Get Mystery Box with random crypto!

#የአጋንንት ! #የዓይነ ጥላ! #የዛር መንፈስ! መራቅያ የብራና አስማተ ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይህ | መርጌታ አለምአየሁ

#የአጋንንት !
#የዓይነ ጥላ!
#የዛር መንፈስ! መራቅያ የብራና አስማተ ቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ይህ ነው::

#ይህ ጸሎተ ሚካኤል በቀደምቶቹ በብራና ላይ ተከትቦ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ ቆይቶ ይሄው እኛ ዘንድ ደርሷል::

በድርሳኑ እንደሚለው ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠ ልዩ እና ኅቡዓት አስማት ዲያብሎስን ድል መንሻ ነውና ልብ ይበሉ::

#እኛ እኮ በብዙ መንገድ የታደልን ግን ደግሞ በአጉል ፍርጃ ማንነታችን ያጣን ሰዎች ሆንን እንጂ የተሰጠን እና ያለን ነገር ብዙ ነው::

#ለረዥም ጊዜ በዚሁ ቤት አዲስ ነገር መላክ እና ማስተላለፍ ካቆምኩኝ ቆየሁ ይህ የሆነበት ምክንያትም ከአሁን በፊቱ በተሻለ መልኩ እውቀትን ለማቀበል በማሰብ ነውና ይቅር በሉኝ::

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ቶሎ ቶሎ እውቀቶችን ለማስተላለፍ እሞክራለሁ::ወዳጆቼም እንዲሁም ቤተሰቦቼ እንደበፊቱ በአጋንንት ወጥመድ ውስጥ ላሉ ይደርስ ዘንድ እንዲሁም በጸሎተ ሚካኤል በቤታቸው ከችግራቸው ይላቀቁ ዘንድ!

መልእክቱን ለወዳጆቻችሁ አጋሩ!

ገቢሩም:

#በንጽህና ጧት ጧት 3 ወይም 7 ጊዜ በውኃ ላይ ማድረስ
#በቅብዓ ቅዱስ ላይ ጸሎት በማድረስ የታመመው አካላችን መቀባት
#ስራ ባይሳካልን ጧት በባዶ ሆድ ጸሎቱን አድርሰን መሄድ
#እንዲሁም ለማንኛውም ችግራችን አስማተ ሚካኤል በቀይ ቀልም በልሙጥ ወረቀት ከነጠልሰሙ ጽፈን አክብረን ብንይዘው ይሆንልናል::

የቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ አይለየን!

በአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ እና በፈጣሪ ኃይል፣ ከህይወትዎ ላይ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችልና፣ እንዲሁም የብራና መጽሐፍት ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ::


0912999705
0912999705