Get Mystery Box with random crypto!

#ቁጥር_፫ #ስንፈተ_ወሲብ #ስንፈተ ወሲብ ማለት ምን ማለት ነው ?? ስንፈተ ወሲብ ማ | መርጌታ አለምአየሁ

#ቁጥር_፫ #ስንፈተ_ወሲብ

#ስንፈተ ወሲብ ማለት ምን ማለት ነው ??

ስንፈተ ወሲብ ማለት የወንድም ሆነ የሴት ብልት አለመነቃቃትንና ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ስንፈተ ወሲብ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ አለመሆን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው፡፡

የስንፈተ ወሲብ ችግር በሁለት መንገድ የሚከሰት ነው፡፡
1. ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር
ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን

2. ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በአዕምሯዊ፣ በስነ
ልቦናዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው ችግር ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን፣
ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን፣ የመጨረሻው እርካታ ላይ
አለመድረስን፣ የሌላኛውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ ለግንኙነት
ዝግጁ ያለመሆንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

ከስነ አካላዊ ወይም ከስነ ልቦናዊ የተነሳ የሚመጡ የግብረ ወሲብ ችግሮችና ዓይነታቸውን ተረድቶ መፍታት አስፈላጊ ነው
፩. #መንስኤ እስኪት ፦ የሚጠቅመው ግንኙነት ለማድረግ በምንዘጋጅበት ወቅት
የብልት መሞትን ወይም አለመነሳትን የሚያስወግድ ነው
፪. #መፅንኤ እስኪት ፦ የሚጠቅመው ግንኙነት በምንፈፅምበት ሰዓት ብልታችን
የሚልፈሰፈስብንን የሚያጠነክር የሚያበረታ ነው
፫. መፍትሄ እስኪት ፦ የሚጠቅመው በአንዳንድ ክፉ ሰዎች የክፋት ስራ
አማካኝነት በድግምት የታሰረ ብልትን የሚፈታ ማለት ነው
፬. #ዘኢያወርድ/ ገትር ፦ ቶሎ ለሚጨርሱ ሰዎች የሚያቆይ ረዘም ላለ ጊዜ ግንኙነት እያረጉ እንዲቆይ የሚረዳ ነው
፭. #ፀላኤ ወሲብ (ዓይነ ጥላ) ፦ የግብረ ስጋ ጥላቻ ወይም ፍራቻ
፮. #የብልት ማነስ

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው፣ በጋራ ወይም በተናጠል ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ዋና ዋና ተብለው የሚታወቁት
የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)
የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)
ለግንኙነት ዝግጁ የሚያደርግ ፍሳሽ በበቂ መጠን አለመመንጨት፣ የሚደረገውን የወሲብ ግንኙነት ደረቅና ህመም የበዛበት ያደርገዋል (ለሴቶች)
የመጨረሻው የእርካታ ደረጃ ላይ አለመድረስ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች ናቸው ተብሎ ይወሰዳል፡፡.

ልብ ይበሉ
በዘመናዊ ያለ ሐኪም ትእዛዝ የሚወሰድ ቪያግራ ጉዳት
ቪያግራ ማንኛውም ሰው የሚወሰደው መድሃኒት አይደለም፡፡
መድሃኒቱ የስኳር፣ የደም ግፊት፣ የልብና የኩላሊት በሽታዎችን ያባብሳል፡፡
እነዚህ የጤና ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች በምንም ምክንያት ቪያግራን መውሰድ
የለባቸውም፡፡

የቪያግራ የጎንዮሽ ጉዳት
የደም ስሮችን በማጥበብ ስትሮክንና ደም ማነስን ያመጣል
ከፍተኛ ራስ ምታት
ከፍተኛ ጭንቀት
እንቅልፍ ማጣት
ራስን መሳት
ጉንፋን የመሰለ ህመም
ማቅለሽለሽ
እንቅልፍ ማጣት
የአፍንጫ መታፈን
የመተንፈሻ አካላት ችግር
የቆዳ ሽፍታ
የመስማት ችሎታ መቀነስ
በእይታ ጊዜ የቀለሞች መዘበራረቅ
በሆድ, በጀርባ, በጡንቻዎች ወይም በመገጣጠሚያዎች ላይ ህመም

