Get Mystery Box with random crypto!

#ሰላም #ፍቅር #ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እና ለዓለሙ ህዝብ ሁሉ ይሁን። እንዲሁም አሁን በሀገራችን | መርጌታ አለምአየሁ

#ሰላም
#ፍቅር
#ጤና ለእምየ ኢትዮጵያ እና ለዓለሙ ህዝብ ሁሉ ይሁን።

እንዲሁም አሁን በሀገራችን ላይ ያንዣበበው ክፉ

#የሪህ በሽታ መፍትሔ ቁጥር ሁለት

ከዚህ በፊት ስለ ሪህ መንስኤ እና መፍትሔ ያየን ሲሆን!
ዛሬ ደግሞ ቀለል ያለ እና በየቤታችሁ ተጠቅማችሁ መፍትሔ ታገኙበት ዘንድ እንሆ!

#ሪህ እንዳይባባስ የሚረዱ አምስት ቁልፍ ነገሮች

የሪህ ሕመም ከአኗኗራችን ጋር ተያያዥነት ስላለው የሚከተሉት እርምጃዎች የሪህ ሕመምተኞች በሽታው እንዳይቀሰቀስባቸው ሊረዱ ይችላሉ እና ተግባር ላይ ያውሉት።

1. ሪህ፣ ሰውነት ምግብን ጥቅም ላይ ከሚያውልበት መንገድ ጋር የተያያዘ ችግር በመሆኑ ሕመምተኞች የሚወስዱትን የካሎሪ መጠን በመቆጣጠር ጤናማ የሆነ ክብደት እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። ከዚህም በላይ ከልክ ያለፈ ውፍረት፣ የሰውነትን ክብደት በሚሸከሙት መገጣጠሚያዎች ላይ ጫና ይጨምራል።

2. ክብደታችሁን በፍጥነት ለመቀነስ ከፍተኛ የሆነ የአመጋገብ ለውጥ ከማድረግ ተቆጠቡ፤ እንዲህ ያለው የአመጋገብ ለውጥ በደማችሁ ውስጥ ያለውን የዩሪክ አሲድ መጠን ለተወሰነ ጊዜ ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

3. ከእንስሳት የሚገኝ ፕሮቲን አታብዙ። አንዳንዶች፣ በቀን ውስጥ የምትመገቡት ቀይ ሥጋ (የዶሮ ሥጋንና ዓሣን ጨምሮ) ከ170 ግራም መብለጥ እንደሌለበት ይናገራሉ።

4. የአልኮል መጠጥ የምትጠጡ ከሆነ ልከኛ ሁኑ። ሪህ ካለባችሁ ከነጭራሹ አልኮል አለመጠጣቱ የተሻለ ይሆናል።

5. አልኮል የሌለባቸው መጠጦችን በብዛት ጠጡ። ይህ ዩሪክ አሲድ ከሰውነት ታጥቦ እንዲወጣ ለማድረግ ያስችላል።

#የዱባ ፍሬ ለሪህ በሽታ መፍትሔ ነው።

በቅድምያ ስለ ዱባ ጥቅሞች በትንሹ ሊለቃውንት ዶክተሮች የተደረገ ጥናት ከስር አስቀምጥላችኃለሁ።

#የዱባ ፍሬ የጤና ጥቅሞች

1. ለልብ ጤናማነት
የዱባ ፍሬ በቀን ውስጥ ልናገኘው የሚገባውን የማግኒዝየም መጠንን በግማሽ ስለሚይዝ ለልብ ጤናማነት ለአጥንት እንዲሁም ለጥርስ እና ለደም ስሮች ከፍተኛ ጠቃሚነትም አለው፡፡ ማግኒዝየም ድንገተኛ የልብ ሕመምን እና ስትሮክን የመከላከል ጥቅምን ይሰጣል፡፡
2. በሽታ የመከላከል አቅምን ማዳበር
ዚንክ የሚባለው ንጥረ ነገር በዱባ ፍሬ ውስጥ ይገኛል፡፡ ዚንክ ለሌሎች ዕድገትና ክፍፍል ውስጥ፣ እንቅልፍ፣ የማሽት እና የመቅመስ ችሎታችን እና ለዓይን ለቆዳ ጤና ጠቃሚ ነው፡፡
3. በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው
የዱባ ፍሬ እንደ ተልባ እና ሌሎች ፍሬዎች በጣም ጠቃሚ በሆነው በኦሜጋ 3 የበለፀገ ነው፡፡

