Get Mystery Box with random crypto!

የሰው ነገርን የማትወደዋ ዕጽ #የሰው ነገር ~የሰው ነገር ቆላማ አከባቢ ላይ በክረምት ወራት በ | መርጌታ አለምአየሁ

የሰው ነገርን የማትወደዋ ዕጽ
#የሰው ነገር

~የሰው ነገር ቆላማ አከባቢ ላይ በክረምት ወራት በቅላ የምትገኝ እጅግ ድንቅ ዕጽ ናት።

~የሰው ነገር ዝርያዋ በአበባ ቀለም ወደ ፫ ዓይነት ዝርያ ያላት ስትሆን! በዓይነት ደግሞ ትንሿ ከ 10 ሳንቲ ሜትር የማትበልጥ ስትሆን ትልቋ ደግሞ እሾህ ያላት ከ 50 ሳንቲ ሜትር በላይ የምታክል ዕፅ ናት።

~የሰው ነገር ካደገች በኃላ ልክ እንደጃንጥላ ሆና ከራሷ ላይ ብዙ ቅጠሎች ያላት ድንቅ ዕፅ ናት።

~የሰው ነገር ከዕጽዋቶች ለየት የሚያደርጋት እጅግ ልዩ እና ውስብስብ ያለ ታሪክ ያላት ሲንኳት የምትሰበሰብ ሲለቋት የምትዘረጋ ድን ዕፅ ናት።

~የሰው ነገር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላት ዕፅ ስትሆን፦
፦ለንቃተ ህሊና
፦ለዓይን ህመም
፦ለራስ ህመም
፦ለአጓጉት ለቆዳ በሽታ
፦ለዓቃቤ ርእስ....ወዘተ ስትሆን ትስተዋላለች።

ከዚህ በፊት በሰው ነገር የሚሰራ ለንቃተ ህሊና የሚሆን መልካም እውቀት ያካፈልኳችሁ ሲሆን ዛሬ ደግሞ ለራስ ሕመም ለማይግሬን ማዳኛ ስትሆን እንሆ!

#የራስ ህመም መፍትሔ
#የሰው ነገር ቅጠል እና ሥር
በብዛት በማሰባሰብ አድርቀው በንፅህና ወቅጠው አዘጋጅተው!
#በንፁህ ቅቤ በመለወስ መሀል ራስ ላይ ጧት መቀባት ለ 3 ቀናት ቢጠቀሙ የቆየ የማይግሬን በሽታ ሙሉ መፍትሔ ይሰጣል።
ለአጓጉትም ሲሆን በቅቤ ለውሰው ቀን በቀን እየታጠቡ በስሱ የሰው ነገር ቅጠል በማዘጋጀት አጓጉት ያለበት የቆዳ ክፍ መቀባት።
ይህ ድርጊ ለሰባት ቀናት ቢጠቀሙ ቶሎ ይድናሉ።

#የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ።
ለበለጠ መረጃ ከስር ባለው ስልክ በስራ ሰዓት ይደውሉልኝ።

09 12 99 97 05