Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም እንዴት ናችሁ ወዳጆች ------------------------------------- ዛሬ አንድ | መርጌታ አለምአየሁ

ሰላም እንዴት ናችሁ ወዳጆች
-------------------------------------
ዛሬ አንድ ድንቅ ጥበብ የሚከወንበትን እፅ ላስተዋውቃችሁ በተቀመጠው ገቢርም በመጠቀም ትርፋማ መሆን ትችላላችሁ።

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት እፅ #እፀሀሎ ይባላል።ይህ እፅ በአብዛኛው በቆላ እና በረሃማ ቦታ የሚበቅል ሲሆን አልፎ አልፎ በወይና ደጋም ይበቅላል።

እፁ እጅግ በርካታ ጥቅሞችን መከወን እና ማስከወን የሚችል ነው።ከነዚህም ጥቅሞቹ መካከል ከነገቢራቸው ጥቂቶቹን ላሳውቃችሁና ትጠቀሙበት ዘንድ መልካም ፈቃድ ይንገስበት!

1.ገንዘብ ለመስለብ ወይንም ሀብት ለማከማቸት

የዕፁን ስር ፊትን ወደ ምስራቅ በማዞር እፅ አንግስ ድግምትን በመድገም ከ7ቦታ ላይ በወይራ አንካሴ በመቆፈር አድርቆ አልሞ ፈጭቶ አርብ ለቅዳሜ፣ማክሰኞ ለረዕቡ እና ረቡዕ ለሀሙስ ማታ ከራት ጋር ለቤተሰቡ ወይንም ለብቻችሁ ብሉ።እነዚህ ቀናት የማይመቿችሁ ከሆነ ደግሞ ያላችሁበትን አካባቢ ዋና የገበያ ቀን ተጠቅማችሁ ለ3ቀን መጠቀም ትችላላችሁ።ከምግብ ጋር ስትመገቡት ሚያመጣው ምንም የጎንዮሽ ጉዳት ስለሌለው ስጋት አይኑራችሁ።

ከምግብ ጋር አብሮ ለመብላት የማይመቻችሁ ከሆነ ደግሞ ስሩን ሳታደርቁ 2ራስ ነጭ ሽንኩርት እና ከ3ሎሚ የወጡ 9የውስጥ ፍሬዎችን አንድላይ አድርጋችሁ ጨቅጭቃችሁ መስቀለኛ መንገድ ላይ ማክሰኞ ቀን ከጥዋቱ ከ12ሠዓት በፊት መጣል ትችላላችሁ።ከጣላችሁት በኋላ ቤት እስክትደርሱ ወይንም ስራ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ ዞሮ ማየት አይቻልም።

2.ብድር ወስዶ አልመልስ ያለ ሰው ብድርዎትን እንዲመልስ ለማድረግ።

ይህን ለማድረግ 2መንገድ አለው።
*.የእፁን አበባ 3 ከ3ቦታ የተለያየ ተክል ልልይ በድምሩ 9አበባዎችን እፅ አንግስን በመድገም ቁረጡ።ከዛም የተቆረጡት አበባዎች አንድ ላይ በንፁህ እቃ በማድረግ "በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ፀሎተ በእንተ መልስኦሙ ፍታህ ወአድህን ነዋየ አነ(የአበዳሪው ስም)በአደ ሰጥኦሙ ለ(የተበዳሪው ስም)መልስወሰጥ አሰጥ አሰልቅጥ ይህህህ ክሎሎሎ ውልደ ፈቃዴኦሙ ለእሱ" የሚለውን ድግምት 9ጊዜ ደግማችሁ አበባውን በብረት ምጣድ አሳርራችሁ ቆልታችሁ አድቃችሁ በእለት ውሃ በጥብጣችሁ ከበራችሁ በግራ በኩል በውጭ ቆማችሁ የተበጠበጠውን አስማት ወደ ቤታችሁ ውስጥ ርጩት ለ1ቀን ብቻ።ከዛን እለት ጀምሮ በህያው ያለ ማንኛውም ገንዘባችሁን የወሰደ ሰው እናንተን ለማግኜት እናገንዘባችሁን ለመመለስ ውሳኔ ላይ ይደርሳል።ገንዘባችሁንም እናንተ ለተበዳሪው በምትሰጡት ፈቃድ መሰረት ይመልስላችኋል።
*የእፁን ቅጠል ከ3ቦታ ላይ እፅ አንግስን ደግማችሁ ረቡእ ወይም አርብ ቀን ቆርጣችሁ ቅጠሉን በእጃችሁ አሻሽታችሁ ማንንም ሰው ሰላም ሳትሉ በውሃም ሳትጣቡ ብድር የወሰደባችሁን ሰው ፈልጋችሁ ሰላም ብትሉ በናንተ ስምምነት ምክንያት ገንዘባችሁን ይመልሳል።

ሌሎች አገልግሎቶቹ
3.ለመሰውር ከቁራ እንቁላል ጋር
4.ቤትናንብረትን ከሌባ እና ከእሳት ለመጠበቅ በመራራ ቅል ከጊንጥ ራስ ጋር ተዘፍዝፎ

~~~~~~~
"ጥበብን ያወቀ እንጅ የናቀ አይጠቀምባትም"
ይዘዙ በጥበብ ዓለምን ይግዙ

ስልክ 09 12 99 97 05