4. ለፕሮስቴት ጤናማነት
ለወንዶች ጤንነት ጠቃሚነቱ የተረጋገጠው የዱባ ፍሬ በተለይም ለፕሮስጤት ጤናማነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጥናቶች አሳይተዋል፡፡
5. ፀረ ስኳር ሚና
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ኢንሱሊንን መጠን በማመጣጠን ከስኳር ሕመም ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሕመሞችን ይከላከላል፡፡
6. ላረጡ ሴቶች
የተደረገ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የዱባ ፍሬ ጠቃሚ የሆነውን የኮሌስትሮል ዓይነት በመጨመር እና የደም ግፊት፣የእራስ ምታት፣የመገጣጠሚያ ሕመሞችን በመቀነስ ጠቃሚነትን ይሰጣል፡፡
7. ለጉበት እና ልብ ጤናማነት
በፋይቦር፣የአንቲኮክሲደንት እና ጤናማ ቅባት የበለፀገው የዱባ ፍሬ ለልብ እና ለጉበት ጠቃሚም ነው፡፡
8. ለጥሩ እንቅልፍ
በዱባ ፍሬ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ትራይፕቶፋን የሚባል ኦሚኖ አሲድ ሰውነታችን ወደ ሴሮቶኒን ቀጥሎም ወደ ሜላቶኒን የእንቅልፍ ሆርሞን በመቀየር ይጠቀምበታል፡፡ ከእንቅልፍ በፊት የዱባ ፍሬን መመገብ ለሰውነታችን የሚገባውን ዕረፍት እንዲያደርግ ይረዳዋል፡፡

9. ለካንሰር ተጋላጭነትን ይቀንሳል፡፡
የዱባን ፍሬ መመገብ ለጡት ካንሰር፣ለጨጓራ ካንሰር፣ለሳንባ ካንሰር፣ለአንጀት ካንሰር ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ የስነ-ምግብ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
10. የውንድ የዘር ፈሳሽ ጥራትን ያሻሽላል (sperm quality)
በዱባ ፍሬ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ዚንክ የተሰኘው ንጥረ ነገር ለውንድ የዘር ፈሳሽ ጥራትን ይጨምራል፡

#የሪህ መፍትሔ ከነ አጠቃቀሙ

#የዱባ ፍሬ ( ዕፀ ገላውዴዎስ)

የዱባ ፍሬውን በንጽህና በርከት አድርገው በማድረቅ በንጽህና ደቁሰው ዶቄቱን በማዘጋጀት!

1ኛ, ከ20 ዓመት እስከ 50 ዓመት ላሉ ሰዎች አንድ የሾርባ ማንኪያ የተደቆሰ የዱባ ፍሬ በአንድ ሌትር አጓት በጥብጠው ጧት ጧት በባዶ ሆድ ለ 14 ቀን አድርገው መጠጣት ነው።

2ኛ, ከ 20 ዓመት በታች እና ከ50 እስከ 80 ዓመት በላይ ላሉ ሰዎች ግማሽ የሾርባ ማንኪያ የዱባ ፍሬ በግማሽ ሊትር አጓት በጥብጠው ለ 8 ቀን በየቀኑ ይውሰዱ።

ይህ መፍትሔ እሙን እና የተፈተነ #የሪህ በሽታ መፍትሔ ነው።

ይህ መልእክት ብዙዎች የሪህ መፍትሔ ለሚሹ ሰዎች ይደርስ ዘንድ በፈቃደኝነት #SHARE ያድርጉ።

ለበለጠ መረጃ 09 12 99 97 05 በስራ ሰዓት ይደውሉልን ።

#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።

09 12 99 97 05