Get Mystery Box with random crypto!

ስንፈተ ወሲብ እና መፍትሔው #ሰላም #ፍቅር #ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እና ለብርቅየ ልጆችዋ | መርጌታ አለምአየሁ

ስንፈተ ወሲብ እና መፍትሔው

#ሰላም
#ፍቅር
#ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እና ለብርቅየ ልጆችዋ ይሁን!

#ETHIOPIA

ዓለም በአስከፊው የወረርሺኝ ኮሮና በሽታ እየታመሰች አንተ ስለስንፈተ ወሲብ ትጽፋለህ ብላችሁ ብታስቡም ቅሉ!!!

ለጊዜው አስፈላጊ ሁኖ በማግኘቴ እንዲሁም ብዙ ጥያቄዎች ስለቀረብሉኝ ይህንኑ መፍትሔ ከተብኩላችሁ!

ትዳር በታኙ ስንፈተ ወሲብ!!!

ስንፈተ ወሲብ የሚለውን ቃል፣ ጠበብ ባለው ዐውዱ ሲታይ፣ከዚህም የወንድም ሆነ የሴት ብልት አለመነቃቃትንና ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ስንፈተ ወሲብ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ አለመሆን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር በሁለት መንገድ የሚከሰት ነው፡፡

የመጀመሪያው ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን፣

ሁለተኛው ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በአዕምሯዊ፣ በስነ ልቦናዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው ችግር ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን፣ ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን፣ የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስን፣ የሌላኘውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

ችግሩ ያለበት ሰው ከሚያሳያቸው ምልክቶች ዋና ዋና የሚባሉትን እንሆ!

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው፣ በጋራ ወይም በተናጠል ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ዋና ዋና ተብለው የሚታወቁት ቀጥሎ የምገልፃቸው ናቸው፡፡

– የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)

– የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)

– ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፍሳሽ በበቂ መጠን አለመመንጨት፣ የሚደረገውን የወሲብ ግንኙነት ደረቅና ህመም የበዛበት ያደርገዋል (ለሴቶች)

– የመጨረሻው የእርካታ ደረጃ ላይ አለመድረስ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች ናቸው ተብሎ ይወሰዳል፡፡

በዘመናዊ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰድ ቪያግራ ጉዳት


ቪያግራ ማንኛውም ሰው የሚወሰደው መድሃኒት አይደለም፡፡

መድሃኒቱ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የልብና የኩላሊት በሽታዎችን ያባብሳል፡፡ እንደዚሁም የደም ስሮችን በማጥበብ ስትሮክንና ደም ማነስን ያመጣለ፡፡ እነዚህ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በምንም ምክንያት ቪያግራን መውሰድ የለባቸውም፡፡

ስለሆነም በምንም መንገድ ቢሆን ቪያግራም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መወሰድ የለበትም፡፡ መድሃኒቱ በሐኪም ትዕዛዝ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ ሱስ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ሱስ ከሆነ መድሃኒቱ ካልተወሰደ በስተቀር ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ያደርሳል፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ተመሳሳይ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ስላላቸው በተቻለ አቅም አግባብ ያለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊታከምና ሊድን የሚችል የጤና ችግር መሆኑን ሁሉም ሰው ቢገነዘብ ጠቃሚ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

በተጨማሪም ላልፈው የማልፈልገው ነገር ቢኖር ከላይ የጠቀስኳቸው የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች በዘመናዊ ሕክምና ዘንዳ የታመነባቸው ችግሮች ሲሆን!!!

በተጨማሪም የክፉ መናፍስቶች ሴራም መዘንጋት አይገባንም።
ይህ ማለት በወንዶች ዘንዳ የሴት ዛር የምትባል መንፈስ!
በሴቶች በኩልም የወንድ ዛር የሚባል ትዳር በጥባጭ መንፈስ ሲጠጋንም ከላይ የተቀስናቸው ችግሮች እንደሚከሰትም ሊቃውንቶች ዘግበውት አልፈዋል።

ዘመናዊው እና የጠቢቦቹ ንግግሩ እና የቃላት አጣጣል ተለያየ እንጂ ጠለቅ ብለን ብናየው ቅሉ ተመሳሳይነት አላቸው። ከአደጋ ውጭ የሚከሰቱ ድክመቶች በዘመናዊ አነጋገር ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ብሎ ሲገልፀው የጠቢባን ቃል ደግሞ በክፉ መናፍስት ዘንዳ ችግሩ ይከሰታል ብለው ደመደሙ።

ክፉ መናፍስት ሲጠጉን አእምሯአችን እና ስነ ልቦናችን ቅድምያ እንዲቆጣጠሩት ይሆናል ።ይህ ማለት ስንፈተ ወሲብ ለመፍጠር አእምሮአችን ላይ ውጥረት መፍጠራቸው በቂ ነው ማለት ነው።

#ለምሳሌ

_የስራ ጫና
_ጭንቀት
_ፍርሃት
_ተጓዳኝ በሽታ ስኳር፣ደም ግፊት፣ካንሰር..
_ዝሙት
_ሕልመ ሌሊት
_ግለ ወሲብ...ወዘተ በመጠር የአእምሮ እና የስነልቦናዊ ጫና ይፈጥራሉ።

ያኔ ስንፈተ ወሲብ እንዲከሰት ይሆናል።
_የወሲብ ጥላቻ
_የመጨረሻ እርካታ አለመድረስ
_ብልት አለመነሳት
_ብልት ማነስ የመሳሰሉ ችግሮች ይፈጠራሉ።

ይህ ሁሉ ችግር በዕጽዋት እና በፈጣሪ ኃይል የሚስተካከል ይሆናል።

# የስንፈተ ወሲብ መፍትሔ

የአብላሊት ሥር
የዶግ ሥር
የእንቧጮ ሥር
የእንስላል ሥር
የቀስተንቻ(የሴት ቀስት) ሥር

እነዚህን እጽዋቶች ለየቅል አድርቀው አልመው ፤በትንሿ ማንኪያ ደምደም አድርገው ለክተው አንድ ላይ አምስቱ እጽዋት በማቀላቀል ማታ በግማሽ ሊትር የላም ወተት አድርገው አፍልተው ቀዝቀዝ ሲል ይጠጡ።

ይህ ድርጊት ለ ሰባት ተከታታይ ቀናት ያድርጉት ለሁሉም ስንፈተ ወሲብ መፍትሔ ይሆናል።ለብልት ማነስ ግን አይሆንም።

#ተፈትኖ ያለፈ ጥበብ
ለበለጠ መረጃ 09 12 99 97 05 ብለው በስራ ሰዓት ይደውሉ።


የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።