Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላች | መርጌታ አለምአየሁ

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ

በቅንነት ሸር ይደረግ

ዛሬ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ስለአላት አንዲት እፅዋት ጥቅሟንና አሰራሯን እናያለን።

#እፀ ፈላፁት፦
እፀ ፈላፁት አይነቷና ተፈጥሮዋ ሦሥት አይይነት ሲሆን ሦሥቱም ለተለያየ ጥቅምና አገልግሎት ይውላሉ ።

ከሦሥቱ የፈላፁት አይነቶች ዛሬ ስለአንዷ ጥቅምና አሰራር እናያለን።እፀ ፈላፁት ለህክምና አገልግሎት
ለመፍትሔ ሥራይ
ለመፍትሔ ሐብት
ለሕዝብ መስተፋቅር
ለግርማ ሞገስ
ለገብያ መፍትሔ
ለሰላቢ መጠበቂያ
ለሥራይ መዓቅብ ወዘተ እስከ 200 ገቢር አላት ለምሳሌ የተወሰኑትን እንይ ፦

፩ ለሆድ ሥራይና ለእጀሰብእ የፈላፁት ሥሯን ከአቱች ስር ጋር ሁሉንም አልሞ ፈጭቶ ነፍቶ አንዳንድ የስኳር ማንኪያ በማር እየለወሱ ጥዋት ጥዋት በባዶ ሆድ በልቶ የአምስት ሰአት ልዩነት መፆም

፪ ለቆረባ በሽታ ስሯን ነቅሎ እያላመጡ ውሀውን መዋጥ ነው።

፫ ለከፋ ቁስል ስሯን ነቅሎ አድርቆ አልሞ ቁስሉ እስኪድን ዱቄቱን መነስነስ ነው።

፬ ለስንፈተ ወሲብ ከሴቴ እሬት ስር ከአቱች ስር ጋር አልሞ አቀላቅሎ ሰባት ቀን ሰባት ማንኪያ መቅመስ እሱን ሰባት ቀን መታጠን ነው።
፭ ለሕዝብ መስተፋቅር ማክሰኞ ጥዋት ከአለችበት ሂዶ ማርና ወተት እየረጩ የሚፈልጉትን ሐሳብ ለዚህ ለዚህ ሁኝኝ ብሎ በዝርዝር ተናግሮ ተማሕፅኖና ቃልአስገብቶ በወይራ አንካሴ ቆፍሮ በቀንድ ቢላ ቆርጦ ከትክል ድንጋይ ቀጥቅጦ አልሞ በምጣድ አጥቁሮ (አሳሮ ) ከፈለጉት ላይ በፈለጉት ቅርፅ መነቀስ ነው ።

፮ ለመፍትሔ ሀብት ሲሆን በ፬ ኛው ገቢር መሰረት ለዚህ ሁኝኝ ብሎ ቆርጦ አምቶ ወቅጦ አድርቆ አልሞ ነፍቶ ለ፯ ቀን በማር እየለውሱ መቅመስ

፯ ለግርማ ሞገስ ሲሆን በ፬ኛው ገቢር መሰረት ለግርማሞገስ ለዚህ ለዚህ ሁኝኝ ብሎ ነቅሎ አምቶ በትንሿ ጣት አፅቅ ሶስት ከርክሞ ቆርጦ ሰባቱ ቀለማትና የአንበሳ ፀጉር ጨምሮ ከትቦ በኪስ መያዝ ነው የሚያይህ ሁሉ ይሰግዳል ይርዳል ይንቀጠቀጣል

፰ ለተዘጋ ገብያ ሐሙስ በጥዋት ከአለችበት በወይራ አንካሴ ወይም በቀንድ ካራ ቆፍሮ ነቅሎ አምቶ ስሯንም ቅጠሏንም በእርጥቡ ቀጥቅጦ አልሞ በእለት ውሀ ዘፍዝፎ የተዘጋውን ገብያ ጥዋት ጥዋት ከ፭ - ፯ ቀን ቢረጩት መልካም ገብያ ይመጣል ።

፱ በመስተፋቅር ለታሰረ ሰው በስሙ ነቅሎ ከአንባጮና የሎሚ ተቀፅላ ጋር አልሞ ፯ ቀን በነጭ ማር ማቅመስ።

፲ እድሉ ለተዘጋበት ነገሮች ለተመሰቃቀሉበትና ገንዘብ ለራቀው በረከት ላጣ ሰው ስሯን ከ ፯ ላይ ነቅሎ ስሩንም ቅጠሉንም ሁሉንም በአንድ ቀጥቅጦ በእቃ ዘፍዝፎ ለ ፯ ቀን የእለት ውሀ እየጨመሩ መታጠብ ነው ሁሉም ነገር ይፈታል ያለጥርጥር ።

፲፩ ለመተት እና ድግምት መመለሻ ስሯን እንደሟሟጫ መጠቀምና በኪስ መያዝነው ።

፲፪ አልረባ ላለ ከብት (ሀብት) ስርና ቅጠሏን ከአሰርኩሽ ስር ጋር ቀጥቅጦ አልሞ በመራራ ቅል ዘፍዝፎ በረቱን ፫ ወይም ፭ ቀን ቢረጩት ሀብት አይሞትም ይረባል።

፲፫ ባል ላጣች ሴት ስሯን ከሞይደር ስር ጋር አቀላቅሎ ለ ፯ ቀን በመራራ ቅል ዘፍዝፎ ትጠመቅ ሰባት ቀን ከዚያው ቀንሳ ትታጠነው ከሁለቱም አልሞ ሰባት ቀን በነጭ ማር ትቅመሰው አይነ ጥላዋ ይፈታል ታገባለች ።

09 12 99 97 05 በስራ ሰዓት ይደውሉ