Get Mystery Box with random crypto!

ፀሎተ ነድራ የተሰኘው ጥንታዊ መፅሐፍ ሊቃውንቶቻችን ማንኛውም አይነት ተላላፊ በሽታና በሰውነት ውስ | መርጌታ አለምአየሁ

ፀሎተ ነድራ የተሰኘው ጥንታዊ መፅሐፍ ሊቃውንቶቻችን ማንኛውም አይነት ተላላፊ በሽታና
በሰውነት ውስጣዊ አካላችን ውስጥ የሚፈጠሩ ቁስለቶችን ለመፈወስ ይጠቀሙበት የነበረ
ታላቅ የጥበብ መፅሐፍ ነው። ይህ መፅሐፍ በይዘቱ ትልቅ ሲሆን እንደሌሎቹ የህክምና
መፃሕፍት ሁሉ የራሱ ጠልሰሞችና ገቢሮች አሉት።
ይህን መፅሐፍ ሊቃውንቶቻችን በመጠቀም አሁን AIDS በመባል የሚጠራውን አስከፊ
በሽታ ይፈውሱበት እንደነበር የመፅሐፉ ሊቃውንት ያስረዳሉ። እንዲሁ በመፅሐፉ ላይም
እንዲህ የሚል የፀሎት ቃል ይገኛል :
" በመለኮተ አብ ወወልድ ወመንፈስ አሐዱ አምላክ አውግዙሞ ለባርያ ወሌግዎን ለኤድስ
ወለካንሰር ለምትሐት ወለፍልፀት ለመጋኛ ወለውጋት ለንዳድ ወለቡዳ ወለኩሎሙ
መናፍስት ርኩሳን መሰርያን ይርኃቁ እምኔየ ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኪየ ዕቅእብ
ሕይውትየ ወሰርየ ሃጢአትየ ወአድኃነኒ እመከራ ስጋ ወነፍስ ለ " የክርስትና ስምዎ " አሜን
" !