ስለሆነም በምንም መንገድ ቢሆን ቪያግራም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ መወሰድ
የለበትም፡፡ መድሃኒቱ በሐኪም ትዕዛዝ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ ከተወሰደ ሱስ
የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
ሱስ ከሆነ መድሃኒቱ ካልተወሰደ በስተቀር ወሲባዊ ግንኙነት መፈፀም የማይቻልበት ደረጃ ላይ ያደርሳል፡፡ ሌሎችም መድሃኒቶች ተመሳሳይ የሆነ የጎንዮሽ ጉዳት ስላላቸው በተቻለ አቅም አግባብ ያለው ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የስንፈተ ወሲብ ችግር ሊታከምና ሊድን የሚችል የጤና ችግር መሆኑን
ሁሉም ሰው ሊገነዘብ ይገባል ፡፡
በተጨማሪም ላልፈው የማልፈልገው ነገር ቢኖር ከላይ የጠቀስኳቸው
የስንፈተ ወሲብ ምልክቶች በዘመናዊ ሕክምና ዘንዳ የታመነባቸው ችግሮች
ሲሆን!!!
በተጨማሪም የክፉ መናፍስቶች ሴራም መዘንጋት አይገባንም።
ይህ ማለት በወንዶች ዘንዳ የሴት ዛር የምትባል መንፈስ!
በሴቶች በኩልም የወንድ ዛር የሚባል ትዳር በጥባጭ መንፈስ ሲጠጋንም ከላይ የተቀስናቸው ችግሮች እንደሚከሰትም ሊቃውንቶች መስክረው አልፈዋል።

ዘመናዊው እና የጠቢቦቹ ንግግሩ እና የቃላት አጣጣል ተለያየ እንጂ ጠለቅ
ብለን ብናየው ቅሉ ተመሳሳይነት አላቸው። ከአደጋ ውጭ የሚከሰቱ ድክመቶች በዘመናዊ አነጋገር ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ብሎ ሲገልፀው የጠቢባን ቃል ደግሞ በክፉ መናፍስት ዘንድ ችግሩ ይከሰታል ብለው ይደመድማሉ።

ክፉ መናፍስት ሲጠጉን አእምሯአችን እና ስነ ልቦናችን ቅድምያ እንዲቆጣጠሩት ይሆናል ።ይህ ማለት ስንፈተ ወሲብ ለመፍጠር አእምሮአችን
ላይ ውጥረት መፍጠራቸው በቂ ነው ማለት ነው።
እንደ ምሳሌ ብንወስደው
ዓይነ ጥላ
የስራ ጫና
ጭንቀት
ፍርሃት
ተጓዳኝ በሽታ ስኳር፣ደም ግፊት፣ካንሰር
ዝሙት
ሕልመ ሌሊት
ግለ ወሲብ በመፍጠር የአእምሮ እና የስነልቦናዊ ጫና ይፈጥራሉ።
ያኔ ስንፈተ ወሲብ እንዲከሰት ይሆናል።

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የስንፈተ ወሲብ ችግር ሲከሰትባቸው፣ በጋራ ወይም በተናጠል ከሚያሳዩዋቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ
ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን
የመጨረሻው እርካታ ላይ
አለመድረስን
የሌላኛውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መጨስሰ
ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን
የወሲብ ፍላጎት ማጣት (ለሁለቱም)
የወሲብ መፈፀሚያ አካላት ለወሲብ ዝግጁ አለመሆን (በወንዶች)
የወሲብ ጥላቻ
የብልት አለመነሳት
ብልት ማነስ የመሳሰሉ ችግሮች ይፈጠራሉ።
ይህ ሁሉ ችግር በዕጽዋት እና በፈጣሪ ኃይል የሚስተካከል ይሆናል።

#መፍትሔ
#የአደንድን ስሩን የቅሉን ፍሬውን
#የጋንቢሎ ስሩን
#የችፍርግ ስሩን
#የአብላሊት ስሩን
#የምስርች ስሩን
#የጊዜዋ ስሩን
#49 የቁንዶ በርበሬ ፍሬ

#አዘገጃጀት
ሁሉንም በንፅህና አዘጋጅቶ አልሞ ነፍቶ ከእያንዳንዱ አንዳን የሾርባ ማንኪያ የላመ ዱቄት መጥኖ አገናኝቶ ለ 7 ቀን ጥዋት በባዶ ሆድ አንዳንድ የሾርባ ማንኪያ መድኃኒት በጠላ ቀላቅሎ መጠጣት ወይም በጠጅ መጠጣት እስከ ስድስት ሰአት ምግብ አለመብላት ለስድስት ሰአት መፆም

የሚከለከሉ ነገሮች
አልኮል ፣ ፆታዊ ግንኙነት

በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ #ሸር #share ማድረግዎን እንዳይረሱ

➤ የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይቀርባል ይብራራል

0912 99 97 05
0912 99 97 05በስራ ሰዓት ይደውሉ