወትር/በተደጋጋሚ መታጠብ እና ፊትዎን ሲታጠቡ በጣም ማሸት።

※ ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም እንዲባባስ ያደርገዋል።

※ ጭንቀት ሲኖር

※ ፊትን በተደጋጋሚ መንካት

※ ላብ በብዛት ሲያልበን

※ በፊት ላይ በዛ ያለ ፀጉር መኖር የፊት ቆዳ ዘይት/ቅባት እንዲኖረው ያደርጋል።

※ አንዳንድ መድሃኒቶች መውሰድ

※ በዘይት እና ኬሚካል ማምረቻዎች አካባቢ መስራት

※ አትሌቶችና ሰውነታቸውን የሚገነቡ ስፓርተኞች ስቴሮይድ ስለሚወስድ በብጉር የመጠቃት ዕድል አላቸው።

የብጉር መከላከያ መንገዶች

ብጉርን መከላከል አይቻልም ነገር ግን እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች አሉ ከነዚህም መካከል፦

※ በዝግታ ወይም በጣም ሳይሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም።

※ በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ።

※ ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ።

※ አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም ለምሳሌ፦ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት

※ ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ

※ ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው።

※ ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ/ማቆም ለምሳሌ ፔትሮሊየም።


#የቆየ ብጉርንም ጭምር መፍትሔ

#ነጭ ሽንኩርት ተልጦ ተፈጭቶ ግማሽ የሾርባ ማንኪያ!

#የዝግባ ፍሬ ተፈልቅቆ ቅባቱን አውጥተው ፈጭተው ግማሽ የሾርባ ማንኪያ

#ሁለቱም ውህድ በአንድ ሎሚ ውኃ አሽቶ ፊት ታጥቦ መቀባት ከዛ በኃላ ከ 3 ሰዓት በኃላ መታጠብ
የቆየ ከሆነ አንድ ቀን እየዘለሉ ለ 3 ሳምንት ይጠቀሙ
ብዙም ካልቆየ ከሳምንት እስከ ሁለት ሳምንት ይጠቀሙ ይድናል።

የዝግባ ፍሬ ካላገኙ በሁለቱም ብቻ ማድረግ ይችላል።
ሽንኩርቱ ተፈጭቶ በሎሚ ውኃ ታሽቶም መተቀም ይችላል።
ለበለጠ መረጃ 09 12 99 97 05 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።